>
5:13 pm - Thursday April 19, 5607

ማእቀቡ ለአገዛዙ መልካም እድል ወይስ ስጋት? (ጎዳና ያእቆብ

ማእቀቡ ለአገዛዙ መልካም እድል ወይስ ስጋት?

    ጎዳና ያእቆብ

አቶ ደመቀ መኮንን <<ቪዛ ሊከለክሉን ይችላሉ: ከብልፅግና ጎዞ ግን ሊያቅቡን አይችሉም የሚል>> የሞኝ ንግግር ሲናገሩን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር መሆናቸውን ስታክልበት ኢትዮጵያ ላይ የመጣው መከራ ምን ያህል እንደሆነ ማሳያ ነው:: << ሕዝቤ እውቀት በማጣት ምክንያት ጠፍቷል>> የሚለው የቅዱሱን መፅሀፍ ቃል ያስታውሰኛል:: 
በማእቀብ ውስጥ ሆኖ የበለፀገ አንድ ሀገር መጥቀስ ከተቻለ እስቲ አግዙኝ? 
እንደ ኢራን የመሰለ ተፈጥሮ በነዳጅ ከርሰ ምድሯን ያጠገበቻት ሀገር እንኳን በማእቀብ እንዴት ተሰባብራ ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንደመጣች ማጣቀስ የማይችል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር: የሚፋንንበት ብር ከየት እንደመጣ እንኳን ረስቶ ሞያሌና አድዋ መሄድ እስከቻልኩ ድረስ who cares! የሚለውን ሽመልስ አብዲሳን ስታደምጥ ላለፉት 30 አመታት በተለያየ እርከን የመንግስት ስልጣን ይዘው የኖሩ ባለስልጣኖቻችንን ከእውቀት የፀዱ ብቻ ሳይሆን እውቀት የማይዋሀዳቸው እንደሆኑ ማስገንዘቢያ ነው:: አላዋቂነትና እብሪት ሲዋሀዱ ደግሞ recipient for disaster የሚሉት ነው የሚሆነው::
አርሰን ኤክፓርቱን ከፍ እናድርግ ሲል የኢኮኖሚ ማእቀብ አድጎ መሸጥ መለወጥን እንደሚነካ አለመገንዘን ምን የሚሉት ነው? ኢራን ኢራቅ አለም የሚፈልገውን ነዳጅ ታቅፈው ሲያኩ እንዲኖሩ የተደረጉት በማእቀብ መሆኑን እንዴት መገንዘብ ይቸግራል?
ኩባን በ1960ቹ ላይ ተቸንክራ እንድትቀር ያደረጋት ማእቀብ እንጂ የምትሸጥ የምትለውጠው ሳይኖራት ቀርቶ ወይም የተማረ ሀገር ወዳድ ሀይል ስለሌላት አይደለም:: ወይም ሰሜን  ኮሪያ ከአለም ተገላና ብቻዋን ያለች ደሴት ሆና እንድትኖር የተደረገችው የቻይና ወዳጅነት ስለሌላት ሳይሆን የማእቀብ ቀንበሩ በወዳጅነታቸው ልክ እንዳይረዱዋቸው የማእቀብ ግድግዳ ስለገታቸው ነው::
ሽመልስ ማእድን አለን: ወርቅ አለን ሲል ገዢ ከሌለ የወርቅ ተራራ ቢኖር ተሽጦ የውጭ ምንዛሪ ካላመጣ ከጥቅሙ አንፃር እምብዛም ፋይዳ አይኖረውም:: ይህ የቪዛ ክልከላ የማእቀብ ጅምር እንጂ መጨረሻ እንዳልሆነ አውቀው ሰከን ብሉ ጥሩ ነው::
የዛሬ ወርም ይሁን የዛሬ 30 አመት የውይይት መድረክ መክፈታቸው አይቀሬ ሆኖ ሳለ ስለምን ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊያንን ለችግርና ለመከራ ይዳርጋሉ:: አመራሩ እንደው ምቾቹ አይቀርበትም ይብላኝ ለህዝብ እንጂ::
ሽመልስም አማራን ከኦሮሚያ ለማፅዳት ትጥቅም ስንቅም አይጎድልበትም:: የባእዴን አመራሮችም ሆዳቸው አይጎድልባቸውም::
ጎረቤታችንን ኤርትራን ተመልከቱ?
ማእቀብ ሕዝቡን አደቀቀው እንጂ ኢሳያስ ምን ጎደለበት?! ከአለም ተገሎ ብልፅግና ከመብራት መስመር ጋር ያልተገናኘ አምፓል ነው:: አይሰራም::
ባይሆን አንድ 5 አመት ማእቀብ ውስጥ ሆኖ እና ኢምባሲዎችን ዘግቶ አዲስ አበባን irrelevant ማድረግ ይቻል ይሆናል:: ለስልቀጣውም ይመቻል:: የኦሮሚያ ተቋማት እና የክልሉን ጥቅም ለማስከበር ተብሎ የተጀመረው የኦሮሚያ ፍርድ ቤት በግለሰብ ደረጃ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ በቋንቋው የመዳኘት ህገ መንግስታዊ መብት ብሎ የለጠጠው አንተ ሀገር ተደፈረች ብለህ አገር ይያዝ በምትልበት ወቅት ነው::
ታዛቢ እያለ እንኳን ካለይሉንታና አንድ ሳይፎርሹ ይህን ያህል ከተጓዙ ታዛቢ የለ ይሄ ይቀርብኛል ብሎ መስጋት ሳይኖረው ምን ያህል በህግም ያለህግም አዲስ አበባን እንደሚውጧት ካላየሁ አላምንም ለምትሉ ቶማሶች በቅርቡ የምታዩት ሀቅ ይሆናል::
ገለልተኛ አካል ይግባ ያጣራ ሳይባል በሚኖር አምስት አመት አማራውን እንኳን ከኦሮሚያ ከአማራም ክልል ለማፅዳት በቂ ጊዜ ይመስለኛል:: በአጣዬ የጀመረ ስለሆነ ብዙም መመራመር የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም:: ቅርሶች ታሪካዊ ቦታዎች እና ኦርቶዶክስን ለማድቀቅ እጅግ በጣም በቂ ጊዜ ይመስለኛል::
መከራህን እና መገለልህን ለፓለቲካ ቁማር አውለውት እነሱ ህዝብ ከመንግስት ጎን እንዲቆም ይረዳል እያሉ ነው:: ስልጣናቸውን ያፀናል::
ነፃነቱ ለነሱ ባርነቱ ለህዝብ ይሆናል::
እነሱ ባንተ ደምና ላብ ይበለፅጋሉ አንተን ግን የኑሮ ውድነቱ አቆርቁዞና ሰብሮ የመንግስት ጥገኛ: የአገልጋዮችህ ባሪያ ያደርግኃል::
Filed in: Amharic