የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች ገጽ
የደቡብ ክልል ግዙፉ ህንፃ መቅደስ የሆነውን የአርባምንጭ ደብረ መድኃኒት መድኃኒዓለም ህንፃ መቅደስ ምረቃ እያሳለጡ የሚገኙት የአርባምንጭ ከተማ ኦርቶዶክሳዊ ወጣቶች ለቅዱስ ፓትርያሪኩ እና ለቅድስት ቤተክርስቲያን ያላቸውን ውግንና እየገለፁ ይገኛሉ።
በመግለጫቸው ላይ ካስተጋቡት መግለጫዎች መሀከል….
“በምድር ያስራችሁት ሁሉ በሰማይ የታሰረ በምድር የምትፈቱት ሁሉ በሰማት የተፈታ ይሁን !”
“በፍቃደ እግዚአብሔር የተሰየሙ በቅባ ሜሮን የከበሩ ቅዱስ አባት ላይ አፍህን ትከፍት ዘንድ እንዴት ቻልክ?”
የሚሉ እና ሌሎች መልእክቶችን በጎዳና ላይ ያስተላለፉ ሲሆን መልእክቱን ያዘሉ ባነሮችን አደባባዮች ላይ በመስቀል ለቅድስት ቤተክርስቲያን እና ለቅዱስነቶ ያላቸውን የማይናወጥ ውግንና አሳይተዋል።
በቀጣይ 3 ቀናትም ይህ የክብር መልእክት ማስተጋባት ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር