>

የኒውዮርክ ታይምስ ኢትዮጵያ ዘጋቢ ከሀገር ተባረረ.. !!! (አዲስ ታይምስ)

የኒውዮርክ ታይምስ ኢትዮጵያ ዘጋቢ ከሀገር ተባረረ.. !!!

አዲስ ታይምስ

«ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ በማቅረቡ» ከሀገር መባረሩን የመንግሥት ባለሥልጣን ማረጋገጣጠውን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ከአዲስ አበባ ዘገበ። ኢትዮጵያ ውስጥ ለሁለት ዓመት ገደማ መቆየቱን ያመለከተው ሲሞን ማርክስ የተባለው አየርላንዳዊ ጋዜጠኛ በራሱ የትዊተር ገጽ የኢትዮጵያ መንግሥት ሐሙስ ዕለት ከሀገር እንዳባረረው ገልጿል። ጋዜጠኛው «የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ወደ ቤቱ ሄዶ ንብረቱን ለመሰብሰብ ብቻ ሳይሆን ሰዎችን ለመሰናበት እንኳ ፋታ አልሰጡኝም» ሲልም የደረሰበትን ዘርዝሯል። የጋዜጠኞችን የመብት ይዞታ የሚከታተለው ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስተዳደር የውጭ ጋዜጠኛ ሲባረር የመጀመሪያ መሆኑን በማመልከት ድርጊቱን ኮንኗል። ኒውዮርክ ታይምስ ዘጋው ከኢትዮጵያ ከመባረሩ በፊት በጻፈው ዘገባ ምክንያት ትናንት ባለሥልጣናት ጠርተው አነጋግረውት እንደነበረና በአውሮፕላን ማረፊያም ለስምንት ሰዓታት አቆይተው ከእኩለ ሌሊት በኋላ በተነሳ አውሮፕላን እንደሸኙት አመልክቷል። የጋዜጣው ረዳት ሥራ አስኪኢጅ ማይክል ስላክማን «የኢትዮጵያ መንግሥት ሲሞን ማርክስን እንደ ወንጀለኛ በመያዝ፣ ከቤቱ ንብረቱን እንኳ እሚሰበስብበት ፋታ ሳይሰጥ ማባረሩ  አስጊ ነው» ማለታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ በዘገባው ጠቅሷል። የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ኃላፊ መሐመድ ኢድሪስ ለዜና ወኪሉ ዛሬ በሰጡት ምላሽ ማርክስ ያለ ዘጋቢነት ሥራ ፈቃድ ሀገር ውስጥ መቆየት እንደማይችል ገልጸዋል። «እዚህ ያለኸው ለሥራ ነው። ፈቃድ ካለህ ትቆያየለህ። ፈቃድ ከተቀማ ግን ኃላፊነት ያለው አካል ወደመጣህበት ይመልስሃል።» ማለታቸውንም አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ጠቅሷል። አዣንስ ፍራንስ ፕረስ እንደዘገበው ማርክስ በትግራይ ክልል ስለሚካሄደው ውጊያ ጠንካራ ዘገባዎችን በተከታታይ ሠርቷል። የተሠጠው የሥራ ፈቃድ ባለፈው መጋቢት ወር ከትግራይ ተመልሶ ጥቂት እንደቆየ መሰረዙንም አመልክቷል።
Filed in: Amharic