>

"ለኮንሶ ህዝብ መሪ ከአዲስ አበባ እንደማይላክለት ሁሉ፣ ለአዲስ አበባ ህዝብም ከአርሲ መሪ ሊመጣላት አይገባም"(ዶክተር በቃሉ አጥናፉ - የባልደራስ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ)

“ለኮንሶ ህዝብ መሪ ከአዲስ አበባ እንደማይላክለት ሁሉ፣ ለአዲስ አበባ ህዝብም ከአርሲ መሪ ሊመጣላት አይገባም”

ዶክተር በቃሉ አጥናፉ – የባልደራስ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ

The abc of Federalism የሚባለው የመጀመሪያው ራስን በራስ ማስተዳደር ነው። ለኮንሶ ህዝቦች መሪ ከአዲስ አበባ እንደማይላከው ሁሉ፣ ለአዲስ አበባም ከአርሲ፣ ከኢሊባቡር፣ ከባህርዳር ወይም ከመቀሌ መሪ ሊመጣላት አይገባም።
ህወሃትም ሆነ ኦህዴድ በፌደራል ስም የሚያጨበረብሩ ድርጅቶች ናቸው። የፌደራሊዝም ስርዓት እያሉ በስሙ ይምላሉ መሬት ላይ ግን አያውቁትም። ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ግን አዲስ አበባ ራሷን ማስተዳደር እንድትችል ይሰራል።
የአዲስ አበባ ህዝብ የአዲስ አበቤ ስነ ልቦና ባለው አመራር ካልተመራ ችግሩ አይፈቱም። ከሌላ አካባቢ የሚመጡ አመራሮች የሜትሮፖሊትያን ከተማን ባህሪ ማወቅ አይችሉም። በመሆኑም የአዲስ አበባ ህዝብ ቀዳሚው ጥያቄ የመኖሪያ ቤት እጦት ሆኖ እያለ፣ እነሱ ግን የህዝቡ ዋነኛ ጥያቄ የመዝናኛ ፓርክ ነው ይላሉ።
የባልደራስ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዶክተር በቃሉ አጥናፉ – ለ ethio 251 የተናገረው
Filed in: Amharic