>

ባልንጀራዬ ማን ነው? የአብይ አህመድ ባንዳና ባዳ ዲስኩር...!!! (ጎዳና ያእቆብ)

ባልንጀራዬ ማን ነው? የአብይ አህመድ ባንዳና ባዳ ዲስኩር…!!!

ጎዳና ያእቆብ

የአብይ አህመድ ንግግሮች መስማት የሚያታክትበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ገና እንደመጣ የሚናገራቸው አስደማሚ ንግግሮች አልቀው፣ ተገርበው አሁን አሁን የጠላ ቤት እና የመንደር ወሬዎች መሆን ከጀመሩ ሰነባብተዋል። በቀጥታ የተኮረጁ ንግግሮችም ትናንት ቢያንስ ከነ ሂነሪ ኪሲንጀር፣ ልደቱ አያሌው፣  አርስቶትል፣ ሄግል፣ ኒቻ፣ ኦባማ መሆኑ ቀርቶ ቲክ ቶክ ላይ መገኘት ጀምረዋል። መንደር መንደር መሽተት ከመጀመራቸውም አልፎ እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ብቻ ሳይሆን የሚደነቃቀፉም ከሆኑ ውለው አድረዋል።
ለምሳሌ ያህል ከሰሞኑ ባንዳና ባዳ የሚለውን ሀሳብ የጠፋበትን የቃላት ጋጋታ ሲደረድር « የሙቀጫ ግልገልን እናቱን ይወቅጣል» በሚል ሲከሰው አድምጬ « የሙቀጫ ግልገል መውቀጥ ተፈጥሮአዊ ባህሪያቸውና ስሪታቸው አይደለም ወይ? እናቲቱ የተባለችውስ  ተፈጥሮአዊ ባህሪያቸውና ስሪቷ እና የመኖር አላማዋ መወቀጥ አይደለም ወይ? እውነት በተለምዶ እንምሚባለው እናትና ልጅ ቢሆኑ እንንኳ የተፈጥሮ አላማዋና ግቧ መወቀጥ የሆነት እናት ወደ አላማዋና ግቧ (ያም መወቀጥ) የሚያደርሳትን ወቃጭ ልጅ ብትወልጅና ልጁ እናቱን አክባሪ፣ ለተፈትሮውና ለባህሪው ታማኝ ሆኖ የመወቀጥ አላማና ግቡ ያላትን እናቱስን ቢወቅጥ፣ ሙቀጫ የመሆን ህልሟን ቢያሳካና ፍቃዷን ቢፈፅም ያስመሰግነዋል፣ ብሩክ ያደርገዋል እንጂ ያስወቅሰዋል? ያስረግመዋል?
የማይገናኝ ነገር አገናኝቶ አብይ አህመድ እንዲህ አይነት የቡና ላይ ወሬ አደባባይ ይዞ ሲቀርብ ስንት መከራ ያለባትን ሀገር እያስተዳደረና የዜጎችን ሰቆቃ ለመቀስነ እንዲህ አይነት ጥቃቅንና አነስተኛ የመንደር ወሬዎችን የሚያወራበትን ጊዜ ለተሻለ ነገር ቢጠቀምበት ምን ነበረበት ያሰኛል። እንዲህ አይነት ትርኩስኩስ ወሬስ ለኢትዮጵያ ተፈጥሮአዊ ስሪት እና አላማ ፋይዳውስ ምንድነው? እናቱ ሲቀቅጥስ ባንዳ ማን ነው? አብይ አህመድ አይደለምን?
ከ14 ዐመቱ ጀምሮ ኢትዮጵያ ጨቋኝ፣ ልጅን ከልጅ በጎሳ፣ በነገድ፣ በቋንቋ የምታበላልጥ፣ ፍትሀዊነት ብቻ ሳይሆነ የብሔር ብሔረሰቦች እስር ቤት ናት  በዛም ምክንያት ፈርሳ እንደገና መሰራት አለባት ከሚሉት ጋር  ናት ብለው እናቱን ኢትዮጵያን ሲያሟት ከነበሩት ጋር አብሮ ሲያማ የነበረ፣ አፍርሰን እንሰራታለን ብለው ከተነሱት  ጋር በመተባበር ከልጅነት እስ ከእውቀቱ (?) የኖረው እናቱን ወቃጭ ባንዳ እና ለእድሜ ጠገቧ እምዬ ኢትዮጵያ ባዳ ሆኖ የጎለመሰ አብይ አህመድ አይደለምን? መንግስት አሸባሪ ነበር ያለንና የእምዬ ኢትዮጵያ ልጆችን፣ የአብራኳ ክፋዮችን በማሰር፣ በማሰቃየት፣ በመግደል እና በመሰወር ኢትዮጵያን ሲያሸብሩ፣ ሲወቅጡ የነበሩትና አሁንም ያሉት ባንዳዎችና ባዳዎች እነ አብይ አህመድ አይደሉምን? እድሜ ጠገብ የሆነችው ታላቋን ኢትዮጵያን እድሜዋን ቀንሰው 150 ብቻ ያደረጉት፣ ስለፍትሀዊነቷ ነብዩ መሀመድ (ሰ.ዐ.ወ.) የመሰከሩላትን የፍትህ ተምሳሌት የሆነችውን ደጓን ኢትዮጵያን ታሪኳን አዛብተው  ጨቋኝና ቅኝ ገዢ አድርገው ካለስሟ ስም የሚሰጡና ባእድና ባንዳ የሆኑትስ እነ አብይ አህመድ አይደሉምን?
ለመሆኑ ባእድና ቤተሰብ ብሎም ባልንጀራ የሚለካበት ሚዛን፣ የሚሰፈርበት መስፈሪያ ምን ይሆን?
ሻሸመኔ በአንድ ለሊት ስትጋይና ኢትዮጵያዊያን (ዜጋን የማያውቅ ስርዓት ይዘን ዜጋ ማለት ስለከበደኝ ነው) በነገድ ማንነታቸው አማራ፣ በእምነታቸው ደግሞ ኦርቶዶክስ የሆኑ የየትኛውም ነገድ አካላት ሲታረዱ የሻሸመኔን ከንቲባ አርፈህ ተኛ ያለው ሽመልስ አብዲሳ ዘመድ ተብሎ ነው ስለ ባዕድ የሚወራው?
ወይስ በቡድን ስለሚደፈሩ ትግራዋይ ሲነሳ «እነሱ እኮ በወንድ ነው የተደፈሩት፣ ሰሜን ዕዝ አለ አይደል እንዴ በሳንጃ የተደፈረ» ብሎ የሴቶችን መደፈር አቃሎ፣ ስቃያቸውን አጣጥሎ የተናገረው አብይ አህመድ ለትግራዋይ ቤተሰብ ሆኖ ነው የሴቶች መደፈር ይቁም፣ ረሀብን እንደጦር መሳሪያ መጠቀም ይብቃ የሚሉ ምዕራናዊያን ባዕድ የሚባሉት?
 ለመሆኑ ዘመድ፣ ወገን፣ ባልንጀራ ማን ነው? የችግር ግዜ የደረሰ ባዕድ? ወይስ አይቶ እንዳላየ ሆኖ ያለፈ ዘመድ ለሚለው በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ከቁጥር 25-37 እንዲህ ይላልና እነሆ!
25 እነሆም፥ አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው ተነሥቶ። መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ? አለው።
26 እርሱም በሕግ የተጻፈው ምንድር ነው? እንዴትስ ታነባለህ? አለው።
27 እርሱም መልሶ። ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።
28 ኢየሱስም። እውነት መለስህ፤ ይህን አድርግ በሕይወትም ትኖራለህ አለው።
29 እርሱ ግን ራሱን ሊያጸድቅ ወድዶ ኢየሱስን። ባልንጀራዬስ ማን ነው? አለው።
30 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ። አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት ደበደቡትም በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ።
31 ድንገትም አንድ ካህን በዚያ መንገድ ወረደ አይቶትም ገለል ብሎ አለፈ።
32 እንዲሁም ደግሞ አንድ ሌዋዊ ወደዚያ ስፍራ መጣና አይቶት ገለል ብሎ አለፈ።
33 አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥
34 ቀርቦም ዘይትና የወይን ጠጅ በቍስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው፥ በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደርያ ወሰደው ጠበቀውም።
35 በማግሥቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠና። ጠብቀው፥ ከዚህም በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ አለው።
36 እንግዲህ ከነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነው ማንኛው ይመስልሃል?
37 እርሱም። ምሕረት ያደረገለት አለ። ኢየሱስም። ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ አለው።
አዎ! ባልንደራ ምህረት የደረገ እንጂ በእህቶች ጉዳይ የሚሳለቅ አይደለም:: ባልንጀራነት የተበየነው በቅርበትና በዝምድና ሳይሆን <<ምህረት>> በሚባል መስፈሪያ ነው:: ለትግራዋይ ባእድ በመከራው የሚሳለቅበትና የሚያላግጥበት ነው:: ለአማራ ባእድ ልጆቼና ሚስቴ ታረዱብኝ ሲል ስለመከራ ማውራት ትታችሁ ስለብፅግና እናስብ የሚሉ ባለጌዎች ናቸው:: ለትግራዋይ ባእድ የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ገብቷል በጦርነቱስ እየተሳተፈ ነው ወይ ሲባል እግዚአብሔርን ለአድር ባይነቱና ለውሸቱ ምስክር አድርጎ የሚጠራ ዲያቆን ነው:: ለአማራ ባእድ የህዳሴ ግድብን እየሰራን ስለሆነ አትረብሸን አርፈህ ታረድ የሚሉት ናቸው:: ሰው በሰውነቱ ይከበር አይታረድ አይደፈር የሚለውን የሚያወግዝ ነው ባንዳም  ባዳም:: ይኼው ነው::
Filed in: Amharic