ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ – Eritv
የሀገረ ኤሪትራ ፕሬዚዳንት ክቡር አይተ #ኢሳያስ #አፈወርቂ ከሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ #Eritv ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ተከታዩን ተናግረዋል
አሜሪካ ባሳለፍነው 2 አመት ውስጥ ብቻ ፦አፍጋኒስታንን
፦ኢራቅን
፦የወያኔ የነበረችውን እና አሁን ከወያኔ አገዛዝ ነፃ የወጣችውን ኢትዮጵያንም አጥታለች
አሁን ላይ ደሞ አፓርታይዷን እስራኤልንም አጥታለች ብሎዋል
ሰሞኑን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስላወጣው መግለጫ ተጠይቀው ሲናገሩም ተከታዩን ብለዋል
ዛሬ ዲፕሎማሲያችን ከጎረቤት ሀገራት በተለይ #ከኢትዮጵያ ጋር ተጠናክሮ ባለበት ወቅት ይቅርና ያኔም አሜሪካ እና የወያኔ ንብረት የነበረችው ኢትዮጵያም አግልለውን ላለፉት 20 አመታት ለአሜሪካ ማእቀብ አልተንበረከክንም ነበር ብለዋል
ያኔም ሆነ ዛሬ ወደፊትም መቼም ቢሆን ለአሜሪካ #አንንበረከክም በማለትም አስረግጠው ተናግረዋል
ኤሪትራ በሁሉም መስክ በሚባል መልኩ እራሷን ለመቻል ጥረት ስታረግ መኖሯ እና አሁን ላይ የራሷን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ አልፋ ለሌሎቹም መትረፍ የምትችል ሀገር ሁናለች
ላለፉት 24 አመታት ማንኛውም የውጭ እርዳታ በተለይ ከአሜሪካ ተቀብለን የማናውቅ ሲሆን ይህችው ዛሬም የምትዝትብን #አሜሪካ የጣለችብንን ማእቀብም ላለፉት አመታት ተቋቁመን ኖረናል ብሎዋል
ስለዚህ #ከአሜሪካ ጋር ያለን ግንኘነት ተሻሻለ አልተሻሻለ እኛ አይሞቀንም አይበርደንምም ብለው አስረግጠው ተናግረዋል
ሀገረ #ኤሪትራ ወደፊት ስላወጣችው የእድገት ፕላን እና ለቀጣይ #አሜሪካ ልታደርግላት ስለምትችለው እርዳታ ሲጠየቁም ፕረዚዳንት #ኢሳያስ ተከታዩን ብለዋል
እኛ #ኤሪትራውያን #የአሜሪካንን እርዳታ ፈፅሞ አንፈልግም
እኛ የምንፈልገው #አሜሪካ እንድትረዳን ሳይሆን #እንድትተወን እና የክፋት #እጇን ከኛ ላይ እንድታነሳ ብቻ ነው በማለት መልስ ሰጥተዋል