>
5:21 pm - Sunday July 20, 1603

የብልጽግና አካኄድና የአማራው ሚና በምርጫ 2013 (ሲናጋ አበበ)

የብልጽግና አካኄድና የአማራው ሚና በምጫ 2013      

 

ሲናጋ አበበ


         አማራ ወደድንም ጠላንም ኢትዮጵያ በዓለም ዙሪያ የምትኮራባቸውን ሥነ ጽሑፎች፤ የአገር ግንባታ፤ የሙዚቃ፤ የሃይማኖትና ባህሉዋን ሁሉ  ጠነስሶና አበልጽጎ አብረውት ላሉት ወንድሞቹ አበርክቶ እነሆ ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ ገዝፎ ከመታየት ይልቅ ኢትዮጵያዊነትን እንደመለያው ያደረገ ሕዝብ መሆኑ አሌ አይባልም፡፡

     ሕውሓት የተባለው ድርጅት በለስ ቀንቶት ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር በቻለ ጊዜ ከዚህ ቀደም ደደቢት ላይ አማራ ጠልነቱን በጉልህ በማኒፌስቶው ያንጸባረቀውን ወደ አዲስ አበባ ተሸክሞት በመምጣት ለአገዛዙ እንዲያመቸው አገሪቱን በዘር ከፋፍሎ ጎረቤታሞቹን በማናከስ ለ27 ዓመት እርስበርሱ እንዳይተማመን አንዱ አንዱን ለማጥፋት እንዲንቀሳቀስ ሸርቦ በማስቀመጥ ጥዋት ማታ በመቆስቆስ ሲያናጫቸው ቆይቶዋል፡

          አሁን ባለንበት ወቅት ወደ ዴሞክራሲ የሚሊያሸጋግረን ብቸኛው አማራጭ ምርጫ ነው በተባለበት ወቅት ምርጫውን ለማስፈጸም ሸብ ረብ በሚባልበት ወቅት ሁሉም የሚቁቁት ፓርቲዎች በዘር ላይ ያተኮሩ መሆኑ ያልዘሩት አይበቅልም እንዲሉ ከዛሬ 30 ዓመት ጀምሮ እንደተከፋፈለውም ዛሬም ሁሉም ዘመዱን ፍለጋ ገብቶ እነሆ አብዛኛው ፓርቲ  ሁሉ ምሥረታው ለኢትዮጵያ አደጋ በፊቱዋ እንዲጋረጥ በተፈለገው መልኩ ተዋቅረዋል፡፡

       ከሦስት ዓመት በፊት በኢህአዴግ ውስጥ በተከፈተው የአመራር ክፍተት ብአዴን የተባለው የአማራ ፓርቲ ተብዬው፤ ለአማራው ህልውና ቸርሶ ደንታ የሌለው፤ ለኦሮሞ ኦፒዲኦ ድጋፍን በመስጠቱ ዶክተር አቢይ አህመድ የመሪነቱን ልጉዋም ሊጨብጡ ስለቻሉና ብልጽግና የተባለ ፓረቲ አቁዋቁመው በኦሮሞው የበላይነት የአማራውን ፤የሱማልውን፤ የትግሬውን ወዘተ. ሁሉ የብልጽግና አካል አድርገው ቀረጹጽ፡፡ ብልጽግና ሁሉንም አቅፌያለሁ ይበል እንጂ በትክክል የሚያስፈጸመው ግን የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባርን  ዓላማ ለማሳካት እንደሆነ እያደረ ግልጥ መሆኑ ተረጋግጡዋል፡፡ ብልጽግናና ኦነግ አንድ አካል አንድ አምሳል መሆናቸው በተግባር እየታየ ነው፡፡ ኦነግ ወይም ኦነግ ሸኔ በዳቦ ስም ህዝብን እያወናበዱ አማሮች በሠፈሩባቸው መጤ በሚል እሳቤ በቤንሻንጉል፤ በወለጋ ፤ በባሌ ወዘተ. በተደራጀና ዘመናዊ ጦር በታጠቀ ቡድን እጅግ አሰቃቂ ግድያ፤ መፈናቀል፤ መሰደድ ሲፈጽሙ ቆይተው ወደ ራሱ አማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ህዝብ ላይ ወደር በሌለው መልኩ ከተሞች እንዳሉ እንዲወድሙ ተደርጉዋል፡፡ ይህ አህዛባዊ ጭፍጨፋ ሲፈጸም መንግሥት ማስቆም ቀርቶ ከድርጊቱ በሁዋላ እንኩዋን መቆርቆሩን ለማሳየት አልተግደረደርም፡፡ ቢያንስ የአዞ እንባ እኩዋን አላሰየም፡፡

       አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዴንና የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ አባል “የኦሮሞችን ተረኛነት” በእብሪት ከመናገር ባሻገር “አማርኛን በኦሮምኛ እንተካዋለን”

“የሰበሩንን ሰበርናቸው ፤ያዋረዱንን አዋረድናቸው፤ ከኛ ፈቃድም ውጭ እዳይነቀሳቀሱ አድርገናቸዋል” ብሎ አቢይ አሕመድ ሽመልስ በኤሬቻ በዓል ላይ የተናገርውን በባሌ ጉብኝቱ ወቅት መድገሙን እናስታውሳለን፡፡

     አቢይም በመቀጠል “እግዚአብሔር የሰጠንን አእምሮ ተጠቅመን በተግባር በሚታይ ሥራ ሀገር ቀይረን የኦሮሞን ሕዝብ ለማኩራት በልዩ ቆራጥነት ሌት ተቀን እየሠራን ያለን በመሆኑ በዱዓችሁ አትርሱን” ብሎ የቦረና ሼኮችን ተማጽኗል፡፡

     የመላ ኢትዮጵያ መሪ መሆኑን ረስቶት፤ አቢይ ሙሉ ኦሮሞ ስላይደለ ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ መስሎ ለመታየት በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነትን ለማትረፍ እንደሆነ ቢገመትም “የቆጡን አወርድ ብላ የብብትዋን ጣለች” እንደተባለው ሊደርስበት የሚችለውን አላጤነውም፡፡

       በአማራ ላይ ያለው የኦነግ ጥለቻ አቢይም እንደሚጋራው በተግባር ተረጋግጡዋል፡፡

        ብልጽግና በአማራው ላይ የሚወረውረውን የጥላቻ ንግግር አማራው ሁሉ እንደሌላው  እንደሚሰማው ጥርጥር የለንም፡፡ 

          በበልጽግና ፓርቲ ሥር ለመወዳደር የቀረቡ አማሮች እራሳቸውንና ወገኖቻቸውን ሰድበውና ለሰዳቢ አሳልፈው ሰጥተው ያሉት እራሳቸውን ያዋረዱት ለሆዳቸው ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ እንዳሉት ለሆዳቸው ያደሩ መሆናቸው ነው፡፡ 

           እንዴት በብልጽግና ቲኬት ተወዳድሮ ለማሸነፍም ሆነ ለመሸነፍ የተሰለፉት የራሳቸውን ዘር ያዋረዱ ስብዕናቸውንም መሳቂያ ያደረጉ ናቸው፡፡

     ከዚህም በተጨማሪ ብልጽግና የሚያቀርባቸው እጩዎች የተሰለፉት አማራውን አዋርዶ የኦሮሞን ገናናነት ለማስፈን ከተዘጋጀ ፓርቲ ጋር ነው፡፡ የኢትዮጵያን ትልቅነት ለማይመኙት  የብልጽግና አጩዎች አማራው ድምጹን እንዴት ይሰጣል፡፡ ለሚያዋርደውና ለሚገለው ጥብቅና ይቆማል ብሎ ማሰብ ይዘገንናል፡፡  ያገሬ ሰው “ጨው ለራሰህ ስትል ጣፍጥ አለበለዚያ ድንጋይ ነህ ብለው ይወረውሩሃል” እንደተባለው አማራው በመንቃት እራሱን ማስከበር የሚገባው ሰዓቱ አሁን ነው፡፡

     ሰኔ 4 ቀን 2013 ዓ.ም.                    

Filed in: Amharic