>

ግፍን በመቃወም ቀዳሚ ጀማሪ መሆን  የአንበሳ ልብ ይጠይቃል!!! (መስከረም አበራ )

ግፍን በመቃወም ቀዳሚ ጀማሪ መሆን  የአንበሳ ልብ ይጠይቃል!!!

መስከረም አበራ 

*… አንበሶች_ክብር_ይገባችኋል…!!!
 
 
አትነሳም ወይ፤ አትነሳም ወይ
እየሞተ ያለው አማራ አይደለም ወይ?
 
አትነሳም ወይ፤ አትነሳም ወይ
አማራ እየጠፋ አይደለም ወይ?
 
አትነሳም ወይ፤ አትነሳም ወይ
የሚፈሰው ደም የአንተ አይደለም ወይ?
 
ረዥም ርቀት በአንድ እርምጃ ይጀመራል። ግፍን በመቃወም ቀዳሚ፣ጀማሪ መሆን ግን የአንበሳ ልብ ይጠይቃል። (የአንበሳ ልብ ያላቸው ጥቂቶች) የአማራ ህዝብ ሞት መሰደድ ይቁም ሲሉ  ምግብ ባለመመገብና በምስሉ ላይ በሚታየው የተቃውሞ ትዕይንት ተግባራዊ ትግላቸውን ጀምረዋል። እደግመዋለሁ ጀማሪ መሆን የአንበሳ ልብ ይጠይቃል ።
… የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ   ተማሪዎች ከረጅም ዝምታና ትእግስት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በነገዳቸው ላይ የታወጀውን መንግሥታዊ ጄኖሳይድ ተቃውመው መውጣታቸው ተሰምቷል።
በአማራ #ህዝብ ላይ  እየተካሄደ ያለውን #ጄኖሳይድ በመቃወም በአንድነት በግቢ ውስጥ ሰልፍ ከማድረጋቸው በተጨማሪ የምግብ አዳራሾችን ጥለው መውጣታቸው ታውቋል!!
… እናቱ የታረደችበት፣ አባቱ የተገደለበት፣ እህቱ በደቦ የተደፈረችበት፣ የደረሰች ነፍሰጡር ሚስቱ ሆዷ የተቀደደበት፣ ዐማራ በመሆኗ ብቻ የሴቶቹን ጽንስ አውጥተው የበሉበት፣ በሴቶቹ ማኅጸን እንጨት ከተው የተሳለቁበት፣ ንብረቱን ሃብቱን በአንድ ጀንበር አውድመው ለማኝ የእኔ ቢጤ ያደረጉት የዐማራው ልጅ “ከዚህ በላይ ምንም አይመጣም” ብለው እነሆ ዛሬ የዐቢይ አሕመድን ጨካኝ የአፓርታይድ ፋሽስት ሥርዓት ተቃውመው አደባባይ መውጣታቸው ተነግሯል።
Filed in: Amharic