>

ብአዴን ትኩረታችንን እየተጨፈጨፉ ካሉ ወገኖቻችን ለማስቀየር ነው ይሄንን አጀንዳ በቅጥረኞቹ በኩል በሶሻል ሚዲያው እያራወጠው ያለው??? (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ብአዴን ትኩረታችንን እየተጨፈጨፉ ካሉ ወገኖቻችን ለማስቀየር ነው ይሄንን አጀንዳ በቅጥረኞቹ በኩል በሶሻል ሚዲያው እያራወጠው ያለው???
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

በእውነት አሁን አማራን የቸገረው ጉዳይ ይሄ ነው??? እኔ እኮ የሚገርመኝ እየተጨፈጨፉ ያሉና ተፈናቅለው እየተሰቃዩ ያሉ ወገኖቻችን ጉዳይ ብአዴንን ባያሳስበውና ለመፍትሔ እንዲሯሯጥ ባያደርገው እሽ የተፈጠረበትና የቆመለት ዓላማና ተልእኮው ባንዳነት ስለሆነ ነው!!!
መንጋው ግን ወገን እየተጨፈጨፈ ስለዚሁ ጉዳይ መምከር፣ መወያየት፣ አፋጣኝ መፍትሔ መተለም ሲኖርበት ከአራስ ጨቅላ እስከ ደካማ አረጋውያን ድረስ እንደበግ የታረዱ ወገኖቹን አስከሬን ከቤቱ አስቀምጦ ስለዚህ አሁን ስላልቸገረው ይጉይ ማቡካቱ አይገርምም??? አያሳዝንም???
ብአዴን ለራሱ የፈለገውን ጨርቅ መምረጥ ይችላል፡፡ ሲፈልግ ኮከብ አይደለም የጭራቅ ሥዕል ያስቀምጥበት፡፡ ፀረ አማራው የጥፋት ኃይል ብአዴን አማራን እንዳለመወከሉ ብአዴን የፈለገውን ዓይነት ጨርቅ ቢመርጥ የብአዴን ጨርቅ ፈጽሞ የአማራ ሕዝብ ሰንደቅ አይሆንም፡፡ አማራ ከአረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ ውጭ ሌላ ሰንደቅ የለውም አያስፈልገውምም!!!
ይሄ አሁን በሀገሪቱ ያለው ጠንቀኛው የጎሳ ፌዴሬሽን የአሥተዳደር ሥርዓት በጥፋት ኃይሎች ተጭኖብን እንጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈልጎ የገባበትና የመሬት ሽንሸናውም የታሪክ ሰነዶችን ጭምር መሠረት አድርጎ ትክክለኛ የመሬት ባለቤትነትን ባረጋገጠ መልኩ በትክክል ያልተሠራ በርካታ ችግሮችና ውንብድናዎች ያሉበት እንደሆነ ይታወቃል!!!
አማራ የራሱ ሰንደቅ የሚያስፈልገው ምናልባት ወደፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሄ ጠንቀኛውን የጎሳ ፌዴሬሽን “አዎ እፈልገዋለሁ!” ብሎ በነጻ ውሳኔ የወሰነ ያረጋገጠ እንደሆነና የአማራ ሕዝብም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከሰሜን እስከ ደቡብ ባሉ የሀገሪቱ ክፍሎች ያሉት ጥንታዊ ዐፅመ ርስቶቹ አንዲቷም ሳትቀር ያካተተ የአማራ ክልል የሚኖረው ከሆነ እንዲሁም የአማራ ሕዝብ “ከሀገሪቱ ሰንደቅ ሌላ አዲስ የራሴ ሰንደቅ ያስፈልገኛል!” ብሎ ከጠየቀ ብቻና ብቻ ነው!!!
ጨርቅ መያዝ ግዴታ አስመሰሉትኮ!!!
ፋይሉ ተዘግቧል!!! ትኩረት ወደ አንገብጋቢው ጉዳይ የወገን ጭፍጨፋና መፍትሔው!!!
Filed in: Amharic