>
5:33 pm - Tuesday December 5, 6930

እንባ ያራጨው የሻለቃ ሰፈር መለሰ መልዕክት_ለዋልድባ መነኮሳት! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ

እንባ ያራጨው የሻለቃ ሰፈር መለሰ መልዕክት_ለዋልድባ መነኮሳት!
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ

 የአርማደጋው ንጉስ ፣የጠለምት ቡቃያ  ጀግናው ሻለቃ ሰፈር መለሰ  ዋልድባን ከተቆጣጠረ በኋላ መናንያኑን ሰብስቦ  አስደማሚ ንግግር አደረገ ።
በቅዱሱ ቦታ እንባ ተራጩ ።
 የዋልድባ ገዳም ሙሉ ለሙሉ ከጠላት ነፃ የወጣው በመዶሻው ፋኖ እና በነብሩ የአማራ ልዩ ሃይል ነው ።
 ይህንን ድል ተከትሎ በቅዱሱ መሬት እንሆ ፍሥሃ ደስታ ሆነ ። የምድራዊ ሰይጣን መሰሎች  ቀንበር ተሰበረ ።የዋልድባ ገዳምን አፈር ወይም እምነት  በኪሱ ይዞ የሚዞረው ፡የአርማደጋው ንጉሥ  ባለማተቡ ፋኖ አርበኛ ሻለቃ ሰፈር መለሰን  ከሚመራው ነበልባሉ ጦር ጋራ ሆኖ መናንያኑ ሲያዩት እንባቸው በዓይናቸው ቺፍፍ.… ብሎ ሞላ ።
 ሻለቃን በስስት ዐይናቸው እያዩት የደስታ የናፍቆት እንባ አፈሰሱ ፤ ገዳማውያኑ  እንዴት አያለቅሱ.? ሻለቃ ሰፈፈር  ከፈጣሪ በታች በአምላክ እርዳታ በአባቶች ፀሎት ፡ከ1981 ጀምሮ የገዳሙ ጠባቂ ነበር ።
 በዚህ ገዳም በወያኔ  ድፍረት  አንጀቱ አርሮ   ዋንድባን አትንኩ ብሎ ፡  ሽምቅ ተዋጊ ሆኖ  ብዙ ጓዶቹን እና የሥጋ ዘመዶቹን  አጥቶበታል።  ባለማተቡ (ቃሉን ጠባቂው) ሻለቃ ሰፈር መለሰ  ከወያኔ ሰራዊት ጋራ ሲዋጋ በጦርነት መሞት አይቀርምና  ፡ የጠላት ጦርን ካረገፈ በዃላ የሚፈረጥጠው ከፈረጠጠ በኋላ  በጦርነቱ የተገደሉትን አልቅሶ መልሶ በክብር ቀብሮ።
 ከኪሳቸው መታዎቂያ አውጥቶ በመቃብራቸው ላይ በድንጋይ ላይ ስማቸውን ይፅፍ ነበር ።
በዚ የትጥቅ ትግል ፡ ያለ ራዳር ያለ ዘመናዊ መሳሪያ ፡ ሄሊኮፕተር ማርኮ  ሟቹ መለስ ዜናዊ እና ስዩም መስፍንን ፀጉራቸውን ያስነጫቸው ነበር ።
 መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት አባይ ወልዱ ላይ እንዲ ሲል አምባርቆበታል ።   እንዴት አንድ የአማራ ሺፍታ ሄሊኮፕተር ይማርካል ሲል ጮሆበት ነበር ።
 በዚህም የክልሉ መንግስት አቶ ኣባይ ወልዱ  2 ብርጌድ ጦር ወደ ዳንሻ ጠለምት ልኮ ። በተለይ የብርጌዱ አዛዥ  ብርጋዴል ጀኔራል አስፍሓ መቀሌ ላይ ቤት ስጠኝ እንጂ ያንን አህያ አማራ እሬሳውን ይዤልህ እመጣለው ብሎ ፡ ፎክሮ ሄዶ።
የእነ ሻለቃ ሰፈር ጦር ተዘጋጅቶ ይጠብቃቸው ስለነበረ  ። ጦርነቱ ተጀመረ የአዛዡ  ጦር ረገፈ  በመሃል በስናይፐር እተኩሳለው ሲል ሻለቃ ሰፈር ቀድሞ  አነጣጥሮ ግንባሩን ብሎ ደፋው ።
ሬሳውንም ተለምኖ  በመቀሌ የመጣው በሽሬ እንዳ ሥላሴ ተቀበረ ።
ወደ አሁኑ ድል ስንመለስ ፡ የፋኖ መሪ ሻለቃ ሰፈር መለሰ ገዳማውያኑን ሰብስቦ  በሚመራው ጦር ታጅቦ ለገዳማውያኑ እንዲህ አለ:_
“መነኩሴ መስለህ የገባህ የወያኔ ደህንነት ካለህ አሁኑ ካለማመንታት ውጣ ከዚህ በዃላ ቀልድ የለም።” የአርማደጋው ንጉሥ ባለማተቡ ሻለቃ ቀጠለ ።
 መታወቅ ያለበት እውነተኛ መናንያን ሁኑ እንጂ የትግሬ የኦሮሞ ማንም የሚነካው የለም ።ይህ ቅዱስ ቦታ የአንድነት የፀሎት  የሃይማኖት  ቅዱስ ስፍራ ነው ።ብሔርህ አንተ ከዚያ አንተኛው ከዚ መባል የለበትም ።አባቶቻችን ሆይ ለእኛም ለሃገራችንም ፀልዩልን ። ግን አጥብቄ የምነግራችሁ ቢኖር ፡ እንኳን ኢትዮጵያዊ የሆኑ አባቶች እና እናቶች ይቅርና  ሃይማኖቱን የሚከተል ፈረንጅ እንኳን ቢመጣ  ከዚህ ገዳም አይከለከልም ። ምክንያቱም ሃይማኖት የተለዩ ብሔርም ሆነ ሃገር የላትምና።”
ሲል ለመናንያን ፣ለአባቶችና ለእናቶች መልእክቱን አስተላልፏል ።
አምላከ ዋልድባ ይጠብቅህ ብለው ፀሎት አድርገውለታል ።
ክብር ለባለ ማተቡ የፋኖ መሪ ሻለቃ ሰፈር መለሰ እና ለትግል ጓዶቹ ።
ምንጭ; አፄ ይኩኖ አምላክ
Filed in: Amharic