>

ቅድስት ቤተክርስቲያን መንግስትን አሳሰበች....!

ቅድስት ቤተክርስቲያን መንግስትን አሳሰበች….!

የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንግስት በቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ እየተደረገ ስላለው ሁሉን አቀፍ ግፍ እና በደል መፍቴሄ እንዲሰጥ አሳስባለች
ለዓመታት በኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ እየተደረገ ላለው የርስት መቀማት፤የካህናት እና ምዕመናንን ግድያ፤የቅድስት ቤተርስቲያን ቃጠሎ፤ የቅድስት ቤተክርስቲያን በዓላት ቦታን ስም የመቀየር ወራሪ ሐሳብ ላይ ይፋዊ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ጠቅላይ ቤተክህነት ያለፉትን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተመስርቶ አስጠንቅቋል።የማስጠንቀቂ ውሳኔም በዋናነት
“የመሎ ላኅ እና የሆሳዕና ከተማ ጥምቀተ ባህር ቦታ በቀደመው የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሰረት በአስቸኳይ የይዞታ ካርታ ተሰርቶ እንዲሰጥ”
“በበዓላት ማክበርያ ላይ በልማት ስም የሚደረጉ ማናቸውም ዓይነት መንግስታዊ ግንባታዊች ያለቅድስት ቤተክርስቲያን እውቅና እና ይሁንታ እንዳይፈጸም”
በGoogle map ላይ የመስቀል አደባባይ ስምን “ኢድ አደባባይ” በሚል ስያሜ እየተደረገ ያለው የጠብጫሪነት ተግባር ሙሉ በሙሉ በመንግስት በኩል ርምጃ ተወስዶ እንዲቆም
“የአፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የይዞታ ጉዳይ በአፋጣኝ መፍቴሄ እንዲሰጠው”
“የጃንሜዳ የጥምቀተ ባህር የባለቤትነት ጉዳይ በአስቸኳይ ለቅድስት ቤተክርስቲያን እንዲተላለፍ እና ቤተክርስቲያንም ለማህበራዊ ግልጋሎት እና መንፈሳዊ ተግባራት ለማዋል ፕሮጀክት የነደፈች መሆኑን”
“በመላ ሀገሪቷ በተለይም በኦሮሚያ ፣በደቡብ፣በሲዳማ፣ በቤኒሻንጉል፣በአማራ፣በትግራይ እና በሌሎች ክልሎች በቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ለሚገኘው ስደት ሞት እንግልት እና መከራ መንግስት አስቸኳይ መፍቴሄ እንዲሰጥ እና የተሰደዱ ምዕመናንን በአስቸኳይ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ”
የሚል ሐሳቦችን የያዘ ማስጠንቀቅያ ሲሆን በዋናነት የጠቅላይ ሚኒስተር ቢሮን ጨምሮ ልዩ ልዩ ለሆኑ ባለድርሻ የፌዴራል መስርያ ቤት የተላከ ሲሆን በግልባጭም ችግሮች ለተከሰቱባቸው የክልል መንግስታት ተልኳል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Filed in: Amharic