>

ዛሬም  ፍትህ ተደፈጠጠች:-  አገር የከዱት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም  በዋስ ተለቀቁ...!!! ሄቨን ዮሀንስ

ዛሬም   ፍትህ ተደፈጠጠች:- አገር የከዱት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም  በዋስ ተለቀቁ…!!!

ሄቨን ዮሀንስ
*… የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዋስ ተለቀቁ፡፡
*… እንዲሁም ጉዳያቸውን በፍ/ቤት ሲከታተሉ የነበሩት የትግራይ ክልል የቀድሞው ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት በዋስ ከእስር እንዲወጡ ተወስኖላቸዋል።
 
*… በአንጻሩ አገሬን ህዝቤን ያሉት እነ እስክንድር (ባልደራሶች) በአሰልቺ ቀጠሮ፣ በፍትህ እጦት ይማቅቃሉ…!!!
ታከለ ኡማ አዲስ አበባን እንደ ግል ርስቱ ሲጫወትባት እነ ጀዋር መሀመድ ተከበብኩ ጋርዶቸ ሊነሱብኝ ነው እያሉ ንፁሀንን ሲያስጨፈጭፋ ድምፁን ከፍ አድርጎ የተሟገተውን እና የጮኸውን በእነ ጅዋር ጥፋት የብሄር ኮታን ለመሙላት በሚመስል መልኩ እስክንድር ነጋን አስረህ ፍርድ ቤት እያንገላታህ በሰሜን እዝ ወንድሞቻችን ላይ በውድቅት ለሊት የጨፈጨፋቸውን የህወሃት መዓከላዊ ኮሚቴ አባት  የራያ እና የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄን ስልጣኗን መከታ በማድረግ እያዳፈነች የወገኖቻችንን ስቃይ ያባባሰውን በማይካድራ የዘር ፍጅት እንዲፈፀም ያደረገው ህወሃት ቀንደኛ መሪወች ከነበሩት ውስጥ አንዷ የሆነችውን ኬሪያ ኢብራሂምን በመታወቂያ ዋስ መልቀቅ እዚች አገር ላይ የፍትህ ስርዓቱ ምን ያክል እንደወደቀ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን ሀገራችን አሁን የገባችበትን አዘቅት ቁልጭ አድርጎ የሚያመላክት አንዱ ማሳያ ነው።
በእነ አቶ ስብሀት ነጋ የክስ መዝገብ ተጠርጥረው ጉዳያቸውን በፍ/ቤት ሲከታተሉ የነበሩት የክልሉ የቀድሞው ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ወ/ሮ ሀሪቲ ምረተአብ እና በመዝገቡ 8ኛ ተጠርጣሪ አቶ ወ/ጊዮርጊስ ደስታ ዐቃቤ ህግ ለከፈትኩት የምርመራ መዝገብ የሚያስጠረጥር በቂ ማስረጃ ባለማግኘቴ በዋስ ይለቀቁ ሲል ለፍ/ቤት አመልክቷል።
በዚሁ መዝገብ ተጠርጥረው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የቆዩት አቶ ስብሀት ነጋን ጨምሮ አቶ ሰሎሞን ኪዳኔ ቅዱሳን ነጋና ሌሎች የመዝገቡ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በቀዳሚ ምርመራ እንዲታይ ዐቃቤ ህግ ለፍ/ቤቱ አመልክቷል።
ጉዳዪን የተከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቃቤ ህግ ባቀረበው መሠረት ወ/ሮ ሀሪቲ ምረተአብ እና አቶ ወ/ጊዮርጊስ ደስታ እያንዳንዳቸው በ30,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ አዟል።
አቶ ስብአት ነጋን ጨምሮ የመዝገቡ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በቀዳሚ ምርመራ መዝገብ እንዲታይና እስከዛው በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ፍ/ቤቱ ዛሬ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
Filed in: Amharic