>
5:26 pm - Tuesday September 15, 2731

"ዓብይ አህመድ ግልጽ ጦርነት በአደባባይ አውጀህ እግረ ሙቅ ያስገባህባቸውን የህሊና እስረኞች ፍታ...!!!" (ኤርሚያስ ለገሰ)

“ዓብይ አህመድ ግልጽ ጦርነት በአደባባይ አውጀህ እግረ ሙቅ ያስገባህባቸውን የህሊና እስረኞች ፍታ…!!!”
ኤርሚያስ ለገሰ

*…. ከምርጫ-በፊት-የሕሊና-እስረኞች-ይፈቱ!!!
 
 ማለት ከብዶህ፤  አገሪቱ የገባችበትን ምስቅልቅል የህውሃት/ኦሮሙማ   ሚኒስትሮች እና ዲፕሎማቶች ሽግሽግ እንዲፈታ ብዕርህን ስታደማው ከማየት በላይ የሚያሳፍር ነገር የለም። እርግጥ ድርጊትህ የውስጥ ፍላጎትህን ገሃድ ቢያወጣውም!!
በዚህ ወሳኝ ስዓት እኛ አዲስአበቤዎች ግን የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጠው ዓብይ አህመድ ዓሊ እግረ-ሙቅ ያጠለቀባቸውን የፓለቲካ እስረኞች የሆኑ መሪዎቻችንን ይቅርታ ጠይቆ ያለ እንዳች ቅድመ-ሁኔታ እንዲፈታቸው ነው። እደግመዋለሁ በዚህ አጥረቅራቂ ስዓት እኛ አዲስአበቤዎች አጥር ላይ የምንጠለጠል የገበቴ ውሃ አይደለንም። የዝንጀሮ ቆንጆ እያማረጥን የአገዛዝ በትር የምናሰጥ ውታፍ ነቃዮች አይደለንም። እንደ ጋሪ ፈረስ አይኖቻችን መሪዎቻችን ላይ የተተከሉ ናቸው። ለዓብይ አህመድ የሕሊና እስረኞች የመስቀል ወፍ አይደለንም። በየጊዜው የምንለውጠው ማሊያ፣ ቁምጣ፣ ታኬታ፣ ገምባሌና ካልሲ የለንም።
ባይሆን የባይደን አስተዳደር የፓለቲካ እስረኞችን እና ብሔራዊ ውይይቶች እንዲካሄዱ የባለስልጣናት የጉዞ ማዕቀብ ሲጥል ምስጋና እናቀርባለን። ኢትዮጵያ በዋናነት የህልውና አደጋ የሚያጋጥማት የውስጥ ችግሯን መፍታት የተሳነው የአመራር ስርዓት እና መሪ ሲያጋጥማት ብቻ መሆኑን ስለምንገነዘብ!!
Filed in: Amharic