የእጅ አዙር ጦርነት…!!!
ሙሉአለም ገ/መድህን
ጦርነት በአይነትና በይዘት ደረጃ ሁልጊዜም ይለወጣል። ይህ ከማህበረሰብና ከኢኮኖሚ ፍላጎት ዕድገት፣ ከፖለቲካ እና እምነት ነክ የአስተሳሰብ ለውጦች ጋር ተያይዞ የሚመጣ ነገር ነው። የጋራ ራዕይና ግብ የሌላቸው፣ እርስ በርስ የሚፎካከሩ ወደረኞች አንዱ ሌላኛውን ለማዳከም አልፎም ለማጥፋት አዳዲስ የውጊያ ስልቶችን ይማራሉ እንዲሁም ይላመዳሉ፤ በተመሳሳይ እንዲሁ ማድረግ (በጨዋታው ሕግ መጓዝ) ያልቻለ ቡድን መሸነፍና ውድቀት ዕጣው ይሆናል።
ዛሬ በመላ ዓለም የሚካሄደው ጦርነት ካለፉት መቶ ዓመታት ውስጥ ከማንኛውም ጊዜ በተሻለ እና በፍጥነት የይዘትና የአይነት ለውጥ የታየበት ነው፡፡ ዓለም ጦርነትን በተመለከተ ፈጣን ለውጥ ብቻ አይደለም ያጋጠማት፥ ጦርነት እንዴት እንደሚካሄድ ፣ ማን እንደሚዋጋ እና ምን እንደሚዋጋ ስር ነቀል ለውጦች ታይተዋል፡፡ ዛሬ በአለም ዙሪያ የመንግስት ወታደሮች መንግስታዊ ካልሆኑ ተቃዋሚዎች ጋር ሲዋጉ ይታያሉ (Nowadays all over the world, state militaries find themselves fighting non-state opponents.)” ይህ ነው የጨዋታው ሕግ!
እነዚህ Non-State Actors በተለያዩ ሀገራት/መንግሥታትና ቡድኖች የሚደገፉ ናቸው። ዓላማው በተቀናቃኝ ሀገራት/ቡድኖች ጠላት የተባለውን ሀገር/ቡድን እንዲያዳክሙ ነው።
***
Daesh እንደ አብነት!
~
አንድ ቀላል ምሳሌ እንመልከት፦ ራሱን Daesh (ISIS) ብሎ የሚጠራው ሰለፊ-ጀሃዲስት ቡድን በመሪው አልባግዳዲ በኩል ነግሮን እንደነበረው ዓላማው formation of a cliphate stretching in muslim world መፍጠር ሳይሆን፤ እርሱ በሚፈጥረው ቀውስ በውድቅ መንግሥታት የሚመራ አዲሱን መካከለኛው ምስራቅ የመፍጠርን ግብ ያለሙ ኃያላን ፈተው የለቀቁት ተናካሽ እብድ ውሻ ነበር። የዚህን ቡድን (ISIS) አነሳስ፣ ስርጭትና ውድቀት የተመለከቱ ጽሁፎችን ለተከታተለ ሰው፣ ከቡድኑ ጀርባ የአሜሪካና የእስራዔል የስለላ ድርጅቶች ስውር ድጋፍ እንደነበረው ይረዳል።
2014 ላይ የሶሪያን 1/3፣ የኢራቅን 40 % የሚሆን ግዛት ለመቆጣጠር የበቃው ይሄ ኃይል፤ በዓለም ታሪክ አሸባሪ መንግሥትነቱን ያወጀበትና ሕዝብ የመራበት ብቸኛ አጋጣሚ ሆኖ ይጠቃሳል። እርሱ በተቆጣጠራቸው ግዛቶች እስከ 17.7 ሚሊዮን የሚገመቱ ዜጎች ይኖሩ ነበር። በ2017 መጨረሻ በርካታ ግዛቶቹን ተነጥቆ ከዋና ቤዙ ሞሱል ሲወጣ መቼም የማትነሳዋን ኢራቅ ከጀርባው ትቶ ነው። በተመሳሳይ 2018 ላይ የሶሪያ ግዛቶቹን በአየር ድብደባና በመደበኛ ጦርነት ጨርሶ ሲነጠቅ የበሽር አላሳድን መንግሥት፥ ደማስቆን እንኳ በራሻ ወታደሮች የሚያስጠበቅ አቅመ ቢስ አድርጎት ነው። የኢራን፣ የሂዝቦላና የራሻ ወታደሮች በሽር አላሳድን ከደማስቆ መንግሥትነት ለማውጣት የሞከሩ ቢሆንም እጁ ላይ የነበሩትን (1/3) የጎላን ኮረብታዎች (Golan Heights ) በእስራኤል ከመነጠቅ አላዳኑትም። ትራምፕ የጎላን ኮረብታዎች የእስራኤል አካል መሆናቸውን በፊርማው እውቅና ሲሰጥ፣ እርሱ የሚመራት ሀገር የደህንነት ተቋም ባቋቋመው ኃይል ሶሪያ ወደፍርስራሽ መቀየሯንና አልቦ-ልዖላዊ መሆኗን ስለሚያውቅ ነው። እስራኤል ከ1967ቱ የስድስቱ ቀን ጦርነት በኋላ 2019 ላይ በሙሉ ድፍረት ቀሪውን (1/3) የጎላን ኮረብታዎች ጠቅልላ ስትይዝ የሶሪያ ጦር ፊቱን ወደ እርሷ የማዞር አንዳች አቅም እንደሌለው ሲበዛ እርግጠኛ ነበረች። የ ISIS መነሳት፣ መስፋፋትና መውደቅ የእስራኤልን ያህል የጠቀመው ሀገር የለም። የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራትን አሰላለፍ ከመቀየር ጀምሮ ውድቅ መንግሥታትን እስከመፈልፈል ደርሷል። እርስ በርሳቸው የተከፋፈሉና እጅግ ደካማ የጎረቤት ሀገራት ተፈጥረዋል። በድምር ውጤቱ እስራኤል ተጠቃሚ ሆናለች።
***
በ Non-State Actor የእጅ አዙር ጦርነት!
~
“ኦሮሚያ” ተብሎ የሚጠራውን የኢትዮጵያ ግዛት እያስተዳደረ ያለው ኃይል ራሱን እንደ ልዖላዊ ግዛት እንደሚመለከት በተደጋጋሚ አሳይቶናል። የአማራን ሕዝብ በጠላትነት ስለመፈረጁ ደግሞ ባለፉት ሦስት ዓመታት በክልሉ ውስጥ የተፈጸሙ አማራ ተኮር ፍጅቶች አስረጅ ምሳሌዎች ሆነው ይቀርባሉ። የኦነግ ታጣቂ ኃይል እንደ Non-State Actor የሚቆጠር ግን ደግሞ Regional State Sponser ጨፍጫፊ ኃይል ነው። የኦነግ ጦረኛ የተደራጀ፣ የታጠቀ፣ ስምሪት ሰጭና ተቀባይ ያለው ኃይል ሲሆን፤ ክልሉን ከሚመራው አካል ጋር የጋራ የፖለቲካ አይዲዮሎጅ፣ ዓላማና ግብ አለው። ኦነግ በተግባር የኦሮሞ ብልጽግና Paramilitary Force መሆኑን ደጋግሞ አስመስክሯል። የሚለያዩት በሚና ጨዋታ ብቻ ነው።
“ኦሮሚያ” ተብሎ በተከለለው የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ‘ሀገሬ ነው’ ብለው ሀብትና ንብረት አፍርተው የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ሲፈጸም የከረመው የዘር ማጽዳት ወንጀልም ሆነ ከኸች አምናው የቀጠለው የአማራ “ክልል” አስተዳደራዊ ግዛቶችን መውረር፣ አልፎም በንጹሃን ላይ ጥቃት ማድረስ የዘመኑ ጦርነት የጨዋታ ሕግ አካል ነው። በመግቢያችን ላይ ”state militaries find themselves fighting non-state opponents” ያልነው ፍሬ ነገር ይሰመርበት።
አሁን የአማራ ክልል መንግሥት ራሱን ያገኘው ከNon-State Actor ጋር ጦርነት ገጥሞ ነው። ዋናው ጥያቄ ይሄን ኃይል ማን አደራጅቶና አስታጥቆ ላከው የሚለው ነው? ኦነግን ጨርሶ መደምሰስ ለክልሉም ሆነ ለፌዴራሉ መንግሥት የሚያቅተው አልነበረም፤ የሚያሳካው ተልዕኮ ስላለ ነው የተተው።
ISIS ከጅምሩ ሲያቆጠቁጥ ማጥፋት ይቻል ነበር፤ ነገር ግን በሂደት የሚያሳካው ተልዕኮ ስለነበረ ሆን ተብሎ ተለቀቀ። የኦነግም ከዚህ የተለየ አይደለም። የኦነግ ተልዕኮ ግልጽ ነው፤ አማራን ማዳከም ከበባ ውስጥ በማስገባት ውጥረቱን በማባባስ አቅመ ቢስ ማድረግ ነው! በውጤቱም የኦሮሞ ፖለቲከኞች አዲስ አበባን የመጠቅለል ግብ ማሳካት!
በሸዋ በኩል የአማራው መጠቃት በተራዛሚነት ከታየ አዲስ አበባን የመዋጥ ፕሮጀክት አካል ነው። በመሪ ደረጃ “አዲስ አበባን ከበናታል” መባሉን አስታውሰን፣ ያሁኑ ጥቃት ደጀን የመበተን ውጥን ስለመሆኑ እናሰምርበታለን። በአራቱም አቅጣጫ አማራው ላይ እሳት የመለኮስ ሴራ ነው እየተፈጸመ ያለው! የትህነግ ትንፋሽ ጨርሶ እንዳይቆረጥ መደረጉ በዚህም ዋግና ጎንደር የሽምቅ ውጊያ ተጋላጭ መሆናቸው፣ በመቶሺዎች የሚቆጠሩ የመተከል ተፈናቃዮች ወደቀያቸው አለመመለሳቸው፣ አማራን በመስታውት ቤት ውስጥ የማስቀመጥ ውጥን የሆነው “የኦሮሞ ልዩ ዞን” የኦነግ ምሽግ መሆኑ፣ ከአጣየው ወረራና ጥቃት ጋር ደምረን ስንመለከተው የአዲስ አበባን ደጀን የማዳከምና የመበተን ውጥን ሆኖ እናገኘዋለን። የፋሺዝም ማሽን የሆነ አመራር ባለበት ሁኔታ የማይታሰብ ሴራ፣ የማይፈጸም ጥቃት እንደሌለ ባለፉት ሦስት ዓመታት በበቂ ሁኔታ ተምረናል።
በሌላ በኩል የአጣየው ወረራና ጥቃት የምርጫ ፖለቲካው አካል ሆኖ ይታያል። በመግቢያችን ላይ ‘ጦርነት በአይነትና በይዘት ደረጃ ሁልጊዜም ይለወጣል’ ማለታችን እያስታወስን
አማራን በNon State Actor የማስወጋቱን ግብ በስሱም ቢሆን እንፈትሸው። ክልሉን የሚመራው መንግሥት ከተሳካ የሕዝብ አመጽ እንዲነሳበት በማድረግ ክልሉን ማበጣበጥ፣ በውጤቱም በምርጫው እንዲሸነፍ ማድረግ፤ ካልሆነም አነስተኛ ድምጽ ይዞ ወደ ፓርላማ እንዲገባ በማድረግ የፖለቲካ ማይኖሪቲ ለማድረግ የታሰበ ይመስላል። የኦሮሞ ብልጽግና እመራዋለሁ በሚለው ክልል ምርጫውን % እንደሚያሸንፍ እርግጠኛ ሆኗል፤ ዋነኛ ተገዳዳሪዎቹ የምርጫ ተወዳዳሪ አይደሉምና አሁን ሙሉ ትኩረቱ ጠላት ብሎ በፈረጀው የአማራ ሕዝብና መሪ ድርጅቱ ላይ ሆኗል፤ በNon-State Actors ማስወጋቱና ማስወረሩ በተራዛሚ ግቡ አማራን ማሽመድመድና መበተንን ታሳቢ ያደረገ ነው። መዳረሻው አዲስ አበባን ያለ ብርቱ ተገዳዳሪ መጠቅለል ነው።
‘አማራን ከሰበርነው ሌላው አያቅተንም’ የሚል ነው ስሌቱ!!
እናማ እንደአማራ ከዕለትና ደራሽ መፍትሄዎች ይልቅ በዘለቄታው ማሰብ ይበጃል። በኢትዮጵያ የህልውና አጣብቂኝ ሳይታሰሩ ከሰማይ በታች ያሉ መንገዶች ሁሉ ሊፈተሹ ይገባል! የዕለት መፍትሄ ከተባለ በጨዋታው ሕግ መግባት ነው። በሀገርኛ አባባል ‘እሾህን በእሾህ ነው’
በአደባባይ ልናገር የምችለው፥ የአማራ ጉዳይ ከፓርቲ-ፖለቲካ በላይ ሆኖ በመጫዎት ኃይል ማሰባሰብ ላይ ማተኮር ይኖርበታል። ለዚህ ደግሞ ወደ ውስጥ መመልከት ሊቀድም ይገባል!!
–
ግብግቡ ከጠላት ጋር ብቻ ሳይሆን ከጊዜ ጋር ጭምር ነው!!