>

የሹፌሮች ግድያና አፈና !   ሀብታሙ አያሌው

የሹፌሮች ግድያና አፈና !

        ሀብታሙ አያሌው

በተደጋጋሚ ይህ ለ4ኛ ጊዜ በዚሁ ከአዲስ አበባ አማራ ክልል ባለው መንገድ ኦሮሚያ ላይ  የሹፌሮች ግድያ እና አግቶ መውሰድ ተጠናክሮ ቀጥሏል።  አሽከርካሪዎች በተደጋጋሚ ለአማራ ክልል መንግሥት ቀርበው ሰልፍ  በማድረግ ጭምር  ድምፃቸውን አሰምተዋል ።
የክልሉ መንግሥት ከፌደራል መንግሥት ጋር ተነጋግሮ ችግሩ እንዲፈታ የሰራው ስራ ባለመኖሩ ዛሬ ማታ እዛው ቦታ 6 ሹፌሮች እና ረዳቶች አንድ ህፃንን ጨምረው ሲገደሉ 8 ታፍነው ተወስደዋል ። ”  Via  ሰጡ ብርሀኑ
ምክረ ሃሳብ
የሟቾች ቁጥር አስር ደርሷል የሚል መረጃም አለ !
ሽመልስ አብዲሳ  እና አብይ አህመድ ኦሮሚያን  – የደም መሬት አኬልዳማ አድርገው  አገር ማፍረሱን ቀጥለውበታል።  ገዳዩ አካል አቅቷቸው ሳይሆን ሆን ብለው የለቀቁት ያስታጠቁት የሚንከባከቡት ቡድን ነው።
አማራው አሁንም  ንቃ ፣ ተደራጅ ፣ እራስህን ለመከላከል ተዘጋጅ  ተደራጅ ሩዋንዳ እልቂቱ የባሰው አራጆች ሲዘጋጁ ታራጆች የመከላከል ዝግጅት እንኳ አለማድረጋቸው  አስጨርሷቸዋል።  አደረጃጀት ፍጠር መረጃ ተለዋወጥ ተናበብ … የሚያድንህ የሚከላከልልህ መንግሥት የለም።
ተያያዥ መረጃ 
*****
ዛሬ ማምሻውን በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ ከህዳሴ ግድብ በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ማንጎ ሰፈር ላይ ለግድቡ ግንባታ ግብአት የሚያደርሱ 4 የከባድ መኪና ሹፌሮች በጉሙዝ ሽፍቶች ተገድለዋል።
የንፁሃንን ሞትና መፈናቀል መታደግ ያቃተው  በጄኔራል አስራት ዴኔሮ የሚመራው የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት የአገሪቱን ቁጥር አንድ ፕሮጄክት የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቀጠና በጉሙዝ ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር እንዲሆን አድርጓል።
Filed in: Amharic