>

የኦሮሙማ ፋሺዝም ...! (መስከረም አበራ)

የኦሮሙማ ፋሺዝም …!

መስከረም አበራ

“እኛ ከሱዳን ጋር ለመሬት ብለን አንዋጋም ፣ ስንት አመት ስንዋጋ እንኖራለን…” 
ጀነራል ባጫ ደበሌ
*….ከኦሮሞ ክልል ሲሆን ለመሬት ብለው ሌሎች ብሄሮችን ገድለው አፈናቅለው መሬቱን ይወርሳሉ 
ትናንት ጀነራል ባጫ ደበሌ “እኛ ከሱዳን ጋር አንዋጋም ፣ለመሬት ብለን ስንት አመት ስንዋጋ እንኖራለን?? ባይሆን ፍርድቤት እንሄዳለን እንጅ” ያሏት ነገር ምን ማለት እንደሆነች ሊገባኝ አልቻለም። የሃገር መከላከያ ሰራዊት ዋና ስራው ሃገር ዳርድንበር ማስከበር መስሎኝ?! በዚህ አይነት ጎረቤት ሃገሮች ሁሉ በአራቱም ማዕዘን የቻሉትን ሁሉ መሬት ቢወሩና ቢይዙ መከላከያው ፋይል እየያዘ ወደ ፍርድ ቤት ሊሮጥ ነው??? ወይስ ” ኦሮምያን አትንኩ እንጂ ሌላውን እንዳሻችሁ” ሊል ይሆን???ምላሳችሁ ላይ ያለችው ኢትዮጵያስ በዚህ አካሄድ ትኖራለች? ምን ማለታችሁ ነው?????
በኦሮሙማ ፋሽዝም የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንዲህ ረክሷል !!! በፈራረሰች ሃገር ላይ ኦሮሚያ እየተገነባች መሆኑን እነ ጀነራል ባጫ ሳይቀሩ እቅጯን እየነገሩህ ነው !!!
ገና እኛ ለህዳሴ ግድብ ብለን ከግብጽና ከሱዳን ጋር አንዋጋም ብለው እቅጩን ሲነግሩህ አዳሜ የአዞ ፈገግታ እያሳየህ የምታጨበጭብላቸው ቀን ይመጣል ፣ እርግጠኛ ነኝ!!!
Filed in: Amharic