>

"ነፍጠኛውና አሃዳውያን  ሊያጠፉን ነው!"  በሚል መቀስቀሻ መሪ ቃል ኦነግ፣ ኦፌኮና ኦህዴድ ድርድር ሊቀመጡ ነው...!!! (ኤርሚያስ ለገሰ)

“ነፍጠኛውና አሃዳውያን  ሊያጠፉን ነው!”  በሚል መቀስቀሻ መሪ ቃል ኦነግ፣ ኦፌኮና ኦህዴድ ድርድር ሊቀመጡ ነው…!!!

ኤርሚያስ ለገሰ

 

ኦነግ፣ ኦፌኮና ኦህዴድ በኦሮሙማ ማዕቀፍና በኢትዮጵያ የበላይነት መምጣት ውስጥ ሆነን ልዩነታችንን በውይይትና በድርድር እንፍታ በሚል እሳቤ ሽምግልና መጀመሩን መረጃዎች ደርሰውኛል። በማሸማገል ላይ ያሉት የቀድሞ የኦነግ አመራሮች እና የኦሮሞ ባለሃብቶች ” በእኛ መሻኮት ነፍጠኛውና አሃዳውያን ተነቃቅተው ሊያጠፉን ነው!” የሚል መቀስቀሻ መሪ ቃላቸው ሆኗል። በድርድሩ አገር ቤት ካሉ የኦነግና ኦፌኮ አባላት ከእስር ቤት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ማድረግን ጨምሮ በዲያስፓራ ክስ የቀረበባቸው ኦሮሙማዎች ክሳቸው እንዲነሳ፤ OMN አገር ቤት ገብቶ እንዲንቀሳቀስ ጭምር የሚያጠቃልል ነው። በሽምግልናው ላይ ኦህዴድ(የኦሮሞ ብልፅግና) ለሁለት የተከፈለ ቢሆንም የኦነግና ኦፌኮ አመራሮች በሽምግልናው ሙሉ ፍቃዳቸውን ሰጥተዋል።
የተሻለ ሀሳብ አመንጭተው ፤ በተሻለው ሀሳብ ዙሪያ ከመሰባሰብ ይልቅ የበታችነት ስሜትና ጥላቻ የመተሳሰሪያ ገመድ የሆናቸው ኦነጋውያን ዛሬም “ያጠፉናል፤ ሊያጠፉን ነው! ” አንድነት እንኳ ባይኖረን በአንድ የምንቆም እንምሰል፤ ጠላት ደስ አይበለው…በሚል ዘመኑን በማይመጥን “…አያጅቦ ይመጣብሀል …!” አይነት ማስፈራሪያ ታክሎበት ኦነግ ፣ ኦፌኮ ፣ ኦህዴድ ወደ እርቅ  ሊመጡ መሆኑ በተለይም በየጊዜው የመስዋእት በግ ሆኖ እየታረደ ላለው ፣ በህይወት የመኖር መብቱን በጠራራ ጸሀይ ለተነጠቀው  የአማራ ህዝብ ትልቅ እፎይታ ነውና ሽምግልናውን ይስምር ብለናል!!!
ምርጫ ቦርድም ” የእጩዎች ምዝገባ አልቋል” የሚለው ኦነግና ኦፌኮ ከተስማሙ ሊለወጥ እንደሚችል ሰምቻለሁ። እናም ምርጫ ቦርድ ውሳኔውን ቢገለብጥ እንዳይገርማችሁ!  ያው! ዘመኑ ” የእንስሳት እርሻም” አይደል። እንሰሶች ሁሉ እኩል ናቸው! አንዳንዶች የበለጠ እኩል ናቸው!
Filed in: Amharic