>
5:26 pm - Saturday September 17, 6388

ባለቤቱን እና ልጁን ጎብኝቶ ከመመለስ ባለፈ ከእስር ተፈትቶ የማያውቀው ጀግናው እስክንድር ነጋ ....!!!

ባለቤቱን እና ልጁን ጎብኝቶ ከመመለስ ባለፈ ከእስር ተፈትቶ የማያውቀው ጀግናው እስክንድር ነጋ ….!!!

ማክቤል ሄኖክ

ታላቁ እስክንድርን ገዢዎች ለዘመናት በተደጋጋሚ  ሲገፉት ቢቆዩም እስኬው ግን ፣ ከቅንነት ወርዶ በጥላቻ ሲለወስ አታየውም። ስታስረው ኖረህ ስታበቃ እሱ ግን ወኔው  በልጦና በርትቶ ላንተ ራሱ ሲተርፍ ታየዋለህ። ያጎነብሳል ብለህ ስታሳድደው ብትኖር ልቡ ተራራ ሆኖ ስነ ልቦናው ጭራስ ገዝፎና ፣ ጠንክሮ ታገኘዋለህ  !!
አምባገነን መንግስታት ገድለው ይጥላሉ ፣ አስረውም ያሰቃያሉ  ህዝቡ ደግሞ ሲደፍር ያምጻል ፤ ሲፈራ እያለቀሰ ያደፍጣል ፣ እንደ #ታላቁ_እስክንድር_ነጋ አይነቱ ጀግና  ደግሞ ለወገኖቹ ነፃነት ሲል ከፊት ሆኖ መከራና ስቃይን ይቀበላል ፣ እራሱን አሳልፎ ይሰጣል ። አዎ የእስክንድር ስለንቦና በአሸናፊነት እንጂ በአልቃሻነት ላይ የተመሰረተ አይደለም ።
ዛሬም እስኬው በእሰር ላይ ቢሆንም ድል ለዲሞክራሲ በሚል ርዕስ  ከቃሊቲ የወጡ ስብስብ ፅሁፎቹን አሳትሞ ለገበያ አቅርቧል ።  መፅሀፉን ገዝቶ ማንበብ እስክንድርን በአካል ቃሊቲ ሔዶ የመጠየቅ ያክል ነውና በእድሉ ተካፋይ እንሁን  !! 
ፍትህ ለእስክንድር ነጋ ፣ ድል ለዲሞክራሲ !!
Filed in: Amharic