>

መርህ ወዴት አለህ....?!? (ያሬድ ሀይለማርያም)

መርህ ወዴት አለህ….?!?

ያሬድ ሀይለማርያም

*… እንዲህ ያሉ እርምጃዎች ፍርድ ቤቶችን አያኮስሳቸውም ወይ? ነገስ ከምርጫው ጋር በተያያዘ አለመግባባቶች ቢፈጠሩ ወዴትኛው አካል ሊኬድ ነው? ተሳስቼ ካልሆነ በተመሳሳይ መልኩ ሌሎች ፖርቲዎችም እንዲሁ በፍርድ ቤት ባስወሰኗቸው ጉዳዮች ቦርዱ ለመፈጸም ‘እቸገራለሁ’ ሲል ተደምጧል። ‘እቸገራለሁ’ መልስ ይሆናል???
 
National Electoral Board of Ethiopia- NEBE -የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠበትን ጉዳይ በአንዲት ደብዳቤ እንደ ውሳኔው ለመፈጸም ‘እቸገራለሁ’ ማለት ይችላል? ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ቅሬታ ካለው ያለውን የሕግ መስመር ተከትሎ ውሳኔው እንዲሻር ይጠይቃል እንጂ ለተፈረደለት አካል እንዲህ ያለ መልስ መስጠት አግባብ ይሆናል ወይ? እርግጥ ነው ቦርዱ ብዙ ዝግጅቶችን ባጠናቀቀበት በዚህ ወቅት የሚነሱ አዳዲስ ጉዳዮች ችግር ይፈጥሩበት ይሆናል። ሆኖም ይህን ለፍርድ ቤት አስረድቶ ወሳኔው ላይ በክርክር ወቅት ዳኞችን ማሳመን ካልቻለና ሊያውም በሰበር ችሎት ከተወሰነበት በኋላ ግን የፍርድ ቤቱን የመጨረሻ ውሳኔ እንዴት አልቀበልም ይላል? እንዲህ ያሉ እርምጃዎች ፍርድ ቤቶችን አያኮስሳቸውም ወይ? ነገስ ከምርጫው ጋር በተያያዘ አለመግባባቶች ቢፈጠሩ ወዴየትኛው አካል ሊኬድ ነው? ተሳስቼ ካልሆነ በተመሳሳይ መልኩ ሌሎች ፖርቲዎችም እንዲሁ በፍርድ ቤት ባስወሰኗቸው ጉዳዮች ቦርዱ ለመፈጸም ‘እቸገራለሁ’ ሲል ተደምጧል። ‘እቸገራለሁ’ መልስ ይሆናል? ቦርዱ ከፖርቲዎቹ ጋር ተደራድሮ ለጠቅላላ የአገር ጥቅም ሲባል ይህን መብታቸውን በፈቃደኝነት እንዲተው መደራደር አይሻልም?
Filed in: Amharic