>

ተጠያቂው ማን ነው? ኦሮሚያ፣ መተከል እና ትግራይ...!!! ያሬድ ሀይለማርያም

ተጠያቂው ማን ነው? ኦሮሚያ፣ መተከል እና ትግራይ…!!!

ያሬድ ሀይለማርያም

ኦሮሚያ እና መተከል፤

በተደጋጋሚ በኦሮሚያ ክልል፣ በወለጋ ዞን እና በቤኒሻንጉል ክልል፣ መተከል ዞን በንጹሀን ዜጎች ላይ ለሚፈጸመው ተከታታይ ጥቃት ኦነግ ሽኔ እና ሌሎች ታጣቂ ጏይሎች ብቻ ሳይሆኑ ጥቃቱን ባለማስቆም የክልሎቹ መንግስታት እና የፌደራል መንግስቱም እኩል ተጠያቂዎች ናቸው።

ትግራይ፤

በተመሳሳይ ሁኔታም ትግራይ ውስጥ በንጹሐን ዜጎች ላይ ለደረሰው እና እየደረሰ ላለው አሰቃቂ ጉዳት፤ በሰሜን ዕዝ እና በማይካድራ የደረሱትን እጅግ አሰቃቂ ጥቃቶች ጨምሮ በእኔ እምነት ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው በቅደም ተከተል፤
1ኛ/ በዋነኝነት ህውሃት እና አመራሮቹ፤ በተለይም የክልሉ ም/ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱን ከመለኮስ ጀምሮ ለደረሰው ጠቅላላ ጉዳት፣
2ኛ/ ገዥው ፖርቲ ብልጽግና እና አመራሮቹ፤ በዋነኝነት ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱ ተጠናቋል ከተባለበት ጊዜ አንስቶ በንጹሀን ዜጎች ላይ ለደረሰው ሰቆቃ፣
3ኛ/ የኤርትራ መንግስት፤ በተለይም ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፎርቂ፤ በወታደሮቻቸው ለተፈጸመው ዝርፊያ፣ ግድያ እና አስገድዶ መድፈር፤
ማን ይጠይቃቸዋል፣ የት እና መቼ የሚሉት ጥያቄዎች እንዳሉ ሆነው እነዚህ አካላት በአንድ ወይ በሌላ መልኩ ለተፈጸሙት የመብት ጥሰቶች፣ ጭፍጨፋዎች እና ግጭቶች፤ ማድረግ የማይገባቸውን በማድረግ ይሁን፤ ማድረግ የሚገባቸውን ባለማድረግ ተጠያቂ ናቸው ብዮ አምናለሁ።
Filed in: Amharic