የጠ/ምኒስትር አብይ እግዚአብሔር ተናገረኝ መንገድ… !!!
ፕሮፌት ዮናታን አክሊሉ በሰሞኑ ስብከቱ የእግዚያብሄር ቃል ድምፅ ሆኖ ሲያበቃ መጥቶልኛል አለ።ራእይ መጥቶልኛል አለ።ከላይ ከሰማይ። ትንቢት ተናገር ብሎኛል አለ። ትንቢቱንም ተናገረ ….<መልእክቱም የመጣልኝ ለዶ/ር አብይ ነው ይላል….በዙሪያህ የከበቡህ ግብጽ በለው….. ሱዳን በለው….ኬንያም በለው……በአገር ውስጥም…..በውጭም ዲያስፖራ….፣በአለም መንግስታትም በሁሉም አካባቢ በዚህም በዛም ማእበል ቢነሳ እኔ ግን ያስቀመትኩት አንተ ነው እንዳትፈራ….. ይላል….እግዚያብሄ…… እኔ በስልጣን ላይ ያስቀመጠኩት ማንም አይነቀንቀውም ብሏል….. አሜን በል…. ይልና ትንቢቱ ያበቃል።
በመቀጠልም መልእክቱ ላይ ያቺው የፈረደባት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትከተላለች…..”ገብርኤል ቤተክርስትያን እዚህ አዋሳ ያለው መሬት ስለያዘ ነው…. ይላል….ስለዚህ የኛ ቤቴ ክርስቲያንም (ፕሮቴስታንት ማለቱ)ነው ቤተመንግስትን መያዟ ወሳኝ ነው ይለነል።
ይሄንን ትንቢት እግዚያብሄር 2011 ወይ 2012 ወደ ፕሮፌት ዮናታን አላመጣም።በቃ የዛሬ አንድ ወር ነው ፕሮፊት ዮናታን የላከው።የዛሬ አንደ ወር ያለውን የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለመናገር ደግሞ የእግዚያብሄር ጣልቃ ገብነት አያስፈልግም። እኔም ብሆን ለፕሮፌት ዮናታን እነግረው ነበር የእግዚያብሔርን ኔት ወርክ ከሚያጨናንቅ። ምክንያቱም ይሄ ትንቢት ሳይሆን በገሀድ የሚታየው አሁን ያለው እውነት ስለሆነ ትንቢት የሚባል የዳቦ ስም አያስፈልገውም።ሌላም መንገድ ነበረው ዮናታን አዲስ አበባ በነበረበት የውጣትነት ዘመኑ አይቤክስ ፀጉር ቤት ፊትለፊት የሚያዘውትራት ቤት ነበረች እዛ ብቅ ቢል ከዚህ የተሻለ ትንቢት እኮ በተለይ ባገኘ ነበረ።አሁን እያስገረሙን ያሉት ነብዮቹ አይደሉም በሚሊዮን የሚቆጠሩት ተከታዮቹም ናቸው።ሰው መቼም ከፋብሪካ እንደተሰራ ጠርሙስ አንገት እና ሆድ ብቻ አይደለም ያለው……ሰው ከአንገቱ በላይ በተሰጠው ጭንቅላት ነው የሚለየው ሰው መሆኑን የሚረጋግጠው።ታዲያ “አመክንዮ የሚባል ነገር በጌታ በየሱስ ስም ታሰረ እንዴ? ፕሮቴስታንቶች ጋር” ይሄንን ነው እንግዲህ ፈረንጆቹ a collection deplorable የሚሉት…ዝም ብሎ የሚነዳ መንጋ…የማይጠይቅ፥የማይመረምር፥ የሰጡትን የሚቀበል ብቻ….
ፕሮፌት ዮናታን መቼም የተትረፈረ ገንዘብ ያለው ሰው ነው…እንደ ሁሉም የዘመኑ ሀዋርያና ነብዮች ሁሉ ገንዘብ የተረፋቸው ቀራጮች ናቸው…ይቺ የዮናታን የሰሞኑ እስክስታ ግን “ድጋሜ ያችን የቤተ መንግስት የአብይ አህመድ ሜድልያ አንገቱ ላይ ማድረግ የፈለገ ይመስላል.> ። እኛም እና ዶ/ር አብይን ፕሮፊት ዮናታን እምንጠይቀው ነገር አለ…ያው በነካ ትንቢትህ” እግዚያቤር ተናገረኝ …..በኦሮምያ የሚፈስ የንፁሀን ደም ፥ በትግርራይ የሚፈስ የንፁሀን ደም አስቁም ብሎሀል ብትልልን” እንዴት ክርስቶስን የመሰለ ትንቢት በሆነ…።
እግዚአብሔር ከአትላንታ እስከ ሰበታ ትንቢት እያዘነበ ነው ሰሞኑን እንመረምራለን።ጠርሙሶቹም መሞላታቸውን ቀጥለዋል።ጠርሙስ ደግሞ ሆድ እና አንገት ብቻ አለው።
ሌላው ባለ ትንቢት ደግሞ ዶ/ር ሀብታሙ ይባላል ይሄኛው ደግሞ “ጋሼ የቀለም ቀንድ ነው” ማለት ባለ ዲግሪ ፕሮፌት ነው።በዚህ ዘመን ዶ/ር እና ነብይ በዝቷል።ሁለቱንም ማእረጎች የሚሰጠው ማን እንደሆነ ባይታወቅም። እስኪ ዶ/ሩ ፕሮፌት ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ሹክ ያለውን ይንገረን እኛም እንስማ…. እንሆ ጌታ ተናገረው… እንዲህ ሲል ” እግዚያብሄር አለው በ2013 በኢትዮጵያ ውስጥ የብሄር ግጭት አይነት ይከሰታል አለኝ። ሁለተኛው ትንቢት ደግሞ ለዶ”/ር አብይ ነው።እሱን የሚጠላ መንፈስ መኖሩን አሳየኝ ይላል። ይሄ መንፈስ ከቤተመንግስት ሊያወጣው ይታገላል ።እኛ እንፀልያለን ።ነገር ግን ዶ/ር አብይ ያሸንፋል። አለኝ ሀለሉያ ።አሜን በል ይላል።ይህ ትንቢት በዶ/ሩ ላይ ያወረደው ከእግዚያብሄር በመጋቢት10 2013 አ.ም ነው።
እንግዲህ እግዚያብሄ ለዶክተሩ ፕሮፌት ሀብታሙ 2011 2012 አልነገርውም ።ለዚህ ለዚህማ እግዚያብሄርን ሳያስቸግር እኔም እራሴ በነገርኩት ነበረ።ባይሆን ዝርዝር ጉዳይ ከፈለገ አራት ኪሎ በርሀንና ሰላም ማተሚያ ቤት አጠገብ ያለው ሰብለ ቤት በረንዳ ላይ ሻይ ቢጤ ይዞ ታሪኩ ከሚባለው ጋዜጣ አዟሪ (ቅን ወዳጄ) በአንድ ብር ያገር ጋዜጣ ተከራይቶ ይሄን ሁሉ ትንቢት ሰማይ ለሰማይ ሳይንከራተት እዚሁ ሰፈራችን ባገኘው ነበር……
በኢትዮጰያ ብሄር ተኮር ጥቃት መድረስ የጀመርው ከ2011 ጀምሮ ነው። ሁለተኛው ትንቢት ደግሞ ዶ/ር አብይን የሚጠላ መንፈስ አየሁ የሚል ነው።ግን እኛ ስለምንወደው እንፀልያለን። በመሆኑም እግዚአብሔር ይቀለብሳል የሚያሽንፈው እርግጥ ነው ዶ/ር አብይ ነው ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚያብሄር ።
…….እግዚያቤርም ፈቃዱ በሰማይ መሆኑ ቀርቶ በኦሮምያ ሆነ ማለት ነው?….. በቃ አባታችን ሆይ የብልፅግንና አባል ሆነ ማለት ነው?።.
..ለመሆኑ ዶ/ር አብይ የሚያሸንፈው ከማን ጋር ተውዳድሮ ነው?… ብቻውን ነው ለምርጫ የቀረበው።ይሄ ምን ትንቢት ያስፈልገዋል፡?…..አሁን አያያዙ ሲታይ ያለምንም ጥርጥር አሽናፊው ዶ/ር አብይ ነው በመሆኑም ትንቢት ላርገው ነው? ያው ጠርሙሶቹ መሞላት ስላለባቸው?። አዎ ዶ/ር አብይ እንደሚሽንፍ ካውቅንኮ ሁለት አመት ሆነነን። ይህን ለማወቅ የሮኬት ሳይንስ ተመራማሪ መሆንም አይጠበቅም ነብይም ይሁን ፕሮፊት መሆንም አይጠበቅም። ቀን በቀን እለት በእለት የምንኖረው ህይወት ነው……. ቀን በቀን የምንኖረው ህይውት መካነየሱሥ ወይም አንዱ የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን ደጅ ሲደርስ “ትንቢት” ይሆናል ማለት ነው፧? ? አሜን….ሀለሉያ….!ሄሎ።
እስራኤል ዳንሳ ደግሞ “እኔ የማውቀው ብሎ ይጀምራል….እኔ የማውቀው ዶ/ር አብይ ነው አለ።ደግሞ እግዛቤር ነብይ አደርጋለሁ አለ።ደግሞ አለ እግዛብሄ አለ እድሜ ሊክ ሾሜዋለሁ አለ።ደግሞ አንድ ቦታም አይደለም አለ በተለያየ ቦታ ይሄዳል በህይወቱ በዛ አይደለም የሾምኩት አለ…አለ..በዙራው እናት አና አባቶች የምፀልዩ አዘጋጅቻለሁ አለኝ ….የምይታውቁ ሰዎችን አደራጅቻለታሁ አለ ..። (ምን የሚያደርጉ?)
ይዲድያ የሚባለው ደግሞ።በአለም ዙሪያ ላላችሁ ብሎ ትንቢት ነው ብሎ ሲያበቃ ምስጠንቀቂያ ያስተላልፋል።”እኚሕ ጠቅላይ ሚኒስትር ህዝብ አይደለም የመረጣቸው የመረጣቸው እግዚያብሄር ነው። ልክ እንደዳዊት የሾማቸው ልክ እንደ ዳዊት የቀባቸው ይለናል…ታያላችሁ አለ በመቀጠል…. እግዚያብሄር በሳቸው አልፎ ለአይምሮ የሚገርም እጅ በአፍ የሚይሳጭን ስራ እሰራለሁ አለ። ታያላችሁ አለ ይለናል።በዚህም ምርጫ አብይ ያሽንፋል በቀጣዩ…..ከዛም በቀጣዩም ….እስከውዲያኛው…..”ይላል።( ኩን ካነረቲ ዋቀዮን ገዳ ታሄ ጀቹ….?”)
አንደኛው ደግም የናይጀርያ ቡዳ በልቶት ነው መሰለኝ ብራዘር እያለ ነው የሚሰብከው” በመቶ አመት አንድ ግዜ የሚሆነው ። በመቶ አመት አንድ ጊዜ የምትከሰት ናት አለኝ።ስድባችን ሳይርቅ እግዚያቤር ቤተመንግስቱን ተቆጣጠረው ይላል “እግዚያብሄር የአህመድ አሊ ልጅ ያ እንኳ በሻሻ ተውልዶ በሰባት አምቱ፥
ንጉስ ትሆናለህ ያለችው እናቱ፥
እንግዲህ አራት ኪሎ ምንይሊክ ቤተ መንግስትን የተቆጣጠረው እግዚያብሄር ……..ትላንት ሰልባጅ መጤነህ ተብለህ በተነገረህ ምድር ላይ መሪ ሆነህ መውጣት ይቻልሀል እንዴ ? ሲል ይጠይቃል ?ከእግዚያብሄር በቀጥታ የተላከው መልእክት … ይጠይቃል ግራ የገባው እግዚያብሄር….ነገር ግን ዘንዶ ሆነህ ራስህን ልትበላ ትዘጋጃለህ እንዴ? የሚያምነው ” “ፕሮስፔሪቲ “ነው እያልክ? ብራዘር አጊነስት ሂም…… ትሰራለህ እንዴ ?….አንታይ ክራይስት ነህ ይላል።
ይሄንን ትንቢት እግዚያብሄር 2011 ወይ 2012 ወደ ፕሮፌት ዮናታን አላመጣም።በቃ የዛሬ አንድ ወር ነው ፕሮፊት ዮናታን የላከው።የዛሬ አንደ ወር ያለውን የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለመናገር ደግሞ የእግዚያብሄር ጣልቃ ገብነት አያስፈልግም። እኔም ብሆን ለፕሮፌት ዮናታን እነግረው ነበር የእግዚያብሔርን ኔት ወርክ ከሚያጨናንቅ። ምክንያቱም ይሄ ትንቢት ሳይሆን በገሀድ የሚታየው አሁን ያለው እውነት ስለሆነ ትንቢት የሚባል የዳቦ ስም አያስፈልገውም።ሌላም መንገድ ነበረው ዮናታን አዲስ አበባ በነበረበት የውጣትነት ዘመኑ አይቤክስ ፀጉር ቤት ፊትለፊት የሚያዘውትራት ቤት ነበረች እዛ ብቅ ቢል ከዚህ የተሻለ ትንቢት እኮ በተለይ ባገኘ ነበረ።አሁን እያስገረሙን ያሉት ነብዮቹ አይደሉም በሚሊዮን የሚቆጠሩት ተከታዮቹም ናቸው።ሰው መቼም ከፋብሪካ እንደተሰራ ጠርሙስ አንገት እና ሆድ ብቻ አይደለም ያለው……ሰው ከአንገቱ በላይ በተሰጠው ጭንቅላት ነው የሚለየው ሰው መሆኑን የሚረጋግጠው።ታዲያ “አመክንዮ የሚባል ነገር በጌታ በየሱስ ስም ታሰረ እንዴ? ፕሮቴስታንቶች ጋር” ይሄንን ነው እንግዲህ ፈረንጆቹ a collection deplorable የሚሉት…ዝም ብሎ የሚነዳ መንጋ…የማይጠይቅ፥የማይመረምር፥ የሰጡትን የሚቀበል ብቻ….
ፕሮፌት ዮናታን መቼም የተትረፈረ ገንዘብ ያለው ሰው ነው…እንደ ሁሉም የዘመኑ ሀዋርያና ነብዮች ሁሉ ገንዘብ የተረፋቸው ቀራጮች ናቸው…ይቺ የዮናታን የሰሞኑ እስክስታ ግን “ድጋሜ ያችን የቤተ መንግስት የአብይ አህመድ ሜድልያ አንገቱ ላይ ማድረግ የፈለገ ይመስላል.> ። እኛም እና ዶ/ር አብይን ፕሮፊት ዮናታን እምንጠይቀው ነገር አለ…ያው በነካ ትንቢትህ” እግዚያቤር ተናገረኝ …..በኦሮምያ የሚፈስ የንፁሀን ደም ፥ በትግርራይ የሚፈስ የንፁሀን ደም አስቁም ብሎሀል ብትልልን” እንዴት ክርስቶስን የመሰለ ትንቢት በሆነ…።
እግዚአብሔር ከአትላንታ እስከ ሰበታ ትንቢት እያዘነበ ነው ሰሞኑን እንመረምራለን።ጠርሙሶቹም መሞላታቸውን ቀጥለዋል።ጠርሙስ ደግሞ ሆድ እና አንገት ብቻ አለው።
እንግዲህ እግዚያብሄ ለዶክተሩ ፕሮፌት ሀብታሙ 2011 2012 አልነገርውም ።ለዚህ ለዚህማ እግዚያብሄርን ሳያስቸግር እኔም እራሴ በነገርኩት ነበረ።ባይሆን ዝርዝር ጉዳይ ከፈለገ አራት ኪሎ በርሀንና ሰላም ማተሚያ ቤት አጠገብ ያለው ሰብለ ቤት በረንዳ ላይ ሻይ ቢጤ ይዞ ታሪኩ ከሚባለው ጋዜጣ አዟሪ (ቅን ወዳጄ) በአንድ ብር ያገር ጋዜጣ ተከራይቶ ይሄን ሁሉ ትንቢት ሰማይ ለሰማይ ሳይንከራተት እዚሁ ሰፈራችን ባገኘው ነበር……
በኢትዮጰያ ብሄር ተኮር ጥቃት መድረስ የጀመርው ከ2011 ጀምሮ ነው። ሁለተኛው ትንቢት ደግሞ ዶ/ር አብይን የሚጠላ መንፈስ አየሁ የሚል ነው።ግን እኛ ስለምንወደው እንፀልያለን። በመሆኑም እግዚአብሔር ይቀለብሳል የሚያሽንፈው እርግጥ ነው ዶ/ር አብይ ነው ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚያብሄር ።
…….እግዚያቤርም ፈቃዱ በሰማይ መሆኑ ቀርቶ በኦሮምያ ሆነ ማለት ነው?….. በቃ አባታችን ሆይ የብልፅግንና አባል ሆነ ማለት ነው?።.
..ለመሆኑ ዶ/ር አብይ የሚያሸንፈው ከማን ጋር ተውዳድሮ ነው?… ብቻውን ነው ለምርጫ የቀረበው።ይሄ ምን ትንቢት ያስፈልገዋል፡?…..አሁን አያያዙ ሲታይ ያለምንም ጥርጥር አሽናፊው ዶ/ር አብይ ነው በመሆኑም ትንቢት ላርገው ነው? ያው ጠርሙሶቹ መሞላት ስላለባቸው?። አዎ ዶ/ር አብይ እንደሚሽንፍ ካውቅንኮ ሁለት አመት ሆነነን። ይህን ለማወቅ የሮኬት ሳይንስ ተመራማሪ መሆንም አይጠበቅም ነብይም ይሁን ፕሮፊት መሆንም አይጠበቅም። ቀን በቀን እለት በእለት የምንኖረው ህይወት ነው……. ቀን በቀን የምንኖረው ህይውት መካነየሱሥ ወይም አንዱ የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን ደጅ ሲደርስ “ትንቢት” ይሆናል ማለት ነው፧? ? አሜን….ሀለሉያ….!ሄሎ።
እስራኤል ዳንሳ ደግሞ “እኔ የማውቀው ብሎ ይጀምራል….እኔ የማውቀው ዶ/ር አብይ ነው አለ።ደግሞ እግዛቤር ነብይ አደርጋለሁ አለ።ደግሞ አለ እግዛብሄ አለ እድሜ ሊክ ሾሜዋለሁ አለ።ደግሞ አንድ ቦታም አይደለም አለ በተለያየ ቦታ ይሄዳል በህይወቱ በዛ አይደለም የሾምኩት አለ…አለ..በዙራው እናት አና አባቶች የምፀልዩ አዘጋጅቻለሁ አለኝ ….የምይታውቁ ሰዎችን አደራጅቻለታሁ አለ ..። (ምን የሚያደርጉ?)
ይዲድያ የሚባለው ደግሞ።በአለም ዙሪያ ላላችሁ ብሎ ትንቢት ነው ብሎ ሲያበቃ ምስጠንቀቂያ ያስተላልፋል።”እኚሕ ጠቅላይ ሚኒስትር ህዝብ አይደለም የመረጣቸው የመረጣቸው እግዚያብሄር ነው። ልክ እንደዳዊት የሾማቸው ልክ እንደ ዳዊት የቀባቸው ይለናል…ታያላችሁ አለ በመቀጠል…. እግዚያብሄር በሳቸው አልፎ ለአይምሮ የሚገርም እጅ በአፍ የሚይሳጭን ስራ እሰራለሁ አለ። ታያላችሁ አለ ይለናል።በዚህም ምርጫ አብይ ያሽንፋል በቀጣዩ…..ከዛም በቀጣዩም ….እስከውዲያኛው…..”ይላል።( ኩን ካነረቲ ዋቀዮን ገዳ ታሄ ጀቹ….?”)
አንደኛው ደግም የናይጀርያ ቡዳ በልቶት ነው መሰለኝ ብራዘር እያለ ነው የሚሰብከው” በመቶ አመት አንድ ግዜ የሚሆነው ። በመቶ አመት አንድ ጊዜ የምትከሰት ናት አለኝ።ስድባችን ሳይርቅ እግዚያቤር ቤተመንግስቱን ተቆጣጠረው ይላል “እግዚያብሄር የአህመድ አሊ ልጅ ያ እንኳ በሻሻ ተውልዶ በሰባት አምቱ፥
ንጉስ ትሆናለህ ያለችው እናቱ፥
እንግዲህ አራት ኪሎ ምንይሊክ ቤተ መንግስትን የተቆጣጠረው እግዚያብሄር ……..ትላንት ሰልባጅ መጤነህ ተብለህ በተነገረህ ምድር ላይ መሪ ሆነህ መውጣት ይቻልሀል እንዴ ? ሲል ይጠይቃል ?ከእግዚያብሄር በቀጥታ የተላከው መልእክት … ይጠይቃል ግራ የገባው እግዚያብሄር….ነገር ግን ዘንዶ ሆነህ ራስህን ልትበላ ትዘጋጃለህ እንዴ? የሚያምነው ” “ፕሮስፔሪቲ “ነው እያልክ? ብራዘር አጊነስት ሂም…… ትሰራለህ እንዴ ?….አንታይ ክራይስት ነህ ይላል።
እንግዲህ ሲጀምር እግዚያብሄር ሹክ ያለው….. ትንቢት ነበር መጨረሻው ደግሞ ፍርድ ሆነ……. ይሄን ለማለት ፕሮፌት ወይም ነብይ መሆን አያስፈልግምኮ እነ ጫልቱ አረቄ ቤት ብቅ ብትል ኢብሳ እና ቶሎሳ በየቀኑ የሚያወሩት ይሄንኑ ነው ። ይሄ እግዚያቤሄር የፕሮቴስታንቱ ለመቶ ፕሮፌቶች እና ነብይዮች መቶ የተለያየ ትንቢት እንዴት ላከ? ምንጩ አንድ አይደለም እንዴ?
*
10 (Matthew 21)
“12፤ ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና፡—
13፤ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል፥ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት፡ አላቸው።
****
ጥቅስ አላቸው፦ ሲሰርቁም ጥቅስ አላቸው፥ስዋሹም ጥቅስ አላቸው።ለሁሉም መተላለፍ ጥቅስ አላቸው።

ምንጭ: ወንጭፍ