ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ
በጭንቅላት ትንሽነታችሁ እኛ በዕድገት በሕብረት ዘመቻ በየሌሊቷ አብደን፤ከጦርነት የፖለቲከኛ ጭልፊቶች በተዓምር ተርፈን፤እነሆ ከዘረኞች የቁም ሞት መጠለፍን በደፈጣ ውጊያ ተጋፍጠን፤ዘንድሮም በሞት ሸለቆ ተጉዘን ከሞት ተረፍንና በፖለቲካ ፓርቲ ልማትን ተቃቅፈናል፤ ታሪካችንን በደማችን ለመጻፍ፤ዕድሜ ይሰጠን ዘንድሮም፣አሜን።ዐቢይ ኢ/ሥ/ወ
ኢትዮጵያውያን ሆይ.ዘመናት እና ዓመታት በመጡ ቁጥር የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማስተዳደር ሰዎች መንበረ ሥልጣኑን በአደራነት አሊያም በጉልበት ከሕዝብ ይረከባሉ።ይህን ኃላፊነት ግን በቃለ መሃላ ተረክበው በቅጡ እና በታማኝነት ያስተዳደሩት ደግሞ በቁጥር ውስን ናቸው፤ምክንያቱም “ሥልጣን ካልተባረከ ይላሳል በሰይጣን” ነውና።ይህ ስልጣን በየክልሎች ውስጥ ተሸንሽኖ ለያንዳንዱ ሰው ሲሰጥ ሰዉ እንደሰው አስቦ እንዲያገለግል እንደ አስፈላጊነቱ እየታየ በባለሥልጣኖች ይሰጠዋል፣አንዳንዶቹማ በየዋሕነት ተሳሳቱ፣ይህ የሥልጣን ሥጦታ ደግሞ ክልሎችን የክልል አያደርጋቸውም፤የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ።የህንን በጥሞና ሳይገነዘቡ ለጥቅማቸው ሲሉ እኛ ካልተመረጥን ብለውና ሆን ብለው አጭበርብረው እና ጨክነው የኢትዮጵያ ሕዝብን ለስቃይ፣ለመከራ፣ለስደት እና ለሞት የዳረጉትን በዘዘወትር ሠይፈ ሥላሴ ፀሎት መርገመ-ሥጋ አቀርብባቸዋለሁ፤ሌሎች ስልጣን ፈላጊዎችም ሲመጡ ርግማኑ እንደሚጠብቃቸው አውቀው ቃለ መሃላቸውን እንዲፈጽሙና “አላወቅንም ነበር”ብለው እንዳይፀጸቱ።
እነሆ፦ለኢትዮጵያ ጠላቶች የሚሆን፣የሠይፈ ሥላሴ ዘዘወትር ገጽ ፳፻፺፯ ከቁ፱ ፲፫ ፀሎት፣ ሥላሴዎች ሆይ፦”ጠላቶቻችን የሆኑ ሁሉ በመለኮታዊ ሰይፍ ይጨፍጨፉ፤ነበልባላዊ በሚሆን ቃላችሁ ሥልጣናችሁ ይንደዱ ይቃጠሉ በሲዖል የጨለማ እዘቅት ውስጥ ይዝቀጡ ወይም ይስጠሙ ኅዘን ከላያቸው እይራቅ ትካዜም ከልባቸው እይጥፋ።ጠላቶቻችን እኛ ከምድረ ገፅ ላይ እንድንጠፋ በፈለጉ ጊዜ እነሱን ራሳቸውን እንደቃየል እና ይሁዳ በዱርና በበረሃ በታትኗቸውና ሲቅበዘበዙ ይኑሩ።እሁንም እነሆ ጥላቶቻችን በእሾህና አሜከላ በተታታ ወጥመድ ውስጥ ይግቡ፤አሜን። ”
ይህን ሃቅ አጉልተን ስንመለከተው ከኢትዮጵያውያን መካከል በተለይ በዘመናችን የፖለቲካ ቅዠት ቋንቋን በተመለከተ የግዕዝን ሳይሆን የላቲን ፊደሎችን ካልሆነ በስተቀር የኢትዮጵያውያን የማህበራዊና ባሕላዊ እሴቶችን አንፈልግም ያሉ ኢትዮጵያውያን አሉ።እነዚህ ወገኖች በሃምሳ ዓመታት ውስጥ በተለያዩ ሰበብና ምክንያቶች የተፈጥሩ ቢሆኑም፣የሌሎች አገሮችን ባሕል እና ስርዓት መርጠው፦ባርነታቸውን በስምምነት ተቀብለዋል፤እናም በማህበረሰባቸው ሥም በግል የሚጠቀሙ ናቸው።ዳሩ ግን የሌሎችን ቋንቋ መጠቀማቸው የባርነት መገለጫዎች መሆናቸውን ባይገባቸውም፤ገብቷቸውም ሆን ብለው ቢያደርጉትም በየትኛውም መመዘኛ የዚህ ድርጊት ትርጉሙ ቢታይ የራስ ባልሆነ ነገር የሚተዳደር፣የራሱ አይደለምና የባርነት አንዱ ማሳያ መንገድ ነው።ሁሉም ሰዎች ባርነቱን በስምምነት የፈለጉት ባይሆኑም እንደየዘመኑ በሚነሱት ፖለቲከኞች ነን ባዮች ፍላጎት፣ በሕዝብ ስም ይፈጸማሉ።እናም ባርነቱንም ተቀብለው በባርነት የሚኖሩትንም ጨምሮ፣በአገራችን ውስጥ ብዙ ከይሲ ባሕርያት ያላቸው ሰዎች ተፈጥረዋል፤ከይሲ የሚባሉበትም ምክንያት የታሪክ ተዋረድ መረጃ ሳይኖራቸው አገሮችን ሲይዙ እንደነበሩ ወራሪዎች በሚታወቁት የባርያ ፈንጋይ ቅኝ ገዢዎች ዓይነት የተገዙ መሆናቸው ነው።ሕልውናቸውን ለራሳቸው ፍላጎት ሲሉ ባርነቱን ደግሞ ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረጋቸው ብቻ የተንኮል አስተሳሰብ ነውና ከይሲ እባቦች “አንድስ” ያስብላቸዋል።ለምሳሌ ቋንቋ አንዱ እና አስፈላጊው መግባቢያ መንገድ ነው፤ዜጎች ቋንቋቸውንና ባሕላቸውን ቢተዉ ይህንንም የባርነት ምርጫ ለዛሬዋ ጊዜ ፍላጎት የመረጡት የታሪክን ስረ-መሰረት ካለመረዳት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትን ካለመፈለግ እንደመነጨ ይታወቃል፤ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ለሰብዓዊነት ትርጉም የቀረበ ሆኖ የምናገኝበት የቋንቋ ፍቺ መንፈሳዊ እና ሥጋ ሚሥጥሮችን እናገኛለን።ስለኢትዮጵያ መንፈሳዊ እና ሥጋዊ ሚሥጥራዊነት ተዝቀው የማያልቁ ፀጋዎችን ሳናያቸው ራሳቸው እንድናያቸው ያደርጉናል፤ይህንንም የተመሠጠረ ስጦታ በሥጋዊነት በገሃድ እናገኛቸዋለን።
ስለዚህም እነዚህ ፖለቲከኛዎች ከምንላቸው መካከል ሰዎች ሳይሆኑ ጊዜያዊ ጥቅም ልባቸውን ድንጋይ፤አዕምሮዋቸውን ለሠይጣን መጋለቢያነት ያከራዩ ርጉማን ናቸው።ባጠቃላይ የፈለገውን ያህል ሰው ይገደል ግድ የላቸውም፣ የሚያሳዝነው ደግሞ “መስዋዕትነት”ነው ብለው ቀስ በቀስ በአላስፈላጊ ግድያ ውስጥ ሕይወቱን አስነጥቀው ሕዝቡን በመስዋዕትነት ሥም ያረሳሱታል፣ኋላም ኃላፊነት የጎደለው ትውልድ አድርገው ያስሉታል።ይህ ወደክምር የሚያድገው ማዘናጋት እና ማጭበርበር “በሰለጠነው ዓለም «ፖለቲካ» ይባላል”ቢሉንም እኛ ግን የ«ማታለል» ዘይቤ እንደሆነ ስናውቀው ከሃምሳ ዓመታት በላይ ሆኖናል።እንደውም በስላቅ አገላለፅ የጋዝ ብርሃን ማድረግ በዘመናዊ ምዕራባውያን ፖሊቲካ ዘይቤ ሲሆን በአጠቃላይ «ማታለል» ማለት እንደሆነ ይስማሙበታል።
በተለይ «የጋዝ ብርሃን ማድረግ» አንድ ድርጊት አልተደረገም ብሎ ለማስመስል ማለት ነው። ተደረገ እንጂ የሚሉ ሁሉ ከዚያ እንደ እብዶች ወይም እንደ ተሳቱ ደግሞ ማስመስል ነው።
የዘይቤው መነሻ ከአንድ ፩፱፴ ዓ/ም ድራማ በእንግሊዝኛ «የጋዝ ብርሃን» መጣ። በዚህ ድራማ (በኋላም በ፩፱፫፮ ዓም ፊልም)፣ አንድ ውሸታም ባል ሚስቱን በጣም ረቂቅ በሆነ በጋዝ ብርሃን ያታልላታል።በዘመናዊው ተንቀሳቃሽ ምስል ደግሞ ለዘመናችን አስተሳሰብ የሚመጥነን”አዎ ጠቅላይ ምኒስቴር”አሊያም”እንደቃልዎ ጠቅላይ መሪያችን”እንደማለትም ነው፤ለዚህም አፈጻጸም የሚረዱት ቁልፍ የቃላት መፍቻዎች ደግሞ ይታወቃሉ።
፩ ኛ /ኃይል የሚባለው የአንድን ፍላጎት በሌሎች ላይ የመጫን ችሎታ ነው።በአስተሳሰብ፣በዕውቀት፣በማጭበርበር፣
፪ ” ሥልጣን ህግን የማስከበር፣ የሌሎችን ታዛዥነት የማግኘት፣ የማዘዝ፣ እና የመፍረድ ኃይል ነው።የሚያባልግ የሚያጠቃቅም
፫ ” ህጋዊነት የሚባለው በታወቁና ተቀባይነትን ባገኙ መስፈርቶችና መርሆዎች አማካይነት ኃይልን በመጨበጥ እና በመጠቀም የሚገኝ ሲሆን አንዱ
የመንግሥት ባህርይ ነው፤እና።እንደንግድ ሥራ በሕግ የተፈቀደ ሌብነት የሚሆነው አመቺ ጊዜ እና ቦታ እየጠበቀ ሕሊናቸውን ለሠይጣን የሚያከራዩትን በሙሉ ይጠቀልላል።
፬ ” መንግሥት/አካል ህግና ሥርዓትን የማውጣት እና የማስከበር ሥልጣን ያለው አካል ነው፤የፖለቲካ ኃይሉ ናቸው። በሕገ-ሕዝብ ብቻ መዳኘት የሚችል የሕዝብ ቅጥረኛ ኮንትራት ሠራተኛ ነው።
ብዙዎቹ ፖለቲከኞች ነን ባዮቹ በፍፁም በሕገ-ሕዝብ እና በሕገ-መንግሥት ያሉትን መሠረታዊ ልዩነቶች ሳያውቁ ወይም አውቀውና ሥልጣን አቋምጧቸው ይነከሩበታ፤ መጀመሪያ ላይም እትክ እትክ ይሉና በኋላ መዋኘት ይጀምራሉ፣እስኪሰጥሙ ድረስ።የሕዝብን ሥልጣን አጭበርብረው ሲጠቀሙበት ሰነባብተው ድንገት ሌላው ሆዳም ደግሞ ከእጃቸው መንጭቆ ሊበላው ሲል ወይ ራሳቸው ይጠፉበታል አሊያም ይኖሩበታል፤ይህን የታሪክ ሃቅ የሚክድ ካለ እርሱ የዕውነተኛ ፖለቲከኛ ነው፣ለማታለል ዝግጁ የሆነ፤እንደ እነዚያ ረድፉን ለመያዝ ሲፍጨረጨር ነው፤እስኪ ያሳለፍናችውን ዓመታት ብቻ መርምሯቸው፤አንዳንድ አካይስት ፖለቲከኞችን ታገኛላችሁ፣ዶክተር ዐቢይ አህመድ የሚፈተነውም ይህችን ምርጫ ካለፈ በኋላ መጓዝ ሲጀምር ነው፤አሁን እየረበሹ አቅመደካማን እና ሕጻናትን የሚገድሉት ባለፉት ዓመታት በታሪክ ተፈትነው ላይመለሱ የወደቁትና ከብላሎች ናቸው፤የእርሱ ሚዛን ገና አልመጣም፤ጅሎቹ በሌለ ነገር ላይ እርሱን የሚጠልዙት።ስለዚህም እካይስት ፖለቲከኞች ናቸው እንደ “አንድስ” ወዲ አድሃኖም፤ልበ-ይሁዳ።