እስክንድር ነጋ ለህይወቱ አስጊ ለጤናውም አደገኛ ወደ ሆነ ዞን መቀየሩ ለምን አስፈለግ ??? በእነማንስ ትእዛዝ…!!!
ዘመድኩን በቀለ
… የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ፣ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ሊቀመንበር እና የአዲስ አበባ ምክርቤት ዕጩ ተወዳዳሪው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ህይወቱ አደጋ ላይ መውደቋን የደረሰኝ መረጃ አመልክቷል።
… የፍርድ ቤቱ የእስክንድርን በምርጫው መሳተፍ ውሳኔና በእስክንድር የተጻፈውን ” ድል ለዲሞክራሲ” መጽሐፍ መታተም ተከትሎ በዶር ዐቢይ አሕመድ ጓደኛ በዐቃቤ ሕግ ሹሙ በዶር ጢሞቴዎስ ቀጥተኛ ትዕዛዝ እስክንድር ቀድሞ ከታሰረበት ዞን አሁን ወደሚገኝበትና ለህይወቱም ለጤንነቱም አስጊ ወደሆነው ዞን በግዳጅ እንዲቀየር መደረጉ ነው የተሰማው።
… ከውስጥ ከፖሊሶች የደረሰኝን መረጃ ሌሎች ሰዎች ራሱ እስክንድርን አነጋግረው እንዲያረጋግጡልኝ ያደረግኩ ሲሆን እስክንድርም እውነታውን እንዳረጋገጠላቸው በአካል የጠየቁት ወገኖች አረጋግጠውልኛል። እናንተም የምትችሉ በነገው ዕለት በመሄድ ማረጋገጥ ትችላላችሁ።
… እስክንድር ተቀይሮ በታሰረበት ዞን ” የድብደባ ሙከራ” ተደርጎበት እንደነበር እና በታራሚዎች ርብርብ ድብደባው ለጊዜው መክሸፉ ተረጋግጧል። “ህወሓት በህዝብ እንድትጠላ ካደረጉት ሰዎች መካከል ቀንደኛው ሰው አንተ ነህ” የሚሉ የህወሓት አባል እስረኞች ናቸው አሉ የግድያና የድብደባ ሙከራ አድራጊዎቹ።
… እስከዛሬ ሲታሰር እና ሲፈታ የኖረው እስክንድር አሁን እነ ዶር ዐቢይ ከነበረበት ዞን ቀይረው ካስመጡት በኋላ የጤንነቱ ሁኔታም አሳሳቢ እንደሆነና በተለይ ዛሬ የጠየቁት ሰዎች ” ብርድ ሳይመታው” እንዳልቀረም ተናግረዋል።
… ዝርዝር መረጃውን የምመለስበት ቢሆንም ለጊዜው ዶር ዐቢይ አሕመድ… ዶር ጢሞቴዎስ ጌዲዮን ምክንትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች እና የእስክንድር ለምርጫ ይወዳደር ዘንድ በፍርድበት ውሳኔ ከተሰማ በኋላ ወዶገቦቹ የጠቅላዩ አማካሪ የኢዜማ መሪዎች ሁላችሁም ቆም ብላችሁ ደጋግማችሁ ብታስቡ መልካም ነው። እስክንድርን አሁን ከከተታችሁት ቅርቃር በጤናና በህይወቱም ላይ ችግር ከሚያስከትል የአደጋ ዞን በአስቸኳይ ብታወጡትም ይመከራል።
… ሰምታችኋል !!