>

ዐቢይ አሕመድ ከሪፑብሊካን ጋርዱ ቀንሶ ለኦነግ ያስታጠቀው ራሽያ ሰራሽ ድራጉኖቭ አነጣጥሮ ተኳሽ ጠመንጃ (አቻምየለህ ታምሩ)

ዐቢይ አሕመድ ከሪፑብሊካን ጋርዱ ቀንሶ ለኦነግ ያስታጠቀው ራሽያ ሰራሽ ድራጉኖቭ አነጣጥሮ ተኳሽ ጠመንጃ

አቻምየለህ ታምሩ

ከቻት የምታዩት የኦነግ ወታደር የታጠቀው ከመጋዘውን የወጣ አዲስ ጠመንጃ  ድራጉኖቭ አነጣጥሮ ተኳሽ ጠመንጃ [Dragunov Sniper Rifle] የሚባል ሲሆን  ሩስያ ሰራሽና  ባለመነጽርና የረጅም ርቀት ጠመንጃ ነው። መሳሪያው እስከ አንድ ነጥብ ሁለት ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኝ ኢላማን የመምታት አቅም አለው። በመደበኛ ገበያ የአንዱ ዋጋ እስከ  አስራ አንድ ሺህ ዶላር ይሸጣል።
ይህ ድራጉኖቭ አነጣጥሮ ተኳሽ  አዲስ ጠመንጃ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው የዐቢይ አሕመድ ሪፑብሊካን ጋርዶች ተመርቀው ወታደራዊ ትርዒት ሲያሳዩ ነው። ይህ ማለት ይህ ከታች የምታዩትን የኦነግ ወታደር ጨምሮ ድራጉኖቭ አነጣጥሮ ተኳሽ ጠመንጃ የታጠቀው መላው የኦነግ ጦር የታጠቀው  ከመጋዘውን የወጣ  አዲስ ጠመንጃ ዐቢይ አሕመድ አንዱን በአስራ አንድ ሺህ የአሜሪካን ዶላር እየገዛ ሪፑብሊካን ጋርዱን ለማስታጠቅ  ከገዛው ጠመንጃ ነው ማለት ነው።
ያንን ሁሉ በቪዲዮ ያየነውን  የኦነግ ጦር  ኦነግ ለአንድ የድራጉኖቭ አነጣጥሮ ተኳሽ ጠመንጃ  አስራ አንድ ሺህ የአሜሪካን ዶላር እያወጣ ሊገዛና ሊያስታጥቀው አይችልም። የኦነግ ጦር የታጠቀው ድራጉኖቭ አነጣጥሮ ተኳሽ ጠመንጃ ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ድሀ ገበሬ በተሰበሰበው ግብር ሪፑብሊካን ጋርዱን ለማስታጠቅ በሚል ሰበብ አንዱን ጠመንጃ አስራ አንድ ሺህ የአሜሪካን ዶላር እየገዛ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ ያደረገውንና  መከላከያ መጋዘን ውስጥ እንዲከማች የተደረገውን አዲስና ዘመናዊ ጠመንጃ ነው።
ምን ይሄ ብቻ! የኦነግ ጦር የለበሰው ወጥ የሆነ ዩኒፎርም እና  መሰረታዊ የውትድር መሳሪያዎችን የሚያዝሉበት “Medical Kit”ም ወደ ትግራይ የዘመተው ሠራዊት የሌለው፤ የዐቢይ አሕመድ ሪፑብሊካን ጋርዶች ብቻ እንዲይዙት የተፈቀደው የመከላከያ መሳሪያ ነው። የአማራ ተወላጆችን ለመጨፍጨፍ የሚጓጓዙትም በኦሮምያ ፖሊስና ልዩ ኃይል ተሽከርካሪዎች ነው። ከታች የተያያዘውን የኦሮምያ ፖሊስ ፒክ አፕ ይመለከቷል።
ሲጠቃለል ይህ ሁሉ የሚያሳየን የኦነግ ጦር ራሽያ ሰራሽ ባለመነጽር የረጅም ርቀት ድራጉኖቭ አነጣጥሮ ተኳሽ ጠመንጃ እንዲታጠቅ  የተደረገው፣ ወጥ የሆነ ዩኒፎርም  የለበሰው እና መሰረታዊ የውትድርናና የመድሀኒት አቅርቦቶችን ከነ Medical Kit”ቱ የሚቀርብለት በዐቢይ አሕመድ በራሱ መሆኑን ነው! ለዚህም ነው አማራንና አማርኛን ከኦሮምያ ለማጥፋት በዐቢይ አሕመድ አዝማችነት፣ ስንቅና ትጥቅ አቅራቢነት የኦነግና የኦሮሞ ልዩ ኃይል  በአማራ ላይ እያተካሄዱት ላለው ጭፍጨፋ ዋናው ተጠያቂ የፍጅቱ ጠማቂና ስራ አስፈጻሚ የአገዛዝ ቁንጮ ዐቢይ አሕመድ ራሱ ነው የምንለው!
Filed in: Amharic