>

ም/ከንቲባዋ ፈጣን ይቅርታ ጠየቁ ...!!! (አባይ ነህ ካሴ)

ም/ከንቲባዋ ፈጣን ይቅርታ ጠየቁ …!!!

አባይ ነህ ካሴ

ያጠፉት ካለ ሥራቸውን ያውቃሉና ይቅርታ መጠየቅ መብታቸው ነው። ይቅርታ በመጠየቅ ሰበብ የተናገሯትን  ግን ሊውጧት ይገባል።
“የኢትዮጵያ ዐደባባዮች የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ናቸው” ብለዋል። መስቀል ዐደባባይም የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ስለኾነ ዛሬ ባታደርጉ ሌላ ቀን ግን ታደርጉበታላችሁ ማለት ፈልገው ነው?
መስቀል ዐደባባይ የሃይማኖት ዐደባባይ ነው። ይዞታውም የቤተ ክርስቲያን። ለይዞታው ማረጋገጫ በቂ ማስረጃዎች አሉን። ወታደራዊ መንግሥት በጉልበቱ ቀምቶ ስሙን ለውጦብን ነበር። ዛሬም በዚያ ዘመን መኖር የሚፈልጉ “አብዮት” ዐደባባይ እያሉ ሲጠሩ ሊያጠፋት ቆርጦ ከነበረው መንግሥታዊ ሥርዓት የዓላማ ትስስር እንዳላቸው ያሳያል።
የም/ ከንቲባዋ ጠጋ ጠጋ አያዋጣም። በየትኛውም ወገን ያላችሁ። ይዞታችንን እየቀማችሁ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን የማዳከም ብሎም የማጥፋት ዘመቻችሁን አቁሙ።
እኛም እያንዳንዷን ሒደት በንስር ዐይን እንከታተላለን። ኦርቶዶክሳውያን የአባቶቼን ርስት በሉ። አንዳንድ የእብድ ገላጋዮች በቤታችን ኾነው የሚያናፉትንም መዝግቡ። ጥንትም ኦርቶዶክሳዊነት ርቱዐዊነት እንጅ ተርመጥማጭነት የለበትም።
Filed in: Amharic