>

"ወይ ድርድር እንዲካሄድ እናስገድዳለን ካልሆነ ዶክተር አብይን እናስወግደዋለን....!!!" ምዕራባውያኑ (ደጀኔ አሰፋ)

 

“ወይ ድርድር እንዲካሄድ እናስገድዳለን

ካልሆነ ዶክተር አብይን እናስወግደዋለን….!!!”

ምዕራባውያኑ
ደጀኔ አሰፋ

ይህ ድምፅ የምዕራባውያኑ የመጨረሻው ድምፅ ነው:: ወስነዋል:: የመጨረሻውን ጫና ጀምረዋል:: ጫናው እየጨመረ ይሄዳል:: ለምን በአዲስ መልክ ጫናውን ጀመሩ ብንል ተስፋ አድርገውት የነበረው የተመድ የፀጥታው ም/ቤት እነሱ እንደሚፈልጉት ባለመወሰኑ ይመስላል:: በክፍል 3 የመጨረሻ ካርዶችን እንይ :-
.
#1ኛ) ትላንት አመሻሽ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ብሊንከን ዶክተር አብይ ጋር ደውሎ ነበር:: በትግራይ ረሃብ ሊከሰት ስለሚችል ያሳስበኛል:: በሃገሪቱ ያለው የብሄር ውጥረቶችም ያሳስበኛል:: የኤርትራ ጦር ይውጣ:: ሁሉም አካላት ጦርነት አቁመው ወደ ድርድር መምጣት አለባቸው:: ወዘተ የሚል ውይይት አድርጓል:: የዚህ ስልክ አላማ በአጭሩ ከሞተው ጁንታ ጋር “ድርድር እና እርቅ” አድርግ የሚል ነው:: ካልሆነ ግን (የብሄር ውጥረቶች ያልኩህ ሌላ መልክ እንዲይዙ እናደርጋለን:: እርስበርስ ትፋጃላችሁ:: ከዚያም አልቻልክም ተብለህ ከስልጣንህ እናስወግድሃለን..) ዓይነት የሚመስል ቂም ያዘለ መልዕክት ነው:: ይህን የምትረዱት ቀጣይ ነጥቦች ጋር ስታያይዙት ነው:: ተከተሉኝ:: የሚገርመው #ካናዳም ተመሳሳይ የድርድር እና የእርቅ ፍላጎቷን ትላንት በኤምባሲዋ በኩል ለመጀመርያ ጊዜ ገልፃለች::
.
#2ኛ) ባለፈው ሳምንት የአውሮፓ ህብረቱ ጆሴፍ ቦሬል <<ከምርጫው በፊት ዶክተር አብይ ብሄራዊ ድርድር (ዲያሎግ ሊያደርግ ይገባል>> ሲል በድፍረት ተናግሯል:: ምርጫውን ትቶ ድርድር ካላደረገና በኢትዮጵያ ያለው ግጭት ካልቀነሰ ግን የምርጫ ታዛቢ አንልክም ብሏል:: ግጭት የሚለውን አስምሩበት:: ቦሬል አክሎም ከብሊንከን ጋር በስልክ እንዳወራና “በኢትዮጵያ ላይ አዲስ የዲፕሎማቲክ ጫና መፍጠር አለብን” በሚል እንደተስማሙ ገልጿል:: ስለዚህ ኢትዮጵያን በአዲስ መልኩ የሚወጥሩበት ጊዜው አሁን ነው:: ፍላጎታቸው ግልፅ ነው:: እርዳታ የሰጡንና ብድር የፈቀዱልን ይህን የመጨረሻ ጫና ለማስከተል መሆኑን መረዳት አያዳግትም:: መንግስት ይህን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ደስተኛ ነኝ:: skeptical ሆኖ እያያቸው ይመስለኛል::
.
#3ኛ) የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ ከሶስት ቀናት በፊት “ድርድር እንዲካሄድ pressure እንፈጥራለን : ግፊት እናደርጋለን” የሚል አቋሙን ገልጿል:: የG7 ሃገራትም ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው አስታውቋል:: የሚገርመው እንግሊዝ: EU እና አሜሪካ… ሁሉም ብቻ የኤርትራ ጦር ይውጣ ብለዋል:: ይህን የሚሉበት ዋነኛ ምክንያት የጁንታው ትራፊዎች እና ደጋፊዎቹ “የኤርትራ ጦር ከወጣ የኢትዮጵያን ሰራዊት እናሸንፈዋለን” የሚል ከንቱ ምኞት ስለነገሯቸው ይህ ቀቢፀ ተስፋ እውን እንዲሆን በሚል ነው:: የሰብዓዊ መብት ጉዳይ እነሱን የሚያሳስብ ሆኖ አይደለም!!!
.
#4ኛ) ከሶስት ቀናት በፊት ዶክተር ቴድሮስ ከኒውዬርክ ታይምስ ጋር ቃለምልልስ አደርጏል:: ቴድሮስ እስከዛሬ የዘመተብን እና ያስዘመተብን አልበቃ ብሎት ጭራሽ እያለቀሰ ቃለመጠይቅ አደረገ:: ኢትዮጵያን ለማፍረስ እና ጁንታውን ለማትረፍ እስከዛሬ የቻለውን ሁሉ ተሸፋፍኖ ቢያደርግም ስላስልተሳካለት ተስፋ በመቁረጡ በግልፅ አወጣው:: ከምዕራባዊያኑ ጋር ተነጋግሮ አሁን ላሰቡት አዲስ ጫና ግብዓት ለመሆን በሚል ይመስላል ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ ኢንተርቪው ያደረገው:: ከዚያም በገንዘብ የተገዙ ታዋቂ ጋዜጠኞች: ሚዲያዎች: የትላልቅ ድርጅት ሃላፊዎች ወዘተ የሱን ለቅሶ እስከትላንት ድረስ አራገቡት:: ከ110 ሚሊዮን ህዝብ ይልቅ ለአንድ ሰው አስበው ሳይሆን ከነሱ ፍላጎት ጋር የተስማማ በመሆኑ ነው:: #MSF እና ዩኒሴፍም ከቴድሮስ ኢንተርቪው አንድ ቀን ቀደም ብለው ኢትዮጵያን የሚከስ ሪፖርት አቀረቡ:: ይህ ሁሉ ተደማምሮ ጫናው በአዲስ መልክ ቀጥሏል::
.
#5ኛ) አሜሪካ ለምስራቅ አፍሪካ ልዩ ዲፕሎማት መሾሟን አርብ አስታውቃለች:: በቅርቡ ኢትዮጵያ እንደሚገባም ታውቋል:: ጀፍሪ ዴቪድ ፌልትማን ይባላል:: ጡረተኛው ዲፕሎማት ተመድን ጨምሮ በብዙ ሃገራት የአሜሪካ ዲፕሎማት በመሆን ከ 26 አመታት በላይ ሰርቷል:: መለስ ዜናዊ ሲሞትም የቀብር ስርዓቱ ላይ ንግግር ካደረጉት የትህነግ ወዳጆች አንዱ ነው:: የዶክተር ቴድሮስ ጓደኛ ነው:: የአሌክሳንደር ሮንዶስም የቅርብ ወዳጅ ነው:: ሮንዶስን በሚመለከት ከዚህ ቀደም በሰፊው ፅፌያለሁ:: ሰውየው አሁን ሲመጣ የተሰጠው ተልዕኮ በዋናነት “ድርድርና እርቅ” የሚለውን እንዲያሳካ ነው:: ይህ ካልሆነለት ኢትዮጵያን በግጭት ለማተራመስ እና ዶክተር አብይን #ከማስገደል አይመለስም::
ሰውየው ከአንድ ወር በፊት ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ ቀጠናው የተናገረው ነገር ጉድ ያሰኛል:: ጭራሽ  “ግብፅ: ቱርክና የአረብ ኢምሬት ቀጠናውን ለማረጋጋት ሚና ሊኖራቸው ይገባል ብሏል:: አስቡት ግብፅ ለኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ስትሰራ?! የጉምዝን ሽፍታ የሚያስታጥቀው ማን ሆነና? ኦነግ ሸኔን በተለይም ወለጋ ላይ ያለውን ሽፍታ ማን ነው እያስታጠቀ ያለው? ባለኝ መረጃ ወለጋ ላይ በየቀኑ የሚገባው መሳሪያ ለጉድ ነው:: ዘመናዊ መሳሪያ ጭምር ነቀምት ውስጥ በየጊዜው ይጎርፋል:: ከግብፅ የመጣ እንደሆነም ነዋሪዎች ይናገራሉ:: የሰሞኑ ገጀራ በማን እና ከየት የመጣ ነው? ፅንፈኛውንስ በገንዘብ የሚደጉመው ማን ነው? ነባር እና አዳዲስ ዩቱይቦችን እና ቻናሎችን የሚረዳው ማን ነው? በአንድ ጊዜ ይህ ሁሉ የምንሰማው እና የምናየው የጥላቻ ንግግር ማን ያቀደው ነው?? ብዙ ነገር አለ::
ብቻ እዚህ ላይ እንዳይቆጨኝ መናገር የምፈልገው ስለሚመጣው ዲፕሎማት ነው:: ሰውየው በሴራ የተካነ ነው:: ለዚያውም በግድያ ሴራ የካበተ ልምድ አለው:: ግጭት በማስፋፋት በቂ እውቀት እና ልምድ አለው:: ዶክተር አብይን ኢሳያስ አፈወርቂን እና ፈርማጆን በክፉ አይን የሚመለከት ሰው ነው:: የሶስቱን ጥምረት በጭራሽ አይፈልግም:: “ቀጠናው መረበሹ አይቀርም: ኢትዮጵያ እንደ ሶሪያ ልትበታተን ትችላለች: የብሄር ውጥረቱ ወደ እርስበርስ ግጭት ያመራል” ብሎ ያምናል::
ፌልትማን ለፎሬይን ፖሊሲ በሰጠው ቃለመጠይቅ… “የመጨረሻውን አስቸጋሪ ውይይት ከጠሚ አብይ ጋር አደርጋለሁ::” ይህም ከባድ እንደሆነ ከገለፀ በኃላ…. “አብይ ጠንካራ እና አንድነቷ የተጠበቀች ኢትዮጵያን እንጅ የተከፋፈለች ኢትዮጵያን ማየት የሚፈልግ አይመስለኝም:: ይላል በሾርኔ:: ከዚያም… “Ethiopia has 110 million people, If the tensions in Ethiopia would result in a widespread civil conflict that goes beyond Tigray, Syria will look like child’s play by comparison.” ብሏል:: አንድምታው ምንድነው ብንል ዶክተር አብይ የአሜሪካንን ምክረ ሃሳብ ካልተቀበለ ግጭቱ ከትግራይ ይዘልና ኢትዮጵያ ሶሪያን የምታስንቅ ሃገር እናደርጋታለን እንደማለት ነው:: ዛቻ ነው!!!!
ይህ ሰው የአሜሪካ የመጨረሻ ካርድ ነው:: አብይን ለማስገደል ይሰራል ስል የዚህን ሰውየ የግድያ ሴራ ተሞክሮውን እንይ:: ፌልትማን ከ2004 – 2008 በሊባኖስ የአሜሪካ አምባሳደር ሆኖ ሰርቷል:: በወቅቱ ጠሚ ራፊቅ የሊባኖስ ጠሚ ነበር:: ሊባኖስ የተመደበው ራሽያ ቻይና ሶሪያ እና ኢራን ከሌባኖስ ጋር ቅርብ ጉድኝት የፈጠሩበት ወቅት ስለነበርና እንዲሁም ጠሚ ራፊቅ በእስራኤል የተያዘውን የሊባኖስ ደቡባዊ ግዛት ለማስመለስ እንቅስቃሴ የጀመረበት ወቅት ነው:: ጠሚ ራፊቅ ለሃገሩ ብዙ የሰራ እና ብዙ ህልም የነበረው ነበር::
አሜሪካም ሴረኛውን ዲፕሎማት ወደ ሊባኖስ ላከችው:: ሰውየው በገባ በጥቂት ወራት የሊባኖስ ፕሬዝዳንት እና ጠ/ሚሩ ተጋጩ:: አመፅ ተነሳ:: ሊባኖስ ተናጠች:: ፍትጊያው በዛ:: ጫናው ከበደ:: ራፊቅ ከስልጣኑ resign አደረገ:: ለቀቀ:: ከወራት በኃላም መኪናው ውስጥ በ February 2005 በቦንብ ተገደለ:: ገዳዮቹ እስከዛሬ አይታወቁም:: ጠሚ ራፊቅ ከአሜሪካና ከእስራኤል ፍላጎት በተቃራኒ ቆመሃል ስለተባለ በፌልትማን ሴራ እንደተገደለ ይነገራል:: ከዚያ በኃላ ሃገሪቱ ብዙ አመፅ እና ኪሳራ አስተናገደች:: ከሱኒ የተወለደው ራፊቅ የሱን መገደል ተከትሎ በሱኒ እና ሸአ መካከል ከፍተኛ ልዩነት ተፈጠረ:: ግጭቱ ቀጠለ:: ተባባሰ:: ሊባኖስ ብዙ መከራ ገጠማት:: መስማማትና አንድነት ጠፋ:: ብዙ ተጎዱ!
ዛሬም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው ምርጫውን አስቆሞ ጁንታውን እና ሽፍቶችን ወደ ስልጣን በድርድር ለማምጣት:… ካልሆነም በተለይ የኦሮሞ እና አማራን ግጭት በማፋፋም ኢትዮጵያን በማስጨነቅ “አብይ መቆጣጠር አልቻለም” ለማስባል እና ቀጥሎም በግድያም ይሁን በሌላ ዘዴ አብይን ለማስወገድ ነው ብዬ አምናለሁ:: ይህን አጀንዳ የሚያስፈፅሙ ባንዳዎች ቀድመው ይህን ስራ ጀምረዋል:: ጥላቻ እያራገቡ ነው:: የዶክተር አብይን ስም ከተገቢው በላይ ለማጠልሸት እየተሞከረ ያለው አብይን ለማስወገድ ምዕራባዊያኑ ከግብፅ እና ከእስራኤል ጋር የጀመሩት የመጨረሻው ፕሮጀክት አካል ነው:: አሁን የምናየው እጅግ አደገኛ የጥላቻ ንግግሮችም የዚሁ አካል ነው:: ገጀራና መሳሪያ እያስገቡ ነው:: ቦንብም አለ:: የተደገሰልን ብዙ ነው:: ተቀናጅተው እየሰሩ ነው:: በመሆኑም
——–
1ኛ) መንግስት የንፁሃንን ግድያ ያስቁም!!!! በቃ ይህ ንግግር እና ድርድር አያሻውም!!!! ዋናው ይህ ነው!!!! መንግስት ከጨከነ ሞትን መቀነስና ማስቆም ይችላል!!!
2ኛ) መንግስት አሁንም ይፍጠን!!!! ውስጡን ያጥራ!!!! ብልፅግና ውስጥ ብዙ አስፈጻሚዎች አሉ!!!! በተለይ ኦሮሚያ እና አማራ ብልፅግና ውስጥ አሉ!!!! ምንም ርህራሄ አያስፈልግም!!!! እርምጃ ይወስድ!!!! Home arrest is also an option!
3ኛ) በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ መንግስት ክትትሉን ጠበቅ ያድርግ!!!! በአዲስአበባ ዙሪያ የሚኖሩ ወገኖቻችን ይመልከት!!!! ውይይት ያድርግ!!!! ድጋፍ ለሚያሻቸውም ይስጥ!!!! በቂ የፖሊሳና ወታደራዊ ጥበቃ ይደረግ!!!!
4ኛ) የጥላቻ ንግግርን የሚሰብኩ ሚዲያዎች ይዘጉ!!! መሃል አዲስ አበባ ቦሌ መድኃኒአለም ላይ ተቀምጦ ጥላቻን የሚነዛ ቴሌቪዥን ከቶ ምን እየተጠበቀ ዝም ይባላል??? ለጥላቻ የተከፈቱ ዩቲዩቦች ምን እየተጠበቀ ነው??? ጥላቻን የሚነዙ  ወጣቱን በጎበዝ አለቃ እንዲተዳደር የሚሰብኩ : መከላከያን የሚያንቋሽሹ እና የሚከፋፍሉ ሰዎችስ ሃይ አይባሉም ወይ?? መንግስትም ሆነው አክቲቪስትም ሆነው የሚሰሩ ሰዎች አንድ አይባሉም ወይ??? ማንም ቢሆን ህግ ይከበር!!!!
5ኛ) ውድ ኢትዮጵያውያን እናስተውል!!!! እንፀልይ!!! ፈጣሪ ካልረዳን በቀር ከባዱ ጊዜ ከዚህ ይጀምራል!!!! አካባቢያችንን እንቃኝ!!!! ከፀጥታ ሃይሉ ጋር እንናበብ!!!! መረጃ እንስጥ!!!! እንረጋጋ!!!! ከጥላቻ እንራቅ!!!! የምንፅፈውን የምንናገረውን እንምረጥ!!! በዚህ ወቅት ጀግና ጀግና መጫወት አይበጅም!!!ጥላቻም ያጠፋፋናል እንጅ ጠቀሜታ የለውም!!!! ልጆቻችንን እናስብ!!!! ምስኪኑን ገበሬ እናስብ!!!! ኢትዮጵያን እናስብ!!!!
6ኛ) ዶክተር አብይ ከወትሮው የተለየ ጥበቃ እና ጥንቃቄ ያድርግ!!!!! ወዳጅ መስለው የሚደውሉለት የሚቀርቡት የውጭ ሰዎች ላይም ጥንቃቄ ያድርግ!!!! ዙሪያውን ይቃኝ!!! ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን ለማዳከም : እርስበርስ ለማባላትና ለማፍረስ በክፉ ተነስተውብናል!!! አንተንም በክፉ እንዳሰቡህ ከተናገርኩ ከእኔ የተሻለ ሁሉን ታውቃለህ!!!! አንተን በማጥፋት ህዝብ ማፋጀት አስበዋል!!!! ፓርቲህንም ቃኝ!!!! ፈጣሪ ጥበቃውን በአንተ ላይ ያድርግ!!!! በርታ!!!! አይዞህ!!!!የኢትዮጵያ አምላክ ሃገራችንን እና ህዝቧን ይጠብቅ!!!! ያሻግረን!!!! ይህ ቀን አልፎ በድል የምናወራ ያድርገን!!!!! ካስተዋልን እና አንድ ከሆንን እንሻገረዋለን!!!! አሜን!!!!
Filed in: Amharic