የአማራ ሕዝብ ፍጅት የሀገራችን ቁጥር አንድ የብሔራዊ ደኅንንት ስጋት ነው!
የህግ ጠበቃ እና የህግ ምሁር መላኩ ሹምዬ
የሕዝብ እልቂትና መፈናቀል በአጠቃላይ: በተለይም በአማራ ሕዝብ ላይ የቀጠለው መጠነ ሰፊ እልቂት እና መፈናቀል የሀገራችን ቁጥር አንድ የብሔራዊ ደኅንነት ችግር ተደርጎ መወሰድ አለበት::
ለችግሩ የሚመጥን አፋጣኝ እና ፍቱን የፖለቲካና ፀጥታ እርምጃ በመውሰድ እልቂቱን ማስቆም የሁላችንም: የሀገርንም ኅልውና የማረጋገጥ ጉዳይ መሆኑ ለአፍታም ቢሆን መረሳት የለበትም:: በተለይ ሥልጣን ላይ ያላችሁ አካላት ለሕዝቡና ሀገር ብላችሁ ባይሆን እንኳ ለራሳችሁ ስትሉ እልቂቱን አስቁሙ::
ሕዝቡም እየጠየቃችሁ ያለው መንግስት የተቋቋመበትን ቀዳሚ ዓላማ-የጋራ ደኅንንታችን አረጋግጡልን ብሎ ነው:: This is not by any means a tall order. በመንግሥት መዋቅር የሚደገፍ እልቂት ይቁም ነው ያለው:: በየትኛውም መለኪያ ጊዜ የሚሰጥ ወይም የቅንጦት ጥያቄ አይደለም:: ከዚህ ያንሰ ጥያቄም ያለ አይመስለኝም::
የሕዝብ እልቂት ማስቆም ካልቻላችሁ ሀገራችን የምትገባበት የደኅንንት ቃውስ ለማሰብም የሚዘገንን እንደሚሆን ለመረዳት የፖለቲካና ደኅንንት ጉዳዮች ሊቅ መሆንን አይጠይቅም::