ያስተዛዘበን የ‹‹ቃል በተግባር›› ዘጋቢ ፊልም
ኤልያስ ደግነት/የሺ/
ጭፍን ያለ ጥላቻም ሆነ ድጋፍ ክፉ ነው!!! በጭፍን ስንደግፍ ለምን ተነካብኝም ታብኝም እንላለን፤በጭፍን ስንጠላም ቅድስናውንም …አንይ በሚል ዓይንህን ለአፈር ማለት ይቀናናል፡፡ይህ ነገር ገደል ይዘውን ከሚገቡ ነገሮች አንዱ እና ዋነኛው ይመስለኛል፡፡የሚነቀፈውንም እየነቀፉ የሚደገፈውንም እየደገፉ መሄድ ተገቢ ነው፡፡ያስተማረውንም የተናገረውንም የኖረ መሪም መምህርም ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ መሪ በሉት ተመሪ የተናገረውን ኑሮ፣ተግብም፣ከፈፁማዊነት ጫፍ ደርሶ አያውቅም፡፡
ከሰማነው ይልቅ ያየነውን እናምናለን፤ያየነው የሚደነቅ ከሆነም ይበል እንላለን፤ሊነቀፍ የሚገባው ከሆነም እንዳይደገም ለማት ወደኃላ አንልም!! እናም …..ምን ለማለት ነው፡፡
ማታ ያየነው የ‹‹ቃል በተግባር›› ዘጋቢ ፊልም አስደስቶናል/ኛል/፡፡ እስየው ነው…ይበል ያሰኛል፡፡
ዘጋቢውን አያችሁት ወይ ስላቸሁ በጭፍን ጥላቻ ደግሞ ለፖርክ እና ለመንገድ የምን እዩኝ እዩኝ ማለት ነው ብላችሁ ልታጥላሉ የሞከራችሁ ወዳጆቼ ከትዝብቴ ሚዛን ተሰቅላችኃል!!ሰው ስለጠላ መጥላት፣ሰው ስለወደደ መውደድ የራስን የአስተውሎት ሚዛን ያዛባል እና ከደቦ ፍርድና ፍረጃ መውጣቱ ተገቢ ነው፡፡ ነገራችን ሁሉ አመክንዩ ላይ ቢመሰረት እንደምን ሸጋ በነበረ፡፡ደግሞም በትልቁም በትንሹም አቅላችንን እስክንስት ጉንጭ ባላለፋን …አልፍተንም ባልተገማመትን ነበር፡፡
ለማናቸውም ያየሁትን እውነት አይቼ ወድጀዋለሁ …ደስም ብሎኛል!!!ክምር ቁልል ድንጋይ እና የመንገድ ስፋት እና ንፅህና የዲሞክራሲ መገለጫ እንዳልሆም አውቃለሁ!