>

በአስቴር ላይ የሚፈፀመው ግፍ ማብቂያው የት ነው...???? (መቅደስ አበጀበለው)

በአስቴር ላይ የሚፈፀመው ግፍ ማብቂያው የት ነው…????

መቅደስ አበጀበለው

ወያኔ በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ብቻ አስሮ ካሰቃያቸውና ዘግናኝ ግፍ ከተፈፀመባቸው እንስቶች መካከል  አስቴር ስዩም ግንባር ቀደሟ ናት።
ተረኛው የኦሮሙማ መንግስት ወደስልጣን ሽግግር በሚያደርግበት ወቅት፥ ከእስር ከተፈቱ በርካታ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ሰዎች መካከልም አስቴር አንዷ ነበረች።
 ተረኛው የኦሮሙማ መንግስት ለራሱ የፖለቲካ ትርፍ ሲል እሱም በተላላኪነት በተሳተፈበት የወያኔ የአስተዳደር ዘመን በእስረኞች ላይ የተፈፀሙ ግፎችን የሚያትት ዘጋቢ ፊልም ሰርቶ ነበር። በዚህ ዘጋቢ ፊልም ውስጥ አስቴር የደረሰባትን በደል ስታስረዳ እንኳን አዕምሮ ያለው የሰው ልጅ ቀርቶ ግዑዝ ድንጋይን እንኳ በእንባ የሚያራጭ፣ እንደዚህ አይነት ግፍና ሰቆቃ እንዳይደገምም በሰማይና ምድር ፈጣሪ ስም መማማልን የሚያስመኝ ነበር። ዳሩ፥ ተረኛው የኦሮሙማ መንግስት ያንን አይነት ዘጋቢ ፊልም፥ የበደል ግፍ የተፈፀመባቸውን ሰዎች ቁስል እየቆሰቆሰ መስራት የፈለገው፥ መቀሌ መሽጎ በነበረው ወያኔ ላይ ነጥብ ለማስቆጠር እንጂ በእርግጥ በደልንና ግፍን ተፀይፎ አልነበረም።
 እንዲያም ስለሆነ ነበር፥ ኦሮሞን እርስበርሱ ለማበላላት ሀጫሉ ሁንዴሳን ራሳቸው በገደሉ ማግስት፥ የጃዋርና በቀለ ገርባ ማባያ አድርገው የባልደራስ አመራር የነበሩትን እስክንድር ነጋን፣አስቴር ስዩምን፣ ስንታየሁ ቸኮልና አስካለ ደምሴን ወደ ግፍ ማጎሪያ የወረወሯቸው። ከዚያ ሁሉ የወያኔ አካላዊና ስነልቦናዊ ግፍ የተረፈችው አስቴር፥ በድጋሚ የኦሮሙማው መንግስት የግፍ ግዞተኛ ስትሆን ገና ከተወለደ አስር ወር ብቻ ከሆነው ህፃን ልጇ ተነጥላ ነበር።
.
ይህ መሆኑ ሳያንስ፥ ከሰሞኑ ደግሞ በሀጫሉ ግድያ በዋና ተጠርጣሪነት ተይዛ የነበረችና “ተለቀቀች” ተብሎ ከተነገረ በኋላ በድጋሚ ወደእስር ቤት የተጋዘችው “ላምሮት” የተሰኘች ፅንፈኛ የኦሮሙማው አባቶርቤ ገዳይ ቡድን ጋር ንክኪ ያላት ሴት ከአስቴር ጋር በጠባብ ክፍል ውስጥ እንድትታሰር ከመደረጉም ባሻገር ተጨማሪ ግብረአበሮቿም በእዚያው ክፍል እንዲቀላቀሉ ተደርጓል። መቀላቀላቸው ለአንዳች አጥፊ ተልዕኮ መሆኑን ለማወቅ ቀናት አልተቆጠሩም። ላምሮትና ግብረአበሮቿ የድብደባ ሙከራ በአስቴር ላይ ፈፅመው የነበር ሲሆን የማረሚያ ቤት ፖሊሶች ለጊዜው ነገሩን ያረገቡት ቢመስልም በፖሊሶቹ ፊት እጅግ ነውረኛ የዘረኝነት ስድብን ሲሳደቡና “የእንገድልሻለን” ዛቻ ሲያሰሙ፥ “የማረሚያ ቤት” አዛዦችና ፖሊሶች፥ ተናብበው የሚሰሩ ይመስል አንዳችም መፍትሔ ሊሰጡ ፈቃደኛ አልሆኑም። እንደእስክንድር ሁሉ በአስቴር ህይወት ላይም የመገደል አደጋ አንዣብቧል። ባልደራስ ዛሬ ይፋ ባደረገው ደብዳቤ ላይም ከእስክንድር ህይወት አደጋ ላይ መውደቅ ጎን ለጎን ሌላዋ የባልደራስ አመራር አስቴር (ቀለብ) ስዩም ህይወትም አደጋ ላይ መውደቁን አትቷል። በእስክንድር ነጋና በአስቴር ስዩም ላይ እየተፈፀመ ያለውን የስነልቦናና አካላዊ ጥቃት፣ እንዲሁም በህይወት የመኖር መብታቸውን ገፍፎ ለማስገደል የሚደረገውን ግፍ ለማውገዝ፥ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው !
.
አስቴር ሆይ የራሔልን እንባ የተመለከተ አምላክ፥ እንባሽን ያብሰው ስለ ራሔል እንባ ፈንታ፥ ፈርኦንና ሠራዊቱን በቀይባህር ያሰጠመ አምላክ፤ እንዲሁ በግፍ የፈሰሰው እንባሽ ትናንትናና ዛሬ ያሰቃዩሽን ግፈኞች ዘላለማዊ እሳት ሆኖ ይፋረዳቸው!
Filed in: Amharic