>
8:07 pm - Tuesday March 21, 2023

ኩሸት (ኩስየት) ያለቦታው:- ቅኔ ሳይሆን፤ውሸት ነው። (ከዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)


ኩሸት (ኩስየት) ያለቦታው:- ቅኔ ሳይሆን፤ውሸት ነው።
 
ከዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

 

            በቅድሚያ፦መተረብ የማያውቅ ሰው፣በለይም የከተማ ሰው ነኝ ብሎ የሚናገር አሊያም የሚለ*ል*፤አማርኛን ስለሚናገር ወይም ፊደል ስለቆጠረ፤በተገቢው መንገድ አጠቃቀማቸውን ያውቃል ማለት አይደለም።ለዚህ ርዕሴ መነሻ የሆነኝ”የዓብይ አህመድ ኩሸት!!”በርዕሱ ላይ እንደሰፈረው”ኩሸት(ኩስየት)የሚለው ቃል አለኣግባብ በመግባቱ  ነው።የተፃፈውን ጦማር ለማመላከት የቅኔ ሥም ብቻ መሆኑን እና እንደአስፈላጊነቱ በቅኔ ድርደራ ወቅት እንደ መስመሮቹ ተቀባይነት ያለው አንዱ መቀኛ መንገድ መሆኑን ለመግለፅ ነው።
የዚህን የቅኔ ዘርፍ አኮሻሸቱን ወይም አተራረቡን ሳይሆን የቃል አጠቃቀሙን ካላወቅንበት ሰም እና ወርቁን መፈለግ ይቅርና ሕብረ-ቃሉ የትኛው መሆኑንም አንረዳም።ለዚህም ነው ኩሸት የሚለውን ዐቢይ ቃል ያለቦታው ተጠቅመህበታል፤ መኳሸት አላወቅክበትም የሚያስብለው።
“የዓብይ አህመድ ኩሸት!!”በሚለው ጥገኛ ሐረግ ውስጥ ሆን ተብሎም ይሁን ባለማወቅ “ዓብይ አህመድ” ላይ “ዓ”መሆኑ ለምን አስፈለገ፦ኢምንት ግድፈት  ነው ቢባልም እንኳ ከዋናው ጉዳይ ሥምን ከማጠልሸት በፊት ራስንም ከጥቃቅን ግድፈቶች ማፅዳት ተገቢነቱ ዋጋ አለው።
 
መግቢያውም ተገልጿል ወደዝርዝሩ ስንመጣ ደግሞ እነዚህ የአንቀፅ አደራደሮችን አስታወሳችኋቸው፦
አንቀፅ ፩….እያለ ይቀጥላል።እናም ወደ ብልቱ እስኪ እንግባና ኩሸቱን እንመርምር። 
 
 “እኛ ከተሸነፍን ሁለቴ አናስብም! አስረክበን እንወጣለን።”
እኛ ከአሸንፍን ሁለቴ እናስባለን፤አናስረክብም አንወጣም።
 
አንቀፅ ፪ ውሸቱ ምንድነው ምንም የለም፦
ስለዚህ 
ከአንቀፅ ፪፡፩ እስከ ፪-፮ ያሉት ንዑስ አንቀጾች ተሰርዘዋል።
አንቀፅ ፫ “አንድምታው ምንድነው?”
ይህም አንቀፅ የገነፈለ ዋዌ ነው፤አለሥፍራው የሚነገር የፖለቲከኞች መሰሪ ቃል ነው።
እናም አንቀፅ ፫ ከንዑስ አንቀፅ ፫-፩ እስከ ስማ-በለው ነጋሪት ድረስ ያለው ስብከት በሙሉ በአፃፋዊ ፕሮፖጋንዳ የተጋለጠ በመሆኑ ተሽሯል።
 
ማጠቃለያ፦”እኔ እምለው እንዴት ሶስት አራት ከመሃላችሁ የመጣውን የሕልውና አደጋ በአስተውሎት ማሰብ የቻለ ይጠፋል?”ብሎ ጦማሪው ያቀረበው ተማፅኖ ጠቅላይ ምኒስቴር ዐቢይ አህመድን በነገር ደብድቡልኝ ከሆነ፤ማርያምን ያንን ጭራቅ ሠይጣናዊ ሰው ቡድን የፈረካከሰ ጀግና ምንስ ቢደረግለት፤ደግሞስ ለእኛው አይደለምሳ!!!ወይ አበሳ።
 
አንገታቸው አዙሮ ለማየት የማይችል ሰዎች በማናቸውም ቅራኔ ጉዳይ ላይ፦ምንጊዜም በሦስት ምክንያቶች ለጥፋት ይጋለጣል፤
፩ኛው/በጊዜው 
፪ኛው/በቅራኔው እና 
፫ኛው/ሁኔታውን ጠንቅቆ በአለማወቅ ነው።

ቦጊዜ ለኩሉ

በኢኮኖሚ ግንባታ 
በዶላር በብር ቢሸሸግም፤ 
በግድብ ተስፋ ለመኖር 
የሕዝቡን ሥልጣን ቢፈልግም፤ 
ዘረኝነትን የሚዋጋ 
ኢትዮጵያዊነትን የሚያነግስ፤ 
ቆየ’ኮ ከተፈጠረ 
ግልገል ወያኔን የሚያረክስ። 
ልባቸው ባልተቸነፈ 
ሕሊናቸውን ባልሸጡ፤ 
ኢትዮጵያዊነትን አንግበው 
ነፃነትን በሚያምጡ። 
እየደሙ እየሞቱ 
በትግል አሳት እየፋሙ፤ 
ባልታሰበ አቅጣጫ 
ከጉጅሌው በሚቀድሙ። 
እሳት ባሕርን ሊያሻግሩን፤ 
በልብ አፍንጫቸው አሽትተው፤ 
ግልገል ወያኔን አር አብልተው። 
ሥልጣናቸውን በአመፅ፣
በመራር ትግል ቀምተው፤ 
የገዳዮችን ኅጢያት፤
በሞት ሸለቆ ሸኝተው። 
በትዕግስት ስንጠብቅ 
የሠላምን ጫፍ ፍቅሩን፤ 
ይቅርታቸውን ነስተው 
በዐቢይ ፍቅር አሰሩን። 
ቦጊዜ ለኩሉ እያልን 
ያሳለፍነውን መከራ፤
በጌታም እንጠብቃለን 
የጠላትን ሞት ሳንፈራ።
Filed in: Amharic