ጌታቸው ሽፈራው
*… አሸባሪዎቹ ኦነግና ትህነግ ለሀማስ እንጅ ለፍልስጤም ሕዝብ አይቀርቡም!
ትህነግና ኦነግ ሕዝብ ላይ በደል ሲፈፅሙ የኖሩ አሸባሪዎች ናቸው። ፍልስጤም ሕዝብ ሊያዝኑ አይችሉም። ለሰብአዊነት ግድ የሚላቸው ቢሆን የሚቀርባቸው የሀገራቸው ሕዝብ ነበር። ወለጋና ማይካድራ ላይ የዘር ፍጅት ሲፈፀም ደግፈው የቆሙ አካላት ባሕር ተሻግረው ለፍልስጤም ሕዝብ እናዝናለን ሊሉን አይችሉም። ቅጥፈት ነው። ከፍልስጤም ሕዝብ ይልቅ ሀማስ የተባለው በሕዝብ ደም ፖለቲካ የሚሰራ አሸባሪ ለእነሱ በምግባር ይቀርባቸዋል።
ሁለቱም ተገንጣዮች የሀገራቸውን ሕዝብ በማንነት ለይተው ካላጠፋነው ብለው ሰነድ ሰንደው፣ የዘር ማጥፋት የሚፈፅሙ ናቸው። ሁለቱም ድርጅቶች ንፁሃንን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገድሉ የኖሩ ናቸው። ሁለቱም ድርጅቶችና ደጋፊዎቻቸው የዘር ማጥፍትን ደግፈው፣ የሀሰት ትርክትን እውነት አስመስለው በሀገራቸው ሕዝብ ላይ መከራ የሚያመጡ ናቸው።
ሁለቱ ድርጅቶች ሊቀርቡ የሚችሉት ለሀማስ ነው። አሸባሪነታቸው ያመሳስላቸዋል። በንፁሃን ደም መነገድ ያመሳስላቸዋል። ትህነግና ኦነግ የአረቡን ዓለም ፖለቲካ ይፈልጉታል። ትህነግም ሆነ ኦነግ በውሃውም ሆነ በሌላው ፀረ ኢትዮጵያ በሆነው የአረቡ ዓለም ፖለቲካ ተደጉመው ነው ያደጉት፣አሁንም ድጎማ ያደርግላቸዋል። አሁንም መሳርያዎች ናቸው።