>

አማራውን ከአዲስ አበቤ የመነጣጠል መንግስታዊ ሴራ...!!! (ጌታቸው ሽፈራው)

አማራውን ከአዲስ አበቤ የመነጣጠል መንግስታዊ ሴራ…!!!

ጌታቸው ሽፈራው

*.…  ትናንት በቄሮና ልዩ ሀይሉ ጥምረት ድንጋይ ኮልኩለው መንገድ ከመዝጋት ሾፌሮችን ወደ ማገትና መግደሉ ተሰማርተዋል፤  ይህ የምትመለከተው አስከሬን ኦሮሚያ ክልል ከፍቼ ደብረጉራቻ መንገድ አሊደሮ ላይ በታጠቁ ሃይሎች የተገደሉ  ሾፌሮች አስከሬን ነው!!
ከጥቃቱ በፊት የኦሮሚያ ፀጥታ ኃይል መንገደኞችን ሲያጉላላና ሲመልስ ነው የሰነበተው። ያለ ምንም ሕጋዊ ሰበብ የዜጎችን ተንቀሳቅሶ የመስራት መብት አግደው፣ አዲስ አበባን የራሳቸው አስመስለው ነው ሌላውን የሚከለክሉት።
ሌላም ምክንያት አለ። ከየትም እየመጣ አዲስ አበባ መታወቂያ ሲወስድ የከረመ፣ የምርጫ ካርድም ሊወስድ ይችላል ተብሎ የሚሰጋ ወጣት ሞልቷል። እነሱ የሚሰሩትን ሌላው የሚሰራ እየመሰላቸው ይሰጋሉ።  ምርጫው እየተቃረበ ሲሄድ ይሄ መንግስታዊ ሕገወጥነት እጅግ እየከፋ እንደሚሄድ ግልፅ ነው። ከምርጫ በኋላ ደግሞ አዲስ አበባን የባሰ ይዘጓታል። ሊቀጧት አቅደዋል። መልዕክቱ ይሄ ነው።
በመንግስት መዋቅር አ

ንድን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ መቆም ይፋዊ ሆኖ ቀጥሏል። ሽፋን ሳይሰጠው ግልጥልጥ ያለ ሆኗል። አንደኛው ክልል ሌላኛውን ክልል ማፍረስ ድረስ የሚያሴርበት፣ ሕዝቡን የሚያሰቃይበት የፖለቲካ እርኩሰት ደረጃ ደርሰናልኮ። ሰበብ እየፈለጉ መንገድ እየዘጉ፣ ሾፌሮችን ስራ እንዲያቆሙ የሚያደርጉበት ሌላኛው መንገድም አማራውን በአቅርቦት ለመቅጣት ጭምር ነው። አዲስ አበባን ከክፍለ ሀገር የሚገባ አቅርቦት እንዳይደርሳት አድርገው ያስጨንቃሉ። ከአዲስ አበባ ወደ ክፍለ ሀገር የሚሄድ አቅርቦትን ደግሞ ይከለክላሉ። ይሄን ከምርጫ በኋላ በይፋ ያደርጉታል። አማራውና አዲስ አበባ እንዳይገናኙ የቻሉትን ሁሉ ያደርጋሉ። ከአንድ አመት በፊት የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ኃይል ዱላና ድንጋይ ከያዙ ወጣቶች ጋር ተባብሮ መንገድ ይዘጋ ነበር። አሁን ደግሞ መንገድ ከመዝጋት የበሰ ጥቃት መጥቷል። እየተፈፀመ ያለው ዝም ብሎ ጥቃት አይደለም። ልናቃልለው አይገባም።
Filed in: Amharic