>
5:13 pm - Thursday April 19, 8351

ያኔ ነው የፈረሰው ! (ዶ/ር ፍፁም አቻምየለህ - የህግ  አማካሪ እና ጠበቃ) 

ያኔ ነው የፈረሰው !

ዶ/ፍፁም አቻምየለህ – የህግ  አማካሪ እና ጠበቃ

ደስ ካለህ ወደ እዚህም ተፈላሰፍ፣ አብንንም ውቀስ፣
ግን የአማራውም ሆነ የትግሬው፣ የኦሮሞውም ሆነ የኮንሶው፣ የጋሞውም ሆነ የወላይታው ሰው ደም  በዘር ምክንያት ሲፈስ አትቀልድ። አትፈላሰፍ።
ምክንያቱ እኮ….አትበል።
ድሮ ስሙን እዚህ የማልጠቅሰው የአዲስ ነገሩ ጋዜጠኛ የቡራፈርዳ ግዜ “root cause ” ምናምን ብሎ ጀምሮም አልሆነለትም። ይሁዳውያን አውሮፓ ውስጥ ዘር ፍጅት ሲፈጸምባቸው አይ “ድሮ ከፓልስታይን ባይለቁ ኖሮ …” የሚሉት ዓይነት ነገር ነውና።
እንደ ሀገር ፩ም ሰው በዘር ምክንያት ሲገደል “እረ ይህን ነገር እንስቀረው!” በዘር ምክንያት ሲባረረር”እረ ይህን ነገር ትክክል አይደለም” ብለን አባራሪውን ያልቀጣን ቀን” የአሁንም ሆነ የድሮው ጠቅላይ “እነዚህ የምስራቅ ጎጃም ደን ጨፍጫፊዎች” ሲላቸው ያንን ተቀብለው ሚዲያዎች ሲሳለቁ፣አባራሪው ሽፈራው ሽጉጤ ሲሾም፣ ሽመልስ አብዱሳ “ነፍጠኛውን ሰበረነው” ሕዝብ ሲጨፈጨፍ የሻሸመኔን ከንቱባ “አርፈህንተኜ” ካለው በኃላ ስልጣኑን ይዞ ሲቀር፣ የኤርትራ ወታደሮች እንደልብ ትግራው ውስጥ ሲጋልቡ፣ በአውሮፓና በአሜሪካ የቄሮም ሆነ የወያኔ  ደጋፊዎች”አማራ ሌባ፣ አማር ቆማጣ” አያሉ ሲሳደቡ ነው እንደ ሀገር የፈረስነው።
አቁሙ ብለው ወጣቶችን  የሚገስጹ እንደ አባ ዶዮ ዓይነት ሽማግሌዎች ሲታጡ፣ ህግ አስከከባሪው  ፓሊስና ወታደር ዘር ፍጅትን አይቶ እንዳላየ ስምቶ እንዳልሰማ ሲሆን ነው ሀገር የፈረሰው።
ሀገር ያለ ወንድማማችነት ስሜት የለም።
ያለው ተራራ፣ጫካ፣ቁጥቁዋጦ፣ወንዝ፣ጅረት፣ ሸንተረር፣ጉብታ፣አምባ፣ ሜዳና የትም የማያደርስ መንገድ ነው።  መፍረስ ማለት ይህ ነው።
Filed in: Amharic