>
5:26 pm - Wednesday September 15, 6675

ኦሮምያን መተከልን ከአማራ የማጽዳት ዘመቻ!!!  ስደት ወደ ጎጃም ጎንደር… ወሎ ሸዋ… ስደት ደቡብ ስደት.... (ዘመድኩን በቀለ)

ኦሮምያን መተከልን ከአማራ የማጽዳት ዘመቻ!!!
 ስደት ወደ ጎጃም ጎንደር… ወሎ ሸዋ… ስደት ደቡብ ስደት….
ዘመድኩን በቀለ
” ጓ” እያሟሟቀች ነው።

… በዐማራና በኦርቶዶክስ ደም የበለጠገው እና እየበለጠገም የሚገኘው በኢትዮጵያ የኦሮሙማው አባገዳይ የዐቢይ አሕመድ መንግሥታችን የብልጥግናውን ጎዳና ” ቆሻሻ ” ነው የሚለውን የዐማራን ነገድ ዘር ከኢትዮጵያ ምድር በኋይለኛው በማጽዳት ጀምሮታል። መንግሥታችን ለጽዳቱ…  የጦር መሣሪያ፣ ካራ፣ ጩቤ፣ ሜንጫና ቢለዋ የተጠቀመ ሲሆን እሳትም በሰፊው ተጠቅሟል፣ እየተጠቀመም ይገኛል።
… ይሄ የምታዩት ስደት ከመተከል ወደ ጎጃም ነው። በእግር… በመኪናም…  በተገኘው ሁሉ ከሞት ሽሽት ዐማራው እየተጋዘ ነው። ታመው መሄድ ያቃታቸውን በሸክም እያጓጓዙ ነው። ከብት፣ እህል ፣ ንብረት ይዞ መሰደዱ የማይታሰብ ነው። መከላከያው ቆሞ ይስቃል፣ ሽመልስ አብዲሳና አሻህድሊ ሃሰን ቺርስ ይባባላሉ። ዐቢይ አህመድ ጮቤ እየረገጠ ነው።
… ደመቀ መኮንን እኔን ብቻ እንዳታስፎግሩኝ ብሎ ባላየ ባልሰማ ዐማራውን እያሳረደ ነው። ለዚህ ውለታውም ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነቱን ደርቦ እንዲይዝ፣ ሁለት ደሞዝ እንዲበላ፣ ከጎጃም ባለሃብቶች ጋር ካለው ቢዝነስ በተጨማሪ ገንዘብ ገንዘብ እንዲሆን ተደርጓል። ደመቀ ወሎዬ ነው። ከቦረና የፈለስ ኦሮሞ ወሎዬ ነው። በሰፈራ መተከል ሄዶ በዚያ የተወለደ ወሎዬ ነው የሚሉት አሉ። ለዚህ ነው ደመቀ እስላም ቢሆንም ልክ እንደ ሌሎቹ የኦሮሞ ኡስታዝ እስላሞች የዐማራ እስላሞች ሲገደሉ፣ ሲታረዱ የማይሸክከው የሚሉም አሉ።
… ኡስታዝ ደመቀ መኮንንና ኡስታዝ አህመዲን ጀበል አንድ ናቸው። ኦሮሞ የተጎዳ ሲመስላቸው ከጣሪያ በላይ ላንቃቸው እስኪቀደድ የሚጮሁ… የዐማራ እስላም በኦሮሞ ሲታረድ ትንፍሽ ያማይሉ እስላሞች ናቸው። ዐማራ ጉድህ? ሃኣ!
… ይሄ የመተከሉ ስደት ነው። ስደት ወደ ጎጃም ጎንደር… ወሎ ሸዋ… ስደት ደቡብ ይቀጥላል፣ ወደ መሃል ሃገር… ወደ ኬንያና ሱዳን… በሱዳንም የተሰደዱት በሱዳኖች እየታረዱ፣ እየተዘረፉ፣ እየተደፈሩ ነው። የጨነቀ ነገር እኮ ነው። የወለጋውን ቪድዮ ደግሞ ትንሽ ቆየት ብዬ ታዩት ትመለከቱትም ዘንድ እለቅላችኋለሁ።
… የእኔ እከደከን ማንችሎት በብልጠትም ሆነ በጉልበትዬ…  አዲስ አበባዬ ሆዬ… አንቺ ግን… ተኚ… ለጥ … ለሽም በይ … የእኔ እንቅልፋም። ኡሙንዱኖኦውኢሹ… ተኚ…
… ተናግሬአለሁ…  ለሸገሮች ለምናልባቱ…  ደብረ ብርሃንና…  ደብረ ማርቆስ ላይ ትልልቅ ድንኳኖች ከወዲሁ ቢዘጋጅ መልካም ነው።
… ቀልድ አባው… አዎ አንተ በደንብ አፊዝ… ሩቅ ነው ያልከው የወገኖችህ መከራ… ወለጋ ነው፣ መተከል ነው ያልከው መከራ ስደት ከደጃፍህ ከበራፍህ የማይደርስ መስሎህ ነው አይደል? አዎ መስሎሃል… መስሎሃል ቀልድ። አንተ አራዳ… እኔ ዘመዴ ደግሞ ፋራ፣ ሟርተኛ ነኝ ኣ?
… የወለጋዎቹንስ እሺ ከበው ነው እያረዷቸው ያሉት። ማምለጫ መሸሻ የላቸውም። የመተከሎቹም እንደምንም ጎጃም ጎንደር ይገባሉ። ከዚያ ወሎ ሸዋም ይደርሳሉ። አዲስ አበባ ግን አስባችሁታል? ነገሬን አታቅልሉት። ያውም ወደ ደብረ ማርቆስም ወደ ደብረ ብርሃንም በዙሪያህ የሰፈረው የኦሮሞ ጦር  ካሳለፈህ እኮ ነው። ሰምተሃል።
… አሁን በየኮንዲሚንየሙ እየዞሩ ማንን ነው የምትመርጡት? የሚሏችሁ ለምን ይመስላችኋል? ሃይማኖታችሁ ኦርቶዶክስ የሆነ እና፣ ነገዳችሁ ዐማራ የሆነ አስባችሁታል? እደግመዋለሁ የወለጋው፣ የመተከሉ ስደት ብዙም ሩቅ አይደለም።
ይመቻችሁ … እኔ መቀባጠሬን አልተው… እናንተ ደግሞ “መራታው” እያላችሁ መስደባችሁን አትተዉ። በቃ እንዲህና እንዲያ እያልን እስከጊዜው ድረስ እተዛዛግን እንቀጥላለን።
የማንቂያ ደወል ይልሃል ይሄ ነው። አከተመ። 
Filed in: Amharic