>

ያየሁትን ከካዱኝ ያላየሁትንና በውስጥዎ ያለው እንዴት ልመንዎ...?!!? (ጋዜጠኛ ወንድ አጥር ምንተስኖት)

ያየሁትን ከካዱኝ ያላየሁትንና በውስጥዎ ያለው እንዴት ልመንዎ…?!!?

ጋዜጠኛ ወንድ አጥር ምንተስኖት

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ “በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል የምልበት ቦታ የለም!!” አሉ?
*.   አዎ አማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል!! ከእርስዎ በእሳቤም በመታበይም ከተሸበቡት በጥቅማጥቅምም ከታወሩበት ይልቅ እኔና ጓደኞቼ እውነቱን ደም ረግጠን ዝምብና አሞራ ተወዳጅተን ሞትን አሽትተን አናውቀዋለን!!
ፕሮፌሰር #እኔ_የየትኛውም_ፓርቲ_ደጋፊ_ባልሆንም እርስዎ የሚክዱትን እውነት በአካል ደም ረግጬም፣ በዘር ምክኒያት ገድለው የደበቋቸውን አማራዎች አስክሬን በዝንብና በአሞራ ተመርቼ አይቼም፣ በነ  በታሪክ አረጋግጬም አውቀዋለሁ አይቸዋለሁም።
እርስዎ ወይ እውነታውን አልተረዱትም እንዳልል ትልቅ ሰው ነሁና ክደውታል!! አልሰሙትም እንዳልል ዝንብ እያባረርን አስክሬን እያሸተትን አሳይተንዎት ክደውታል።
በእርስዎ ጉልምስና በወያኔ የስልጣን ደጅ በኦሮሚያ በአርባ ጉጉ በወለጋ … ጉድጓድ ላይ የተወረወሩ አማራዎችን አስክሬንስ ምርምር ላይ ስለነበሩ ይርሱት እንዴት አሁን በጎራርፈርዳ፣ በወለጋ፣ በመተከል፣ በወልቃይት ማይካድራ… ያልደረቀውን የአማራ ሞት ብቻ ሳይሆን እርስዎ በግርድፉ ለወሬ ማሞቂያ የጠቀሱትን ዓለም አቀፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል ድንጋጌዎች:-
#ማፈናቀል፣
#አስገድዶ_በዘር_መበረዝ
#እንዳይወልድ_እንዳይራባ_ማድረግ
#እንዳይኖር_በዘሩ_ምክኒያት_ብቻ_ተለይቶ_እንዲሞት ወዘተ በወልቃይት፣ጠገዴ፣ ጠለምት፣ራያ የተፈረደበትን አማራ እንዴት ይክዱታል። ከካዱትስ ይህን ህዝብ በምርጫ እንዴት ይወክሉታል?
እሺ ህዝቡን ሸወድኩ ብለው ይካዱት  #እኔን_አብረውኝ_የዘገቡ_ጀግኖችን_የማይካድራ_አማራዎችን_ትኩስ_ደም_ያየነውን #አስክሬን_ሸቶ_ሽቶ_እየተረጨ_የተቀበረበትን_ሁነት_ያየነውን_ይክዱናል??
በነገራችን ላይ አስክሬኖቹን በትኩሱ ማየትን ብቻ ሳይሆን ከወራት በኋላ በጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ በጳውሎስ ሆስፒታል፣ በፌደራልና አማራ ፖሊስ ኮሚሽን የተደረገውን በማይካድራ በየቦታው የተቀበሩ አስክሬኖችን እያስቆፈሩ የጭንቅላት ቆጠራ /Head count/ እያመመኝ ደግሜ ያየሁ ሰው ነኝ!! (ከዘገባው ከወር በኋላ ከባልደረባየ አክሊሉ ምንተስኖት ጋር)
እርስዎ ስለሞቀዎት የበረደው እንደሌለ አድርገው እውነትን የሚያስቡ አሆነ ጥመቱ አናትዎ ላይ ነው!!
አማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል!!
እንባውም አልታበሰም!!
እውነትን እየካዱ ከሞቱ በላይ አያሳምሙት!!
ወይ ዝም ይበሉ ካለዛ በህዝብ ደም አይዛበቱ!!
ነገሩ እርስዎ ከላይ ሆነው ወደ ችግሩ ሳይወርዱ የስሚ ስሚ ሰምተው እንዴት አውነቱንያውቁታል? ቢሰሙትስ እንዴት ያረጋግጡታል?
ወይ ወልቃይት ሄደው እውነቱን ያውቁታል ካለዛ እውነትን አውልቀው ጥለውታል!!!
#ይፈሩ_የጭቁኖችን_አምላክና_በራማ_የሚጮኸውን_የንጹሃን_አማራዎች_ደምም_ይፍሩ!!
አማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል!! ከእርስዎ በእሳቤም በመታበይም ከተሸበቡት ይልቅ እኔና ጓደኞቼ እውነቱን ደም ረግጠን ዝምብና አሞራ ተወዳጅተን ሞትን አሽትተን አናውቀዋለን!!
ባወሩት ይፈሩ 
ይቅር ይበልዎት 
ወይ ይቅርታ ይጠይቁ!!!
አብረን እውነትን የዘገብን ጓደኞቼ ክብር ለናንተ ይሁን!! ጀግንች ናችሁ!!
Filed in: Amharic