>

የበሻሻው አራዳ ፒፕሉን በአንዴ አጀንዳ አስቀየረው አይደል?  ወንዳታ አቢቹ… ሌንጨ አባ ገዳ ...?!? (ዘመድኩን በቀለ)

የበሻሻው አራዳ ፒፕሉን በአንዴ አጀንዳ አስቀየረው አይደል?  ወንዳታ አቢቹ… ሌንጨ አባ ገዳ …?!?

ዘመድኩን በቀለ

 

… የበሻሻው አራዳ፥ ጨቅላው እና ጩጬው አፈ ቅቤ ሆደ ጩቤው ድንቁ አንቂና አናቂው አሻጋሪ መሪያችን አሁን ደግሞ በአዲስ አጀንዳ ከች ብሎልናል። ወለጋ ወለጋ ሲበዛበት አቤ ኮ ከቀጣሪዎቹም ጫናው ሲበረታበት ጊዜ የተደማሪ ተደጋፊዎቹን ሁሉ ጫጫታ ወደ ጎን ትቶ በ12 ቁጥር ሚስማርም ሶቶ ገብቶላቸው ሲያበቃ ተደማሪ ተደጋፊዎቹ ትናንት አደባባይ ውለው ደግፈውት ወደ ቤታቸው ሳይመለሱ ገና መንገድ ላይ እያሉ በአናታቸው ላይ ቀዝቃዛ በረዶ ውኃ ቸልሶ አኮማትሮ ከጎሬአቸው ወሽቆ… ሌላውን ፒፕል ደግሞ በኬሪያና በብአዴን ባንዲራ ያፋጃቸዋል። ብራቮ አቢቹ ኮ የእኔ አሸማቃቂ በደገፉህ ቁጥር እያስነጠስክ ታሸማቅቅልኛለህ አይደል? ኣ?  
 
… የበሻሻው አራዳ በኦነግ አማካኝነት በወለጋ እየፈጸመ የሚገኘውን የዐማራን ዘር ጭፍጨፋ እና በትግራይ የራሱ ወታደሮች የትግሬ ወጣቶች ላይ የፈጸሙትን የዘር ማጽዳት ጭፍጨፋ የሚያሳይ ቪድዮ መለቀቅን ተከትሎ አባው ዓይኑን በጨው ታጥቦ በፈጣጣው ደንብሮ በመምጣት ለህዝቤ አዲስ የማስቀየሻ አጀንዳ ፈጥሮ በአዲስ ሙድ ከተፍ ብሏል። አሜን ነው አሜን መንጋው አሜን ይበል አሜን ሃሌ ሃሌሉያ !! 
 
… አንደኛው የበሻሻው አራዳ አጀንዳ … እርጉዝ ናት ነፍሰጡር ተብሎ በብልፅግናዎቹ ካድሬዎች ሲወራባት የከረመችውንና በትግራይ የኤርትራ ተወላጅ ሰላዩዋ የዐቢይ አሕመድ ወዳጅ ፀረ ዐማራዋን ህወሓቲቷን ኬሪያ ኢብራሂምን ” በነፃ ” ከእስር ፈትቶ ምደረ ጎጋ ተደጋፊ ተደማሪ መንጋውን በማንጫጫት ዘና ፈታ እያለ እያለ ይገኛል። ትናንት በሀገረ አሜሪካና በሃገረ ካናዳ ዐቢይ ይምራን ሲል የዋለው ሆዳም ዐማራውና ግማሽ ግማሽ በአያት ቅድመአያቱ የኦሮሞ ስም ፈልጎ ሰሞኑን ኦሮሞ ነኝ ማለት የጀመረው አጭቤ ሁላ ኩም ብሎ እንዲቀርም አድርጓል። ጫጫታ በጫጫታ አደረጋቸው እኮ የእኔው የበሻሻው። ወንድ አቢቹ! ብራቮ ዐቢይ !! ይሄን ጎጋ ህዝብማ ጢባጢቤ ተጫወትበት። ከምር እንዳትፋታው። እናስ ምን ልትሉ ነው ነፍሰጡሯን ኬሪያን በእስር አቆይቶ አሸባሪውን እስክንድርን ይፍታልህ? ሆሆይ !! የፅንሱ አባትስ ማን እንደሆነ ይታወቃል? አዳሜና ሔዋኔ በማታውቀው ዝም ብለህ አትቀባጥር። ብራቮ ዐብይ !! 
 
… ሁለተኛው አጀንዳ … ደግሞ ባንዲራ ቅየራ ነው። በወለጋ ላይ ዐቢይ አሕመድ እና ሽመልስ አብዲሳ እየፈጸመሙ ያሉትን የዐማራን ዘር የማጥፋት ተግባር ባላሰቡት መልኩ ከእጃቸው አፈትልኮ እየወጣ ስላስቸገራቸው የበሻሻው አራዴክስ ተደናብሯል። አጭቤዎቹ በቤኒሻንጉል ክልል ዐማራን ሲያስጨፈጭፉ ከርመው ጉዳዩ ወደ እነሱ እያፈጠጠ መምጣቱን ሲያዩ ጨፍጫፊያቸው ኦነግሸኔ ብለው የዳቦ ስም ያወጡለትን ዐማራ አራጅ ሠራዊታቸውን ወደ ወለጋ ልከው የወሎ፣ የጎጃምና የጎንደር ዐማራን በገፍ እያሳረዱ መሆኑ አስበርግጓቸዋል። 
 
… እናም አቢቹ ሆዬ በወለጋ የዐማራ የአስከሬን ክምር ሲበዛበት ጊዜና የበሻሻው አራዳ የጭን ገረዱን እና አሽከር በድኑን አጅሬ ብዐዴንን ቀጭን የአጀንዳ ማስቀየሪያ መመሪያ አውርዶለታል። በድኑም ” የክልሉን ባንዲራ ቀይር” ስለተባለ ይኸው ባንዲራ መቀየር አጀንዳ ሆኖ ከች ብሏል። በድኑ ብአዴንም እንደታዘዘ ዛሬ የክልሉን ባንዲራ ለመቀየር መወሰኑን ገልጦ ዜና አሠራጭቷል። እናም በዚህ አጀንዳ የዋሑን ፒፕል በወለጋ በሚታረዱት ወገኖቹ አስከሬን ላይ ሊያስጨፍረው በዝግጅት ላይ ይገኛል። አይደለም ባንዲራ ለምን ጾታውን አይቀይርም ትላለህ እንዴ?  ደፋር። ብራቮ አቢይ፣ ብራቮ አቢቹ ! አቢቹ ይምራን !! 
 
… አንዳንዶቻችሁ ግን እረፉ። ተጠንቀቁም። በኬሪያ መፈታት የተበሳጫችሁ ሰዎች እረፉ፣ ተጠንቀቁ። የምን መቅናት ነው። ደግሞም እስክንድርን ሳይፈታ እንዴት ኬሪያን ፈታት ምናምን ትሉልኛላችሁ እንዴ? እስክንድርና ኬሪያን ታነፃፅራላችሁ እንዴ? ዋ እረፉ። 
 
… እስክንድር እኮ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆነ ግለሰብ ነው። መቀሌ ከርሞ በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያደረገ ጨፍጫፊ እኮ ነው እስክንድር ነጋ ማለት። እስክንድር ነጋ እኮ በማይካድራ በንጹሐን የዐማራ ነገዶች ላይ የዘር ፍጅት እንዲፈጸም ያደረገ፣ የወሰነ፣ ያስወሰነ ጨካኝ የጨካኝ ጨካኝ ሰው እኮ ነው። ወደ ጎንደር፣ ባሕርዳር እና አስመራ ከተሞች ሮኬት አስወንጭፎ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ አውዳሚ ፀረ ልማት ነው። የቴሌኮሙኒከሽንና የመብራት ኃይል ማሰራጫዎች እንዲወድሙ፣ በወታደሮች ላይ ሲኖትራክ እንዲነዳም ያደረገ ሞሶሎኒ እኮ ነው። እናም እስክንድር ይፈታ የምትሉ አድቡ። 
 
• እስክንድር ነጋ አሸባሪ ነው !  
• እስክንድር ነጋ አልቃይዳ ነው !   
• እስክንድር ነጋ አልሸባብ ነው !  
• እስክንድር ነጋ ጦረኛ ነው !  
• እስክንድር ነጋ ፀረ ኢትዮጵያ ነው ! 
• እስክንድር ነጋ ዐማራ ነው  !
• እስክንድር ነጋ ኦርቶዶክስ ነው ! 
• እስክንድር ነጋ የሰሜን ዕዝ ወታደሮችን በተኙበት ያስጨፈጨፈም ወንበዴ ነው ! እናም እስክንድር ነጋን፣ ስንታየሁ ቸኮልን፣ አስቴር ስዩምን መፍታት የሃገር ሉዓላዊነትን አሳልፎ እንደመሸጥ ይቆጠራል። እስክንድር ይፈታ የምትሉ አድቡ። እስክንድር ነጋ እኮ የስብሐት ነጋ ብራዘር ኖ። አድቡ  !!
 
… ደፋሮች እነ እስክንድርን የመሰሉ ፀረ ህዝብ የሆኑ አሸባርቲዎች ከኤርትራዊቷ ምርጥ የአብቹ ሰላይ ከወሮ ኬሪያ ኢብራሂም ጋር ስታወዳድሩት አታፍሩም እንዴ? ትንሽ አንኳ ቅሽሽ አይላችሁም እንዴ? አለማፈራችሁ። እደግመዋለሁ እንዲያውም ኬሪያ ኢብራሂም አምባሳደር ትደረግልን። በኦርቶዶክሳዊቷ በጣሊያን አምባሳደር በወሮ ዘነቡ ምትክ ሮም ትመደብልን !! 
 
ብራቮ አቢቹ ኮ  !!
ዐቢቹ ይምራን  !!
Filed in: Amharic