>

"ህገ መንግስቱ" ከህወሀት ማኔፌስቶነት ወደ ኦሮሙማ  ማኔፌስቶነት ተቀይሯል!! (አምሀራ ኢንፎርመር)

“ህገ መንግስቱ” ከህወሀት ማኔፌስቶነት ወደ ኦሮሙማ  ማኔፌስቶነት ተቀይሯል!!

አምሀራ ኢንፎርመር

የኦሮሞ ብልፅግና ይፋዊ ባልሆነ መንገድ የትህነግንና የኦነግን “ህገመንግስት” ወደ ኦሮሙማ ማኒፌስቶ (የኦሮሞ ብልፅግና) ሰነድነት ቀይሮታል። የአማራ ብልፅግናም ይህንን እውነታ እየመረረው አምኖ ተቀብሏል። ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ እንደተናገረው ብልፅግና ፓርቲ እውነትም የኦሮሞ ነው፤ ኦህዴድም በሚደንቅ የአፈፃፀም ብቃት ወደ ኦሮሙማ ተለውጧል።  የኦሮሞ ብልፅግና (ኦሮሙማ) ህዝቤን ይጠቅማል የሚለውን ሁሉ ያለ ይሉኝታና ያለ ህግ ማክበር እየፈፀመ ነው።
ኦሮሙማው በሚገርም ፍጥነትና መናበብ “ህገመንግስት” የሚሉትን ሁሉ እያሽቀነጠሩ እየጣሉ ለህዝባቸው የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው። ዛሬ በፌደራል መንግስት መቀመጫዋ አዲስ አበባ አዲስ አበቤውን ለመዳኘት የኦሮምኛ ፍርድ ቤት አቋቁመዋል።
የከተማዋን ተቋማቶች ውስጥ ለውስጥ በሰው ሐይልም በቋንቋም ቀይረውታል። ወርረውታል። ለክልላቸው ህዝብ የማይሰሩት የልማት አይነት የማያቀርቡት የአገልግሎት አይነት የለም። ጎበዞች ናቸው። ህዝቤን አገለግላለሁ ካሉ አይቀር እንዲህ ነው።
የፌዴራል ሲቪል ተቋማትን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ሰልቅጠዋል። የተወሰኑ የሚኒስቴር መስሪያቤቶችን ሃላፊዎች ማለትም ሚኒስትሮች አማራዎችን አድርገው ከስሩ ባሉ ተጠሪ ተቋማቶች እና Departments ሙሉ በሙሉ በኦሮሙማ ተሞልተዋል። የአብይ ብልጠት እዚህ ድረስ ነው። አማራው የተወከለ እንዲመስል ከላይ አንድ ብአዴን ይሾምና ከስሩ ባሉት ዳይሬክተሮች በኩል ስራውን ያሰራል።
የፌደራል ወታደራዊ እና የፀጥታ ተቋማትን የአ.አ ከተማን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ በኦሮሙማ አስይዟል። በዚህም የኦሮሙማ ፕሮጀክት በፍጥነት ከህግና ከአሰራር ውጪ ያለ ይሉኝታ በጥድፊያ እየተፈፀመ ይገኛል። “በህገመንግስቱ ” ላይ የተቀመጡት የፌዴራል እና የክልል መንግስታት አወቃቀር እና ሀገራዊና ብሔራዊ ድንጋጌዎች ሁሉ “ህገመንግስቱ” ይሻሻል የሚሉትን ወገኖች እየሞገቱ እነሱ ግን ቀደው ጨርሰውታል።
ለምሳሌ 1: በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ተቋማት የፌደራሉም ሆነ የከተማ አስተዳደሩ ቋንቋቸው በህግ ሳይፀድቅ ኦሮምኛ እየሆነ ነው። “ህገመንግስቱ” ሳይሻሻል ለምን ይህ ሆነ ካልክ በድፍረት እኛ ተረኞች ነን ወይም ልዪ ጥቅም ይገባናል የሚልህ ገልቱ አታጣም።
ምሳሌ 2: አደስ አበባ የምትጠቀመውን ውሃ ከኦሮሚያ በሜትር ኩብ ህዝቡ እንዲከፍል የሚያስችል መመሪያ እየተዘጋጀ ይገኛል። ስለሆነም አዲስ አበቤው ለሚቀዳው ውሓ ለኦሮሚያ ለልዪ ጥቅም መብት ይከፍላል ማለት ነው።
ምሳሌ 3: የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የኦሮምኛ ቋንቋን እንዲያስተምሩ ገዳጅ ተጥሎባቸው ማስተማር ከጀመሩ አመት አልፏቸዋል።
ምሳሌ 4: በአዲስ አበባ የሚገኙት የከተማ አስተዳደሩም ሆነ የፌዴራል መንግስቱ አንዳንድ ተቋማትና የሰራተኛ ማህበራት የባንክ ቡካቸው በኦሮሞ ባንኮች ብቻ እንዲሆኑ ከተደረገ ቆይቷል።
ወዘተ …”ህገመንግስቱ”  አማራውን በይበልጥ እንደሚያጠቃ የተረዳው ኦሮሙማ ይሻሻል ሲባል እንደ ነብር ይሆንና በጎን ግን ሀይል ሁሉ የኛ ነው በሚመስል መልኩ ይከበር የማሉትን “ህገመንግስት” አሽቀንጥረው እየጣሉ የሚፈልጉትን እየሰሩ ቀጥለዋል። አሻሽለውታል ማለት አይደለም?
Filed in: Amharic