>

ቤተ ክህነት "የቅዱስ ፓትርያርኩ መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም!" አለ!! (ኢፕድ)

ቤተ ክህነት “የቅዱስ ፓትርያርኩ መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም!” አለ!!

ኢፕድ

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የሰጡት መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሳይሆን የግላቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስታወቀች።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ተጠሪነታቸው ለቅዱስ ሲኖዶስ መሆኑን የገለፀችው ቤክርስትያኗ፣ ፓትርያርኩ ሰሞኑን የሰጡት መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሳይሆን የግላቸው መሆኑን የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ እና የሲዳማ እና የጌዴኦ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በሰጡት መግጫ  አስታውቀዋል።
የቅዱስ ፓትርያርኩ መግለጫ የሲኖዶሱን አሠራርን ያልተከተለ እና ከሲኖዶሱ ዕውቅና ውጪ የተከናወነ መሆኑን በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በኩል አስነግረዋል።
የቅዱስ ፓትሪያርኩ መግለጫ አሰጣጥን አስመልክቶ በተሰጠው ማብራሪያ ቅዱስ ሲኖዶስ እና ቋሚ ሲኖዶስ ሳይወስን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በግላቸው ቤተክርስቲያንን እና ቅዱስ ሲኖዶስን ወክለው መግለጫ መስጠት እንደማይችሉም ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም በርካታ መግለጫዎች የተሰጡት እና የሚሰጡት የምልዓተ ጉባኤው እና የቋሚ ሲኖዶስ አዎንታ ሲያገኙ መሆኑን በመግለጫቸው አውስተዋል።
Filed in: Amharic