>

የኦነግ ሸኔ (ኦህዴድ ሸኔ) ጥቃት በመተከል ቀጥሏል ...!!! (መተከል ሚድያ ኔትዎርክ)

የኦነግ ሸኔ (ኦህዴድ ሸኔ) ጥቃት በመተከል ቀጥሏል …!!!

መተከል ሚድያ ኔትዎርክ

*…መንግሥት በሌለበት ሃገር ሁሉም ይደረጋል !
 
*…. የመተከልና ጋምቤላ ተገናቃዮች ለረሀብ አደጋ ተጋልጠዋል
መተከል ዞን ቡለን ወረዳ ጎንጎ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ አቶ ወርቁ ሰዲ ና ስሙን ያላወቅነው አንድ ሰው በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ታፍኖ መወሰዱን ና መገደሉን ሰምተናል።
በቡለን ወረዳ ውስጥ ጎንጎ ቀበሌ፤በድባጤ ወረዳ ውስጥ አልባሳ፣ ቆርቃ ፣ሰምቦሰሬ፣ ጨልያ ፣ጌሼ ና ዳላቲ ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ውለዋል።እኒህ ቀበሌዎች ኮማንድ ፖስት የማይሄድባቸው ቦታዎች ስለሆኑ በርካታ ግፎች እየተፈጸሙባቸው ይገኛል።
በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ በርካታ የአማራና የአገው ማኅበረሰቦች አስቀድመው የወጡ ሲሆኑ አሁንም ጥቂቶቹ ብቻ ቀርተዋል።የመረጃ ምንጮቻችን ባደረሱን መረጃ መሰረት ታጣቂዎቹ አከባቢው ላይ ከሚኖሩ ኦሮሞ ማህበረሰቦችም መሳርያ እየቀሙ የወሰዱ ሲሆን በፈለጉ ሰዓት እየመጡ ከምግብ ጀምሮ የተለያዩ ነገሮች እንደሚዘርፉ እና የፈለጉትን ሰው እየወሰዱ እንደሚገሉ ሰምተናል።
የመተከልና ጋምቤላ ተገናቃዮች ለረሀብ አደጋ ተጋልጠዋል
ከቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ሰዳል ወረዳ ተፈናቅለው በምዕራብ ወለጋ መንዲ እና ሌሎች አካባቢዎች የተጠለሉ ዜጎች የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እያገኙ እንዳልሆነ አስታወቁ፡፡
    ከሚያዚያ 12/2013 ዓዓም በካማሺ ዞን ሰዳል ወረዳ  በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ከ1ሺ በላይ ዜጎች  ቤት ንብረታቸውን ለቀው ወደ መንዲ ከተማ እና አካባቢው መሸሻቸውን  ተናግረዋል፡፡
የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ከሰዳል እና ጉልሶ የተፈናቀሉ  ከ3ሺ በላይ ዜጎች በአሶሳ  ዞን ባምባሲ ወረዳ በተዘጋጀው መጠለያ ጣቢያ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸው ከክልሉ ውጪ ያሉትን ተፈናቃዩች ድጋፍ ማቅረብ እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡
በክልሉ የተጠለሉ ዜጎች በመንግስትም፣ በግል ድርጅቶችም በተለያዩ ጊዜያት ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ ገልጸዋል፡፡
ከምእራብ ወለጋ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር  በስልክ መረጃ ለማግኘት  ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡በሚያዚያ ወር በካማሺ ዞን ሰዳል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር በአሶሳ ዞን እና በምዕራብ ወለጋ ተጠልሎ ይገኛሉ፡፡
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ግንቦት 14 2013 ዓ.ም  ባወጣው መግለጫው በሰኔ ወር አጋማሽ በሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ በጸጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች በከማሺና መተከል የምርጫ ክልሎች 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ተግባራዊ ከማይደረግባቸው አካባቢዎች ተጠቃሾች መሆናቸውን አስታውቋል።
Filed in: Amharic