>

የወለጋው ፍጅት ፣ የሱዳን ወረራ፤ የትግል ጦርነት፤ የጅቡቲ የይገባኛል ጥያቄ....!!! (ዘመድኩን በቀለ)

የወለጋው ፍጅት ፣ የሱዳን ወረራ፤ የትግል ጦርነት፤ የጅቡቲ የይገባኛል ጥያቄ….!!!

ዘመድኩን በቀለ

 

*…. አቢቹ ህወሓት በአየር ላይ የተበተነች ዱቄት ናት ያለውን ጄነራሉ ፉርሽ አድርጎት በትግራይ ከህወሓት ጋር በተዋጊ አውሮጵላን በጀቶችና በሂሊኮፕተር እየተጠዛጠዝን ነው ብሏል። አልተገናኝቶም….!!!
 
… በተሰጡኝ ስልኮች ወደ ምሥራቅ ወለጋ ደወልኩ። ጥይት እንደ ፈንዲሻ፣ እንደ ርጭት ይንጣጣል። “ጫካ ነው ያለነው፣ ፈጁን፣ ጨረሱን፣ አረዱን፣ የወገን ያለህ! የመንግሥት ያለህ! ኧረ ጨረሱን” የሲቃ ድምጽ። ምንም ልረዳቸው ባለመቻሌ እያዘንኩኝ የሆኑትን እየደረሰባቸው ያለውን መከራ ተረጋግተው ይገልፁልኝ ዘንድ ግድ አልኳቸው። ሲጨመቅ ዐማሮቹ የሚሉት እንዲህ ነው።
በመጀመሪያ፦ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን በሊሙ ወረዳ እና በጊዳ አያና ወረዳ ስር  ባሉ ቀበሌዎች ማለትም ጉትን፣ አርቁቢ፣ መንድር 8፣ መንደር 9 እና መንደር 10 ውስጥ በሚኖሩ ዐማሮች ላይ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ተጠባባቂ ቡድን የሆነውና በዳቦ ስሙ ኦነግሸኔ በመባል የሚጠራው የክልሉ መንግሥት አሸባሪ ቡድን በዐማሮቹ ላይ ተኩስ ይከፍታል። ዝርፊያ፣ ሰው ማረድ፣ ሴቶችንም መድፈር ይጀምራል።
በመቀጠል፦ በቀበሌው ውስጥ የሚኖሩት ዐማሮች ተሰባስበው የአቢይሸኔን የጫካ ኃይል ተከላክለው እጃቸው ላይ ባለም መሣሪያ ተዋግተው ይመልሱታል። የሞተው ሞቶ፣ የቆሰለውም ቆስሎ ዐማሮቹ ዐቢይሽሜ ሸኔን ያሸንፋሉ። መትረየስ፣ ዲሽቃ፣ ስናይፐርም ከአቢይሽመልስ ሸኔም ይማርካሉ።
ከዚያ፦ ከዚያማ ይህን ያየው የአቢይሽሜው ሸኔ ሕጋዊ ማልያ ለባሹ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ቦሊስ እያበደ፣ በወንድሞቹ ሸኔዎች ሞት እያለቀሰ፣ በኦቦሌሶዎችም መሸነፍ እየተቆጨ በእልህ ወደ ዐማሮቹ መንደር ወደ ስፍራው ያመራል። ዐማሮቹም ራሳቸውን ተከላክለው ያን ጭምብላም ሸኔ የተባለ ተለዋጭ የጫካ ክንፍ የሆነውን አቢይሸኔ ኦሮሚያ ልዩ ኃይልን ጠብጥበው፣ ጠብጥበው ስላስወጡት ሕጋዊ ማልያ ለባሹ ይበሰጫል። በሰጨ፣ በሰጨና በስጭቶ አልቀረም የሁሉንም ቀበሌ ንፁሃን ዐማሮች ወደ መጨፍጨፍ ገባ። ሲያዩት ሕጋዊ ቦሊስ ነው። አይዋጉቱ ነገር መንግሥት ነው። ዐማሮቹ ምን ያድርጉ?
… አሁን የሸሸው አቢይሽሜ ሸኔም ከሸሸበት ጫካ ወንድሞቹ በፓትሮል ስለደረሱለት ተመልሶ መጥቷል። የኦሮሚያ ልዩ ኃይልም አቢይሸኔዎቹ የወንድሞቻቸውን ደም ይበቀሉ ዘንድ ዐማሮቹን ይረሽኑም ዘንድ አሳልፈው መስጠታቸው ተነግሯል። #ምፅ_ምስኪን_ዐማራ በሰው ኃይልም፣ በመሣሪያም፣ ኦሮሞዎቹ ብልጫ ይዘዋል። መከላከያም በኦሮሞዎቹ የተሞላ ስለሆነ አያገባኝም እዚያው ተፈሳፈሱ ብሏል። ዐማሮቹም የሚደርስላቸው ስለሌለ ከመሞት፣ ከመታረድ ውጪ ሌላ አማራጭ የላቸውም። ጭፍጨፋው መንግሥታዊ ነው። ሩዋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ዐማራ ጄኖሳይድ።
… ህዝቡም ከሞት የተረፉቱ ቤታቸውንና ንብረታቸውን ጥለው ገሚሶቹ ነፍሳቸውን ለማዳን ጫካ ገብተዋል። በመንደር 10 ቀበሌ የሚገኘው ድርብ ታቦት (የባለ እግዚአብሔርና የመቤታችንን ፅላቶች) ያሉበት ቤተ ክርስቲያንም እንዳይቃጠልብን ብለው የሰጉ አባቶች ካህናትም ታቦታቱን ከመቅደሱ አውጥተው በጫካ ተደብቀው እንዳሉም ተነግሯል።
… እንግዲህ በምሥራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ ውስጥ ባሉት ቀበሌዎች እየሆነ ያለው ነገር ከላይ የነገርኳችሁን ይመስላል። ነገደ ዐማሮች በኦሮሚያ ምድር በኦሮሚያ ልዩ ኃይሎች ከትናንት ጀምሮ እየተጨፈጨፉ፣ ንብረታቸውም እየተዘረፉና እተቃጠሉ ናቸው። የእህል መጋዝናቸውን አናስነካም አናስደፍርም ያሉ ዐማሮችም የእህል መጋዝን ውስጥ ተቆልፎባቸው በእሳት እንዲቃጠሉ መደረጋቸው እየተዘገበም ነው። አስከሬን በየቦታው ተረፍርፏል። ሬሳ ማንሳትም አልተቻም ነው የሚሉት ሸሽተው ወደ ጫካ የገቡት የአካባቢው ነዋሪዎች። መንገዶች ሁሉ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ስለተዘጉ ወደየትም ማምለጥ ስለማንችል ሞታችንን ከመጠባበቅ ውጪ ሌላ አማራጭም የለንም ብለዋል በሰቀቀን ውስጥ የሚገኙት ዐማሮች።
… በትግራይ ጦርነቱ ቀጥሏል። ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳ ገብታለች። ትናንት ጀነራል ባጫ ደበሌ የሰጡት መግለጫ ከሳምንት በፊት አቢቹ ከሰጠው መግለጫ አራምባና ቆቦ ረግጧል። አቢቹ ህወሓት በአየር ላይ የተበተነች ዱቄት ናት ያለውን ጄነራሉ ፉርሽ አድርጎት በትግራይ ከህወሓት ጋር በተዋጊ አውሮጵላን በጀቶችና በሂሊኮፕተር እየተጠዛጠዝን ነው ብሏል። አልተገናኝቶም። ከሱዳን ጋር ያለውንም ጉዳይ ጄነራሉ አንስተውት ነበር። “እኛ ከሱዳን ጋር አንዋጋም፣ለመሬት ብለን ስንት ዓመት ስንዋጋ እንኖራለን? ባይሆን ወደ ፍርድቤት እንሄዳለን እንጂ” ነበር ያሉት። ይሄን የሰማችው ጂቡቲም የአዋሽ ወንዝ ይገባኛል ብላ ሄጵ ማለት ጀምራለች። ዘመነ ዐቢይ ኢትዮጵያ፣ ሚጢጢ፣ የማትፈራ፣ የማትከበር መሆኗም ታይቷል። አቢቹ በአፉ አትፈርስም የሚላት ኢትዮጵያን ፍርስርሷን ካወጣትም ቆይቷል።
… ከአማሪካ ጋር ለ5 ሰዓታት ያህል በዝግ ያወሩት አቢቹ አሕመድ በኦሮሚያና በትግራይ መንግሥታቸው እየፈጸመ ስላለው ጄኖሳይድ “ባላየ ባልሰማ እንደሚያልፉት ቃል ሳይገባለት አይቀርም ነው የሚባለው። ጠሚው ያቀፈው ሁሉ እንደሚደርቅ፣ የነካው ሁሉ እንደሚተን የሚናገሩት ተቺዎች አቢቹ ” የኤርትራ ወታደር ኢትዮጵያ አልገባም ብለው የተከራከሩትን” አምባሳደር ዲና ሙፍቲን፣ ዲን ዳንኤል ክብረትን እና አቶ ዛዲግ አብርሃን ፓርላማ ላይ ” ኤርትራ ገብታለች” በማለት ወዳጆቻቸውን በቁማቸው ገድለው ወዳጅ አሳጥተዋቸዋል።
… ጠሚው አሁን ደግሞ ከአማካሪያቸው ከአሽከራቸው ከብአዴንም ጋር በወልቃይት ጉዳይ ለመጣላት የመጀመሪያውን ተኩስ መክፈታቸው ጥይትም መተኮሳቸው ተሰምቷል። እነ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ወልቃይት ከተመለሰልን ስለ ራያና መተከል፣ ስለደራም አያገባንም ማለታቸውን ተከትሎ የተነሣው አዋራ ይታወሳል። ከመተባበር ይልቅ፣ በአንድ ዐማራ መንፈስ ከመንቀሳቀስ ይልቅ እኔ ብቻ የሚለው የራስ ወዳድነት ትግል እንደማያዋጣ ጠሚው የማንቂያ ደወል ለዐማራው ደውሏል።
«የወልቃይት ጥያቄ የውኃ፣ መንገድና የልማት ጥያቄ ነው። የወልቃይት የዐማራ ማንነት ጥያቄ ዲያስፖራዎች የሚያራግቡት አጀንዳ ነው።» እቡይ አሕመድ። ከሳምንት በፊት፣ አሜሪካ መጥታ ጆሮ ጠምዝዛ ሃሳቡን ከማስቀየሩ በፊት ግን እቡዩ አቢቹ በፓርላማ ቀርቦ ” የወልቃይትን ጉዳይ እንዴት እንዳሽሞነሞነውና የዐማራውን ልብ እንደ ቂቤ እንዳቀለጠው” የሚታወስ ነው። ውሸታም፣ የሐሰት ፈጣሪዋ ስለሆነ ግን በቃሉ አልረጋም። ተልባ ነው ጠሚዬ፣ ሙሉጭልጭ እንደ ዓሣ።
… በስተ እርጅና በዘመኑ ፍጻሜ ላይም ቢሆን ዐማራው በጥቂቱ የነቃ ይመስላል። ዳያስጶራ አማራው ገና አሁን ከእንቅልፉ መንቃቱ፣ ብትት ብንን ብሎ መነሣቱ እየታየ ነው። ሌላው ገና ይቀረዋል። መቀመጫው ላይ ሳንጃ እስኪሰካበት የሚጠብቀውም የትየለሌ ነው። በእርግጠኝነት የምናገረው ነገር ግን መከራው የእያንዳንዱን ቤት ይጎበኛል። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉም አብሮ ያለቅሳል። ይሄ ቃሌ ነው።
… ምርጫም፣ ሰላምም ያለ የሚመስለው ለጊዜው ከተሞች ላይ ብቻ ነው። ዳርዳሩ ግን የሬሳ ክምር፣ የደም ጎርፍ፣ ራብና ጠኔ፣ ሰቆቃና ዋይታም ነው።
★ ፎቶው ላይ የሚታዩት ምስኪን ዐማሮች የወሎ ዐማሮች ናቸው ተብሏል። በዚህ በረመዳን ጾም ላይ የሚገኙት የወሎ ሙስሊም ዐማሮች በአቢይሽሜ ኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከመረሸናቸው በፊት በዚህ መልኩ ይዋረዱና ነው የሚረሸኑት ተብሏል።
… እግዚአብሔር ይደረስላችሁ  !!
Filed in: Amharic