>

ሌንጮ ለታና ማሥረጃዎች...!!! [ከታሪክ ተመራማሪው አያሌው ፈንቴ ጥናት የተወሰደ ]

ሌንጮ ለታና ማሥረጃዎች…!!!

 
[ከታሪክ ተመራማሪው አያሌው ፈንቴ ጥናት የተወሰደ ]

 

ሌንጮ ለታ በነጮች አቆጣጠር በ2016 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ስቶክሆልም ከብርሀኑ ጋር በተገኘበት ስብሰባ ላይ ኦነግ ከወያኔ ጋር በሠራበት ወቅት በተለያዩ ቦታዎች በተለይ በበደኖና በአርባ ጉጉ ስለገደላቸው አማሮች ጥያቄ ሲቀርብለት የሰጠው መልስ፡- (1) በደኖ ገዥው ፓርቲ እንጅ እኛ አይደለንም፣ (2) አርባ ጉጉም ኦህዴድ እንጅ እኛ አላስተዳደርንም የሚሉ ናቸው።
 
እውነታው ግን ይህ አይደለም። ምንም እንኳን ያ ወንጀል የተፈፀመበት አካባቢ በአካባቢያዊ ክፍፍል መሠረት ለኦነግ ቢደርሰውም፣ ወያኔና ኦነግ መጀመሪያ ሥልጣን እንደያዙ በደኖም ሆነ አርባጉጉ ውስጥ ሁለቱም በወንጀሉ ውስጥ እንዳሉበት ከእነማስረጃው ስለሚቀርብ በጥሞና ለሚከታተል ሰው ግልፅ ይሆናል።
 
ለማንኛውም በቅድሚያ ሌንጮ ስለ በደኖም ሆነ ስለ አርባ ጉጉ ቃል በቃል የተናገረው ይኸውና። ቀጥሎም ማስረጃዎች ይሠፍራሉ፣ ፍርዱን ግን ለአንባቢ እተዋለሁ።
 
የሌንጮ ለታ ምላሾች!
 
– “ኦነግ ፈፀመ ተብሎ ክስ የሚቀርብባቸው ቦታዎችና ሁኔታዎች ላይ ነው የተነሳው ጥያቄው፣ ይኸ ከ20 ዓመት በላይ ሲያነታርከን የቆዬ ጉዳይ ነው። ምንጩ ምንድነው ብለን እንጠይቅ፣ ከዬት ነው የመጣው፣ ይህ አብዛኛው ውንጀላ የተሰነዘረው አሁን ሥልጣን ላይ ባለው ፓርቲ ነው። በተለይ በደኖ የመጀመሪያዋ የመንደርና የወረዳ ምርጫ ሁለት ሳምንት ሲቀረው የመጣ ጉዳይ ነው። በቴሌቪዥን ላይ ለፕሮፓጋንዳ የቀረበ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም ግልፅ ነው። ኦሮሞንና አጎራባች ብሔሮችን፣ በኦሮሞ መካከል ሰፍረው ያሉትን ብሔረሰቦች ለማጋጨት ነው። 20 ዓመት ያለፈው ነገር ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ይህንን ማጣራት እንፈልጋለን ካልን የትኛው አጥኚ ቡድን ነው ይህንን ሄዶ አጣርቶ ትክክለኛ ፍርድ ሊሰጠን የሚችለው? መደጋገሙ ግን ማንን ነው የሚጠቅመው? ያን ነው መጠየቅ ያለብን፣ ኦሮሞና ሌሎች ብሔሮች እንዲቀራረቡ ያደርጋል ይህን መደጋገሙ? እንተው!” አለ። 
 
– “አርባ ጉጉ ተፈጠረ የተባለው ኦነግ አርባጉጉን አያስተዳድርም ነበር፣ ያስተዳድር የነበረው አሁንም ሥልጣን ላይ ያለው የኦሮሞ ቡድን ነው። ኦነግ በነበርን ጊዜ ማንኛውንም ብሔር እንደጠላት ፈርጀን ለጥቃት ግልፅ እንዲሆን አድርገን አናውቅም (ተሰብሳቢው ሞቅ ያለ ጭብጨባውን አቀለጠው) ይህን የሚያደርጉትንም ኃይሎች እንቃዎም ነበር። ይህ ዓይነት ‘ቴንዴንሲ’ (‘ዝንባሌ’ ማለቱ ይመስለኛል) ያላቸውንም እንቃዎም ነበር። ብዙ ማለት ይቻላል፣ ግን ኢትዮጵያ አካባቢ የሰው ደም በቀላሉ ይፈሳል። በ97 ምርጫ አዲስ አበባ መንግሥት ራሱ ያቋቋመው አጥኚ ቡድን ባረጋገጠው ከ200 በላይ ነው የሞቱት። በግልፅ ማን ተጠያቂ እንደሆነ የሚታወቅ ነው” አለ።
 
በኦነግ ላይ የሚቀርቡ ማሥረጃዎች! 
 
(1ኛ) አባ ኒቆዲሞስ አሰፋ የተባሉት አባት በኢሳት የሰጡት ምሥክርነት ይኸውና፡-
 
“በ1983 ዓ.ም ገዥው መንግሥት ሥልጣን ተቆጣጠረ። ኦነግም መጀመሪያ ምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌን እንደተቆጣጠረ፣ የመጀመሪያ ሥራ ያደረገው በአማራ ተወላጆች እጅ የነበረን የመሣሪያ ትጥቅ ማስፈታት ነበር። ትጥቅ ፈተው መሳሪያ አሥረከቡ። አሁን ከኦነግ ጋር ተስማምተው መኖር ጀመሩ። 
 
“ነገር ግን ኦነጎች ተስማምተው ሠላማዊ መስለው ቢኖሩም፣ ሀብት ያለውን ለትግል ይፈለጋልና ገንዘብ አምጣ ከማለት አንስቶ ሕዝቡ የሰጣቸውን መሣሪያ አምነው ከተቀበሉ በኋላ እንደገና ተጨማሪ መሣሪያ ቀብረሀልና አውጣ እያሉ ይገርፉና ያሰቃዩ ስለነበር፣ በቀን ህወሀት የተወሰኑ ወታደሮች በመኪና ጭኖ መጥቶ እኔ ነኝ የማስተዳድራችሁ ብሎ (ሕዝብ እውነተኛ መንግሥት መጣልን ብሎ ሁሉም እልልታውን ያሰማል)፣ 
 
“ሕዝቡን እልል ካስባለ በኋላ ግን ተመልሶ ሐረር ከተማ ገብቶ ያድራል። ማታ ደግሞ ኦነግ መጥቶ ምን አይታችሁ ነው እልል ያላችሁት በሚል እርጉዝ እናት ሆዷ ተቀዶ ልጇ ከፊቷ ሲወድቅ በዓይኗ እንድታይ አደረገ፣ ሕዝብ እንደጎመን የተቀረደደበትና ወደ ገደል የተጣለበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው። በዚህ ዓይነት የበደኖ እልቂት ተፈፀመ።
 
“ከዚህ ከበደኖ ዕልቂት በኋላ ዘጠኝ (9) የአንጫር ወረዳ ቀበሌዎች ምዕራብ ሐረርጌና አሰኮ ወረዳ አርባ ጉጉ አውራጃ የነበሩ አማሮች፣ ትጥቅ ከፈታን እንደ በደኖዎቹ ወገኖቻችን ስለምናልቅ፣ ትክክለኛው መንግሥት እስከሚመጣ ትጥቅ አንፈታም አሉ። ይህን ተከትሎ ኦነግ ለነፍጠኞች ሥንቅና ትጥቅ ታቀብላላችሁ በሚል የሚከተሉትን ግድያዎች ፈፀመ፡-
 
“(1ኛ) ዘጠኝ ሰዎች አቶ በለው ወርቅነህን ጨምሮ በአውሰይድ ወንዝ አርዶ ጣለ፣ 
(2ኛ) በዳሮ አቦና አካባቢ ከሚጨታ ከተማ አለፍ ብሎ ከምትገኝ ቀበሌ አርባ ጉጉ የአቶ ጌታቸውን አሥራ አንድ ቤተሰብ ገደለ፣
(3ኛ) ወፊ ከተማ ራብሸዲ ቀበሌ ላይ ልጆች የነበሯቸው ሰባት ወንድማማቾችም እንዲሁ።
(4ኛ) የአቶ አቻምየለህ አሰፋ አባት አቶ አሰፋ በኦነግ ኃይሎች ቆዳቸው ተገፎ እንደ ስልቻ የወጣበትና ተሰቃይተው የሞቱበት ሁኔታ ነበር፣
(5ኛ) በአሰቦት ገዳምም 17አባቶች አልቀዋል። 
 
“የእነ ኦነግ ታሪክ የማይረሳ ነው። በዚህ ወቅት የአገር ሽማግሌዎች ተሰባስበው ለታምራት ላይኔ አቤቱታ ሲያቀርቡ ያገኙት መልስ፡- “ይኸን ነፍጠኛውን ነው የምትሉኝ? ሐረር ብሎ አማራ፣ ባሌ ብሎ አማራ፣ አርሲ ብሎ አማራ አላውቅም!” ነው ያሏቸው። ከዚህ በኋላ አቅምና ትንሽ ሀብት ያለው ሕዝብ “ለካ ይህ አገራችን አይደለም፣ ወደ ወገኖቻችን እንሂድ በሚል ተነስተው ሄዱ” አሉ። 
 
ከእነዚህ ወሰንተኛ ከሆኑት ከአንጫር ወረዳ ምዕራብ ሐረርጌ እና ከአሰኮ ወረዳ አርባጉጉ አውራጃ ጋር ኦነግ ወጊያ ገጥሞ ብዙ ወታደር አልቆበታል። እኔ እራሴ ይላሉ አባ ኒቆዲሞስ፣ የ16 እና የ17 ዓመት ወጣት ሆኜ አገልግልና ውሀ ይዤ ከአያቴ ጋር የተካፈልኩበት ጦርነት ነው። በዚህ ጦርነት በእኛ በኩል የተመታው አስፋው ደሳለኝ የሚባል አንድ ሰው ብቻ ነበር። 
 
ከእነሌንጮ ለታ ጋር አብሮ የነበረውና ታዋቂ የቅርብ ሰው የምዕራብ ሐረርጌን የኦነግ ሠራዊት የመራው ሙሀመድ በከሬ የተባለው በዚህ ጦርነት ተገሏል። በዚህ ውጊያ ኦነግ ተሸነፈ። እነኚህ አንጫርና አሰኮ ወረዳዎች ትጥቅ ሊያገኙ የቻሉበት ምክንያት 7,000 የሚሆን የደርግ ወታደር ከአሰብ፣ ከአፋር፣ ወዘተ. ካሉ ቦታዎች ቁጥጥር የሌለባቸውን መንገዶች በመከተል ወደ ናዝሬት ሲጓዝ ዘመናዊ መሣሪያውን በምግብ፣ በልብስ፣ በገንዘብ (በ50 እና 60 ብር) እየሸጠ የሲቪል ልብስ ለብሶ ወደ ዘመዶቹ ለመቀላቀል ሲሄድ ነበር። በዚህ ምክንያት በቂ ትጥቅ አገኙ። 
 
በ1984 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ግን ያንን አካባቢ እንዲቆጣጠር በኢህአዴግ መመሪያ ሰጭነት ለኦህዴድ ተሰጠ። ኦህዴድም የኦሮሞን የበላይነት፣ የአማራን የበታችነት አውጆ መጣ። የኦህዴድም መፈክር “ነፍጠኛን ገረኢታ ጂቢቱስ ጃለልቱስ ኦሮሞ ጀለጉልታ — አንተ ቦርጫም አማራ ወደድክም ጠላህም ለኦሮሞ ትገዛለህ፣ በኦሮሞ ሥር ትተዳደራለህ” ይላል።
 
ኦነግ እንዳደረገው ኦህዴድም የትጥቅ ፍቱ ጥያቄ ሲያቀርብ ተመሳሳይ መልስ አገኘ። ኦህዴድም ከገዥው ፓርቲ ጋር ሆኖ በሦስት አቅጣጫ በከባድ መሣሪያ ጦርነት ከፈተ። በተለይ ሐምሌ 15ና 16 ቀን 1984 ዓ.ም ሪቡ ቀበሌ በተደረገው ጦርነት የታወቀው ጀግና የጎበዝ አለቃ ታደሰ ተገኝ ሲገደል ትልቅ ጉዳት ነበር።
 
ያም ሆነ ይህ እስከ 1986 ዓ.ም ድረስ ይህ ሕዝብ ራሱን አሥከብሮ እየኖረ ባለበት ወቅት አረፍ ዓይኔ የተባለ ገዥውን ወክሎ ከአማሮች ጋር ተደራደረ። በድርድሩ መሠረት ከ1986 እስከ 1989 ዓ.ም ሦስት ዓመት አካባቢዎቹ በአማራው እንዲተዳደሩ ሆነ። በዚህ ጊዜ አማራው መሣሪያውን አስረከበ። ከዚያ በኋላ ቀስ በቀስ አዘናግተው የኦሮሞዎች መስተዳድር ተጀመረ። 
 
በዚህ ጊዜ በአስኮ ወረዳ 34 አማሮች ታሥረው የሞቱት ሞቱ፣ እነ ደመረው አበራም ከ15 ዓመት እሥራት በኋላ ተፈተዋል፣ የተሰደዱም ተሰደዋል፣ በአንጫሮ ወረዳም እነ ዳኜ ልጄ ወርቅ፣ እነ አቻምየለህ አሰፋ፣ እነ ደርቤ አሰፋ፣ ወዘተ. ተሰደዋል ። ኦህዴድ ቂም በቀሉን በሚገባ ተወጥቷል። ኦነግንም ኦህዴድንም እንዲፈነጩብን ያደረገ ወያኔ ነው”። 
 
. . . / ይቀጥላል
 
ጥናት አቅራቢውን አያሌው ፈንቴን ከልብ አመሠገንኩ፡፡
 
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!
Filed in: Amharic