የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ምጥ…!!!
ሸንቁጥ አየለ
ብሬ ህዝብ እያለቀ “ለዉጥ እንዳታደናቅፉ ዝም በሉ” ሲል ከረመ:: ለብሬ የህዝብ ህይወት ምንም ነዉና በሚያልቅ ህዝብ ደም ከአቢይ ጋር ተወዳጀበት:: አሁንስ? አሁን ታሪክ ተለወጠ:: በአቢይ ትዛዝ ምርጫ በኦሮሚያ መወዳደር እንደማይችል ብሬ አሁን በደንብ ገብቶታል ተረድቶታል::
ሶስት አመት ተኩል ለመናገር ያልደፈረዉን እዉነት ለመናገር ተገዷል::የአቢይን ወንጀል ለመናገር ተገዷል::
————
ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የአቢይን ወንጀል ለመናገር ሶስት አመት ተኩል የወሰደ ምጥ አማጣ::አሁን ግን አፈረጠዉ::እናም ብሬ በሶስተኛ አመት አጋማሹ ላይ የአቢይን ወንጀል ለመናገር መድፈር ጀምሯል::ከስድስት ወር ብኋላስ? ብርሃኑ ነጋ የት ይቆሟል?
—–
ብሬ አሁን አምጦ አምጦ አምጦ እዉነቷን ፍርጥ አደረጋት::በኦሮሚያ የሚከናወነዉን ቀዉስ ሁሉ አቢይ እራሱ እየፈጠረዉ እንደሚገኝ ፍርጥ አድርጎታል::
በኦሮሚያ ክልል የሚፈጠረዉ ምስቅልቅል እና ቀዉስ ሁሉ በራሳቸዉ በኦህዴድ/ኦነጎች መሆኑን ተናገራት በዋናነትም በአቢይ አቀናባሪነት እንደሚፈጸም መናገር ጀምሯል::
ህዝብ እየታረድ:እየተፈናቀለ ብሬ ምን ይል ነበር? “ግዴለም ምንም አይደለ::ይሄ በሽግግር ወቅት የሚያጋጥም ነዉ” ይል ነበር:: “አቢይ ሁሉንም ወንጀል ቢሰራም አቢይ አሻጋሪያችን ነዉ”::
አሁን ምርጫዉ ሲደርስ ግን ብሬ “በኦሮሚያ የሚፈጠረዉ ቀዉስ ሁሉ በራሱ በአቢይ መንግስት እየተፈጠረ ያለ ጸሀይ የሞቀዉ ሀቅ መሆኑን ተናገረ::
በድፈረትም “የኦሮሚያ ብልጽግናዎች ምንድን ነዉ የሚያስፈራችሁ?” የሚል ጥያቄ አቅርቦላቸዋል::
ኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን የሚያስፈራቸዉ የስልጣን ነገር መሆኑን ብሬን ጠፍቶት ነዉ ወይስ እንዴዉ ጥቂት ብደልላቸዉ እና ባግባባቸዉ ኦሮሚያ ዉስጥ ገብቼ እንድወዳደር ይፈቅዱልን ይሆናል ብሎ አስቦ?
———-
ለማንኛዉም የወንጀሉ ምንጭ ሁሉ አቢይ መሆኑን ብሬ መናገር በመጀመሩ “ብራቮ ብሬ” ልንለዉ እና ልናጀግነዉ ይገባል::
————
የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ምጥ በጣም የረዘመ ስቃይን በዉስጡ እንደፈጠረበት መገመት ይቻላል::ዶ/ር ብርሃኑ ታሪክህን አድሰህ የትግል ጉዞህን ብትቋጭ ይሻልሃል ብለዉ የሚመክሩት ብዙዎች ናቸዉ::
——–
ከኦነግ ጋር የረከሰ ጋብቻ ፈጥረህ ሀገራዊ ንቅናቄ የፈጠርህ ጊዜ የፖለቲካ ሞት ሞተሃል::ግን አልከሰምክም ነበር::ሁለተኛም ኦህዴድ/ኦነግን ደግፈህ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ እያለቀ :እየተፈናቀለ:ህዝብ ቤቱ በላዩ ላይ እየፈረሰበት ይሄ ሁሉ ወንጀል በአቢይ ቀትተኛ ትዛዝ እንደሚሰራ እያወቅህ ሆን ብለህ “የኢትዮጵያን ህዝብ ክደህ: ለዉጡ እዳይቀለበስ እያልክ በለዉጥ ወቅት ያጋጥማል” እያልክ ህሊናህን ሸጠህ ነበር::
እስክንድር በእዉነት ፊት ሲቆም አንተ በሸፍጥ አምባ ተሰልፈህ እስክንድርን በአክራሪነት ከሰሃል::
ግዴለም ይሄን ሁሉ እንለፈዉ::መቼም ማልጎደኒ ይላል ያገር ሰዉ አይደል::እናም አሁን ዶ/ር ብርሃኑ የጀመረዉን ምጥ ትርክት እንቀጥል::
–
አሁን ግን ምጥህ እየገፋ የመጣ ይመስላል::እናም እዉነት በመጨረሻ ቀስፋ ይዛሃለች::በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ እጅህን ለማሳረፍ የተራመድክበት ረዥም ጉዞ ሁሉ የሚደመደመዉ በእዉነት የትግል መርህ ላይ በመቆም ቢሆን ላንተም ሆነ ካንተ ጋር አብረዉ ለታገሉ ክብር ነዉ::
ምጥህ በምርጫ ፓርላማ እስከ መግባት ባለዉ ስሌት ላይ አይቁም::
ኢትዮጵያ ዉስጥ እዉነት እና መርህ እስኪሰፍን በሚኖረዉ ቅኝት ብሎም ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ የህዝቧ ዬኩልነት ሀገር እስከሚሆን ድረስ በሞኖረዉ መርህ ላይ ይቁም::
–
እናም የጀመርከዉን እዉነት የመናገር ምጥ ኑረዉ::በኦሮሚያ ዉስጥ ለሚደረገዉ የቀዉስ እና የግጭት ፖለቲካ ብሎም ዜጎች የመጨፍጨፍ እና የማፈናቀል ወንጀል ሁሉ የድርጊቱ ተዋናይ አቢይ እና የአቢይ መንግስት መሆኑን አዉጀህ እንደ ጀግና ቁም::
እናም ብሬ በሶስተኛ አመት አጋማሹ ላይ የአቢይን ወንጀል ለመናገር መድፈር ጀምሯል::
ከስድስት ወር ብኋላስ? ብርሃኑ ነጋ የት ይቆሟል? የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ምጥስ ሽሉ ይገፋል ወይስ ይሟሽሻል? የምናዬዉ ይሆናል::
ሽል ከሆነ ይገፋል::ወሽ ከሆነ ይጠፋል እንዲሉ አበዉ !
ያልተመለሰዉ ጥያቄ ???
በሚጨፈጨፍ የህዝብ ደም ከአቢይ ጋር የተወዳጀ: በምርጫ ሂደት ግን የአቢይን ወንጀል ያጋለጠ ተብሎ በታሪክም ለመመዝገብ ብሬ እስከ መጨረሻዉ ገፍቶ የአቢይን ወንጀል ዝክዝክ አድርጎ ለአለም ህዝብ የማቅረብ ግዴታ ከፊቱ ተደቅኗል::የብሬ ምጥ አሁንም ቀጥሏል::ከአሁን ብኋላስ ? ከ እዉነት ጋር እስከ መጨረሻዉ ይቆማል? ወይስ አገም ጠቀም እያደረገ ይቀጥላ?