>

" የአማራ ደም ደሜነው!" ማለታቸው ነውር የሆነው እሳቸው ወላይታ ስለሆኑ ነው? ወይስ? (መስከረም አበራ)

” የአማራ ደም ደሜነው!” ማለታቸው ነውር የሆነው እሳቸው ወላይታ ስለሆኑ ነው? ወይስ?

መስከረም አበራ

ጋሽ ታዲዎስ ታንቱ ያልተከሰሱበት “ወንጀል” የለም። የአማራ ደም ደሜ ነው ብለሃል ፣ ይህን ለማስፈፀም በህቡዕ ተንቀሳቅሰሃልም ተብለዋል። የምን ህቡዕ???? ጋሽ ታዲዎስ ይህን የሚሉት በግልፅ በሚዲያ ቀርበው ፈርጠም ብለው ነው።
 ጋሽ ታዲዎስ የአማራ ደም ደሜነው ማለታቸው ነውር የሆነው እሳቸው ወላይታ ስለሆኑ ነው????  ወይስ የአማራ ደም ደመ ከልብ እንጂ የወላይታም ፣የከምባታም የአደሬም ደም ሊሆን አይችልም ማለት ነው? ነው አማራ የሚባል ዘር በሌለበት ለምን ስለ አማራ ደም ታወራለህ ነው??????
 በጣም የሚገርመው ወላይታው ጋሽ ታዲዎስ የአማራ ወንድሞቸ ደም መፍሰስ ያመኛል ማለታቸውን ወንጀል አድርጎ የሚከሳቸው ብልፅግና መራሹ መንግስት የምርጫ ቅስቀሳ መሪ ቃሉ “ህብረብሄራዊ ወንድማማችነት ለምናምንቴ.. ” የሚል ዲስኩር መሆኑ ነው። ይህንንም በአንድምታ ስንጠይቅ የብልፅግና ህብረብሄራዊ ወንድማማችነት ማለት የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች  ወንድማማችነት against አማራ ማለት ነው?????ከሆነ አማራ ወንድሜ ነው የሚሉት፣ለአማራው ጥብቅና የሚቆሙት፣የአማራ ህዝብ የክፉ ቀን ልጅ ጋሽ ታዲዎስ ገና ብዙ ክስ ይጠብቃቸዋል…….
ሆኖም እሳቸው ከእውነታቸው ጋር ይቀጥላሉ፣ወያኔም እንዲህ አድርጎት ነበር ያንበረክካቸው ዘንድ ግን አልቻለም!
ሆዱ ያልከበደውን ማንበርከክ አይቻልም!
Filed in: Amharic