>
5:31 pm - Tuesday November 12, 0622

ሰላሳ ወረዳዎች ከአዲስ አበባ ተነጥቀው ለኦሮሚያ ሊሰጡ ነው!!! (ባልደራስ)

ሰላሳ ወረዳዎች ከአዲስ አበባ ተነጥቀው ለኦሮሚያ ሊሰጡ ነው!!!
ባልደራስ



*….በእስካሁኑ ስፋቷ የቤቶች ግንባታ መድረስ የቻለው 51 ሺህ 355 ሄክታር ብቻ ነው። በመሆኑም ከተማዋ ወደ ኦሮሚያ እየተስፋፋች ነው በሚል የጋራ መኖሪያ ቤቶች ታግደዋል፤
ኦሕዴድ/ብልፅግና አዲስ አበባን ወደ 43 ሺህ ሄክታር ለማሳነስ እየሠራ ነው!!!


መንግሥታዊው የኦሮሙማ ወራሪ ሃይል አዲስ አበባን ወደ ኦሮሚያ ለመጠቅለል እያደረገው ባለው እንቅስቃሴ 3ዐ የከተማዋ ወረዳዎችን ወደ ኦሮሚያ ለማጠቃለል እየሠራ እንደሆነ መረጃዎች ይፋ ሆነዋል። ይህም ለከተማዋ ህልውና አስጊ መሆኑን ምሁራን ገልፀዋል። ‘አዲስ አበባ ትናንት እና ዛሬ’ በሚል ርዕስ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ባዘጋጀው ጥናታዊ የውይይት መድረክ ላይ የተገኙ ምሁራን እንደገለፁት አዲስ አበባን እንደ አፄ ዳዊት ከተማ በራራ ለማጥፋት የኦሮሞ ፅንፈኞች እየሰሩ ነው። በራራ በኦሮሞ ወረራ እና በግራኝ አህመድ ወረራ እንደጠፋች የገለፁት ምሁራኑ አዲስ አበባም ተመሳሳይ የህልውና ስጋት እንዳለባት አመላክተዋል።
ከተማዋ እስከ ደርግ መንግሥት ማለቂያ ድረስ 122 ሺህ ሄክታር ስፋት የነበራት ሲሆን ወያኔ/ኢሕአዴግ የ’ክልል’ አደረጃጀትን ሲያመጣ ወደ 54 ሺህ ሄክታር አሳንሷታል። በመሆኑም የገጠር ቀበሌዎቿን በሙሉ ለኦሮሚያ ሰጥታለች። በእስካሁኑ ስፋቷ የቤቶች ግንባታ መድረስ የቻለው 51 ሺህ 355 ሄክታር ብቻ ነው። በመሆኑም ከተማዋ ወደ ኦሮሚያ እየተስፋፋች ነው በሚል የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚታገዱበት እንቅስቃቀሴ መሰረተ ቢስ እንደሆነ በመድረኩ ላይ ታሪካዊ ዳሰሳ ያቀረቡት አቶ አምሀ ዳኘው ገልፀዋል።
ኦሕዴድ/ብልፅግና 30 ወረዳዎችን ለኦሮሚያ በመስጠት አዲስ አበባን ወደ 43 ሺህ ሄክታር ለማሳነስ እየተሠራ እንደሆነም ተጠቁሟል። ይህ እቅድ አብይ አህመድ ወደ ጠቅላይ ሚንስትርነት ከመምጣታቸው በፊት ጀምሮ በእሳቸው መሪነት ሲሠራበት ቆይቷል።
በዘርፉ ጥናት ያደረጉት ዶ/ር ብርሀኑ ዘለቀ በበኩላቸው በልማት ስም ከተማዋ እየጠፋች እንደሆነ ገልጸዋል።
Filed in: Amharic