>

የኅልውና ተጋድሎ እያደረገ ያለው የአማራ ሕዝብ የጋለውን ብረት ከመቀጥቀጥ ክንዱ መዛል የለበትም!  (አቻምየለህ ታምሩ)

የኅልውና ተጋድሎ እያደረገ ያለው የአማራ ሕዝብ የጋለውን ብረት ከመቀጥቀጥ ክንዱ መዛል የለበትም! 

አቻምየለህ ታምሩ

የአማራ የምንጊዜም ጠላቱ የሆነውን መለስ ዜናዊን ሕዝባዊ፣ ሰብዓዊ፣ ፍትሐዊና ሩህሩህ እንደሆነ ሲደሰኩር የነበረው፣ ኢሕአዴግ የሚባለው የማታለያ ጭንብል ሕዝባዊ ድርጅት እንደነበር ሲናገር የኖረውና ሰክሮ  ያለ መንጃ ፍቃድ ሲያሽከረክር ሰው ገጭቶ የገደለው አገኘሁ ተሻገር በትዕዛዝ የሚሰጠውን መግለጫ የአማራ ሕዝብ ከቁም ነገር መቁጠር አይገባም። ሕዝባችን እያካሄደ ያለውን ፍትሐዊ የኅልውና ተጋድሎ አጠናክሮ በመቀጠል የጎደለውን መሙላት፤ የላላውን ማጥበቅ፤ የተኙትን መቀስቅሰና የነቁትን ይዞ ወደፊት መሮጥ አለበት።
በዚህ ወቅት በነቂስ አደባባይ የወጣው የአማራ ሕዝብ እያደረገው ያለውን ተጋድሎ የሚያቆምበት አንዳች ምድራዊ ምክንያት የለውም። የአማራ ሕዝብ በማንነቱ ተለይቶ በጅምላ እንዲፈጅና የዘር ማጥፋት እንዲፈጸምበት ያደረገው መንግሥታዊ ሥርዓትና ርዕዮተ ዓለም እስካልተቀየረ ድረስ የጅምላ ፍጅቱና የዘር ማጥፋቱ በከፋ ሁኔታ የሚቀጥል እንጂ የሚቆም ባለመሆኑ የአማራ ሕዝብ እያካሄደ ያለውን ተጋድሎ ከፍ በማድረግ የጋለውን ብረት አብዝቶ  ከመቀጥቀጥ ክንዱ መዛል የለበትም።
Filed in: Amharic