>

የጉድ ሀገር ጃርት ያበቅላል....!!! (ታደለ ጥበቡ)

የጉድ ሀገር ጃርት ያበቅላል….!!!

ታደለ ጥበቡ

 ይገርማል አቶ ታየ ደንዳም “ፓትርያርኩን” ለመውቀስ በቃ። ለነገሩ ሀገሪቱ ሰው ጠፍቶ የጃርት ሀገር ከሆነች ቆየች።  አቶ ታየ ደንዳ መጀመሪያ “ቅዱስነታቸውን” የሚከሳቸው “ወያኔ ነበሩ” በማለት ነው። ጤና ይስጥልኝ አቶ ታየ ደንዳ
1.  አሁን ላይ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት
 ዶክተር አብይ አሕመድ በወያኔ ዘመን  “የኢንሳ” የስላ ድርጅት መሪ አልነበሩምን?
2. አቶ ለማ መገርሳ በወያኔ ዘመን የኦሮሚያ ደህንነት እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
አልነበረምን?
3. አባዱላ ገመዳ በወያኔ ዘመን ፈላጭ ቆራጭ አልነበረምን?
4. አቶ ወርቅነህ ገበየሁ በወያኔ ዘመን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አልነበረምን?
5. ከግርማ ብሩ እስከ ሽፈራው ጃርሶ  ከጁነዲን እስከ ኩማ ደመቅሳ የነበሩ ሰዎች አይደሉም እንዴ የኦሮሞ ወጣትን እራሳቸው ቶርቸር ሲያደርጉና ሲያሳድዱ የነበሩት?
በጣም የሚገርመኝ እነዚህንና ሌሎች በወያኔ ዘመን የነበሩ ባለሥልጣናትን ስለትናቱ በደላቸው “ይቅር” ሲሉህ ተቀብለህ “ተደምረህ” ሲያበቃ የቅዱስነታቸውን የትናንት ታሪክ እያነሳህ የመሳደብ ሞራሉ ከዬት መጣ?
በሁለተኛ  ደረጃ አቶ ታየ ደንዳ ቅዱስነታቸውን ያለፈውን ዘመን  “አላወገዙም” በሚል ከሷቸዋል።
 ጥሩ አቶ ታየ ደንዳ ኦሮሚያ በሚባለው ክልል ንፁሐን  በድንጋይና በዱላ እንደ ዕባብ ተቀጥቅጠው፣ በቆንጨራ ሆዳቸውን ተተርትሮ፣ በጦር ልባቸው ተወግቶ፣ በገጀራ አንገታቸው እና እጃቸው ተቆርጦ፣ በሲባ ታንቀው፣ ከነነፍሳቸው ቤታቸው ተዘግቶ ሲገደሉና ሲፈናቀሉ፣ ቤተክርስቲያን ሲወድም ፓትርያርኩ ሲያለቅሱ  ዝም ያሉ አባ ገዳዎች  በአንዲት ባነር ጽሁፍ “በአማራ ብሔራዊ ክልል ከሰሞኑ በተካሄዱ ሰልፎች ላይ የተሰሙ አንዳንድ መፈክሮች ከባህላችን ያፈነገጡ ናቸው”  ብለው መግለጫ ሲሰጡ  ያኔ ድምጽህን አጥፍተህ ቆይተህ ዛሬ “ቅዱስነታቸውን” ለመስደብ መነሳትህ በጣም ያስገርማል።
ነው ኦሮሚያ በሚባለው ክልል የሚፈፀመውን ጅምላ ግድያና መፈናቀል አባ ገዳዎች እና ስንቄዎች
የማያወግዙት የሚፈፀመው ወንጀል ትክክል ስለሆነ
ነው?
አቶ ታየ ደንዳ ያንተው “ኦሮሙማ”  በቤተክርስቲያንን ለማፍረስ እጁን አስረዝሞ እንደዘረጋ እናውቃለን። ምንም የተደበቀ ሚስጥር የለም።
ሀ. የቅዱስነታቸውን የጥበቃ ሀላፊ ያሰረው ማነው?
ለ. ቅዱስነታቸውን በሰላይ ያስከበባቸውና የፈለጉትን ሰው እንዳያገኙ የከለከላቸው ማነው?
ሐ. በቅዱስነታቸው ሊሰጡ የነበሩ ሁለት መግለጫዎች የፖሊስ ሠራዊ ልኮ የከለከለው ማነው?
መ. ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ወይዘሮ አዳነች አበቤ ፓትርያርኩ ቢሮ ድረስ ሔደው  አቡነ ማትያስን
ከፍ ዝቅ አድርገው በሀይለ ቃል የተናገሯቸው በየቱ ስልጣን ነው?
ሠ. ቅዱስ ፓትርያርኩ ለeotc ቴሌቪዥን የሰጡት ከ1 ሰአት በላይ ቃለመጠይቅ እንዳይተላለፍ በማን ተከለከለ?
ረ. በቴሌቪዥን በሚተላለፍ የፀሎት ፕሮግራም ላይ የሰበኩት ስብከትስ ለምን ታገደ?
ሁሉም ነገር ቀስ በቀስ እየተገለጠ ሲሄድ የናተ ገመና አደባባይ ላይ ይወጣል፤ ትናት የተሳደቡ ኦሮቶዶክሳውያንም ይፀፀታሉ። ግድ የለም… የጊዜ ጉዳይ ነው።
እጃችሁን ከቤተ ክርስቲያን ላይ አንሱ‼️
Filed in: Amharic