>
5:18 pm - Sunday June 15, 5338

 “አገር እየታመሰ ነው ፤ አገርም የአውሬ መፈንጫ ልትሆን ነው” (ከሲናጋ አበበ)

   “አገር እየታመሰ ነው ፤ አገርም የአውሬ መፈንጫ ልትሆን ነው”

      ከሲናጋ አበበ


   በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ጉሙዝ መጤ ተብሎ በተፈረጀው የአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት እርምጃ እየተወሰደበት በሺ የሚቆጠሩ ንጽሐን ዜጎቻችን እየተጨፈጨፉ ነው፡፡ መንግሥት የሚያሳብበው ኦነገ ሸኔ የሚል የዳቦ ስም ለሰጠው  ነው፡፡ ኦነግ የተባለው ኢትዮጵያን ሊያፈራርስ ታጥቆ የሚገኘው ቡድን ኦነግ ሸኔ የሚባል ድርጅት አለመኖሩን አስረግጦ ይናገራል፡፡ በጃነመሮ የሚጠራው ሌላው አሸባሪ ታጣቂ ቡድን ሸኔ አለመሆኑንና ይህን አሰቃቂ ተግባር አለመፈጸሙን ደጋግሞ ገልጡዋል፡፡ ይኸው አጥፊ ቡድን የልብ ልብ ተሰምቶት፤ ሃይ የሚለውም የመንግስት አካል ባለመኖሩ ሲል ሲል ሰሜን ሸዋ በአሰቃቂ ሁኔታ ጭፍጨፋ አካሂዶ ሴቶችን ሕጻናትን እርጉዥ ሴት ሳትቀር ሆድ ሰንጥቆ ሽሉን አውጥቶ የሚበላ አረመኔ ብድን የመጨረሻ ግቡ አዲስ አበባ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በገሃድ አቢይ ለሪፐብሊካን ጋርዱ ያስታጠቀውን አንዱ እስከሁለት ሺህ ዶላር የሚያወጣ ፤ዘመናዊ ራሽያ ሠራሽ ስናይፐር ይዞ የሚንቀሳቀስ መሆኑን አሸባሪው በምስል አሳይቶናል፡፡ ይህ የሚያመለክተው ፈጻሚው ቡድን በኖቤል የሠላም ተሸላሚው አቢይ አህመድ የሚከናወን መሆኑ ያለጥርጥር ተረጋግጡዋል፡፡ አቢይ ለዚህ ሀላፊነት እንዲበቃ የአማራው ቡድን ከማንም በላይ የሱን ሹመት ያረጋገጠለት እሱ ነው፡፡

ለምን በዚህ እኩይ ተግባር ይሳተፋል ቢባል፤ እንደሚታወቀው በ16ኛው ክፍለ ዘመን የኦሮሞ አባ ገዳ ከደቡብ ወደ ሰሜን ወረራ አካሂዶ ከተገታበት ጊዜ ጀምሮ ያን ሕልም አውን ለማድረግ አመቺው ጊዜ አሁን ነው በማለት የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ በመድረሳቸው ይመስላል፡፡ ጦርነትን አስመልክቶ ዲያብሎሱ መለስ ዜናዊ ለወገኑ ለሕውሐት አመራሮች የሰጠውን ምክር ማንሳት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ይኸውም “….ምንም ቢቸግራችሁ ከአማራ ጋር ወደ ጦርነት እንዳትገቡ….” ሲል  “…….ጦርነት ለአማራው ሠርጉ….” ስለሆነ ነው ብሎ እንደመከራቸው ተነግሩዋል፡፡ ኦሮሞው ግን መካሪ አላገኘም ሁኔታዎች የተመቻቹ ስለመሰለው አማራውን ለማሳደድ ተነሳ፡፡  ግፉ ሞልቶ ስለገነፈለ አማራው ምንም ጊዜም ለአገሩ ለኢትዮጵያ ከማንም በላይ ሕይወቱን መስዋዕት ያደረገ ሕዝብ ስለሆነ ዛሬም አገሩን ይታደጋታል፡፡ በሰሜን የተንቀሳቀሰውን ብሄራዊ ጦር ከውርደት ያዳነው የአማራው ልዩ ሓይል መሆኑን መገንዘብና ማድነቅ ይገባል፡፡ይህ ትምክት ሳይሆን መሬት ላይ ያለ ሀቅ ነው፡፡ ዞር ብሎ ታሪክን ወደ ሑዋላ ለተመለከት ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ያደረገና ፤ የበለጸገ ታሪክ ያጎናጸፋት፤ ከቅርብም ሆነ ከሩቅ የመጣውን ጠላት ከማንም በላይ መስዋዕት ከፍሎ እዚሕ ያደረሳት እሱ ነው፡፡ ያገሬ ሰው “ ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ አለበለዚያ ድንጋይ ነህ ብለው ይጥሉሃል” እንደተባለው የኦሮሞ ልሂቃን አደብ ገዝተው ከሁሉም ጋር ተስማምቶ መኖር አማራጭ የሌለው መሆኑን መገንዘብን ለማህበረሰባቸው በማስገንዘብ ሠላም እንዲወርድ መጣር ይኖረባቸዋል፡፡ በሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን በሀሳብ እንጂ በጦር ሀይል ሠላም ማረጋገጥ እንደማይቻል መገንዘብ ብልህነት ነው፡፡

                  “የማን ቤት ፈርሶ የማን ሊበጅ፤

                   የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ”

                                                              ያለው ማን ነበር !

Filed in: Amharic