“የተረገመ ህሊና ተሸክሞ ሲረግም የሚውል አገዛዝ …!!!”
አርቲስት አበበ ባልቻ
“ደርግ ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴን ከነ 60 ሚኒስትሮች መቃብር አዉርዶ የንጉሱን 5% ስራ መስራት ሳይችል እልፍ አላፍ ዜጋ በልቶና አስበልቶ ተንኮታኮተ፡፡ ከዛ በኋላም አራት ኪሎ የከተመዉ ነዉረኛ ቡድን ከ 27 ዐመት ተነግሮ የማያልቅ ግፍና መከራ በኋላ ግዛቷንና የባህር በሯን ያስረከበች ቀፎ ሀገር አስረከበን፡፡
–
ግዜ ወንበር ላይ የሰቀለዉ የለውጥ አይሉት የነውጥ ቡድንም ካሁኑ እልፍ አራጅ መንጋ አሰማርቶ ሀገሪቷን የሰው መታረጃ ቄራ አረጋት ፡፡ ሁሉንም የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ግን ተኝተው በነቁ ቁጥር እንደ ዞትር ጸሎት የድሮውን ስርዐት መርገማቸው ነው፡፡
–
የዛን ስርዐት ሩብ ሳይሰሩ ከአለም የፖለቲካ ካርታ ላይ በእርጅና የተፋቀውን ተራ የጎሳ ዲስኩር እየለፈፉ እዚህ ቅሌት ላይ ደርሰዋል፡፡
–
በጣም የሚያሳዝነዉ ግን በዚህ ሁሉ የብልግና አገዛዝ ርሀብተኛውም፣ ስደተኛውም፣ ሟቹም ደሀውና ምስኪኑ ህዝብ መሆኑ ነው፡፡ ባለፍነው 50 ዐመታት ውስጥ የተረገመ ህሊና ተሸክሞ ሲረግም የሚውል አገዛዝ ነው የገጠመን”[አርቲስት አበበ ባልቻ]