>

አማራ በየቀኑ ዐቢይ አሕመድ ባስታጠቀው የኦነግ ጦር በመቶዎች እየተጨፈጨፈ ያለው ብአዴን ከሰው በታች እንደ ውሻ እንዲታይ ስላደረገው ነው!  (አቻምየለህ ታምሩ)

አማራ በየቀኑ ዐቢይ አሕመድ ባስታጠቀው የኦነግ ጦር በመቶዎች እየተጨፈጨፈ ያለው ብአዴን ከሰው በታች እንደ ውሻ እንዲታይ ስላደረገው ነው! 
አቻምየለህ ታምሩ

ከ160 በላይ  የአማራ ተወላጅነት ያላቸው ሕጻናት፣ ሴቶች፣ አቅመ ደካሞች፣ አልጋ ላይ የዋሉ ሕሙማንና  የሃይማኖት አባቶች ዐቢይ አሕመድ ባስታጠቀው የኦነግ ጦር በምዕራብ ወለጋ ዞን በባቡ ወረዳ ሰደቃ ቀበሌ ውስጥ ተጨፍጭፈው አድረዋል።  ሽመልስ አብዲሳ “አማርኛንና አማራን አጥፍተን ኦሮሞኛን በአማርኛ ላይ የበላይ በማድረግ  አማርኛ የማይነገርባትን አገር እየገነባን ነው” በማለት በአማራ ላይ እልቂትና የሞት ድግስ ካወጀ ወዲህ በተለይም በሻሸመኔ፣ በሐረርጌ፣ በዝዋይ፣ በወለጋ፣ ወዘተ በየቀኑ በመቶዎች በሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ላይ እየተካሄደ ያለው የግፍ ጭፍጨፋ የአማራ ሕዝብ በአማራነቱ የበደል ሀሞት ከተጎነጨባቸዉ ዘመናት ሁሉ በላይ እጅግ የተዋረደበትና ከሰው በታች እንደ ውሻ የታየበት ብቸኛው ጥቁር ጊዜ ነው።
የአማራ ሕዝብ ከሰው በታች እንደ ውሻ ከታየበት ጥቁር ጊዜ መውጣት የሚችለው ከሰው በታች እንደውሻ እንዲቆጠር ያደረገውን፤ በልቶ ማደርን ብቻ የሕይዎት መመሪያቸው ያደረጉ የአማራ ርግማኖችና አማራ መቃብሩን ፈንቅሎ እንዳይወጣ መቃብር ጠባቂ እንዲሆኑ የተፈጠሩ የአማራ ባንዶች ድርጅት የሆነውን ብአዴንን በቅድሚያ ሲነቅል ብቻ ነው። ብአዴን የሚባለው የአማራ ርግማን በአማራ ሕዝብ ላይ ተጭኖ እስከቀጠለ ድረስ አማራ ከሰው በታች እንደውሻ መታየቱና በየዕለቱ በመቶዎች መጨፍጨፉ ይቀጥላል።
ባጭሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ሕጻናትን፣ ሴቶችን፣ አቅመ ደካሞችን፣ አልጋ ላይ የዋሉ ሕሙማንና የሃይማኖት አባቶችን ዐቢይ አሕመድ ካስታጠቀው የኦነግ ጦር ጭፍጨፋ መታደግ የሚቻለው አማራን ከሰው በታች እንደውሻ እንዲታይ ያደረገውን ብአዴን የሚባል የአማራ ርግማን ከሰንኮፉ ደም በሚያስተፋ ቁጣና ንዴት ማስወገድ ሲቻልና አዲስና ሊቀለበስ የማይች ሕዝባዊ እምቢተኝነት መቀስቀስና ሕዝባዊ ማእበል በማስነሳት ብቻ ነው።
ኢትዮጵያ መታረጃ ቄራው የሆነችበት አማራ ብአዴን እስካለ ድረስ አማራን መታደግ እንደማይቻል ተስፋውን ቆርጦ መተማመን በመፍጠር በቃኝ ብሎ  እስካልተነሳ ድረስ በየዕለቱ የሚደርስበትን ብሔራዊ ሐዘን ሳይጨርስ አማራን ከሰው በታች እንደውሻ ቆጥረው የግፍ ሁሉ መሞከሪያ ያደረጉት ጠላቶቹ ተጨማሪ ውርደት በዕየለቱ ይዘውለት እየመጡ ሲጫወቱበት መኖራቸው አይቀሬ ነው።
Filed in: Amharic