የብርሃኑ ነጋ ተቃርኗዊ የፖለቲካ – የአስተሳሰብና የማንነት ቀውስ!!!
ጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸው
* “አማራ መጤና ሰፋሪ ነው”
” በአማራ ላይ የተፈፀመ የዘር ማጥፋት ወይም ጭፍጨፋ የለም” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
* በአሁኑ ምርጫ የብርሃኑን ፓርቲ ከመምረጥ ብልፅግናን መምረጥ ይሻላል፤ ምክንያቱም ሁለቱም ያው ስለሆኑ የስም እንጂ የግብር ልዩነት የላቸውምና !
በአንድ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ቢሮ መጥቶ የኢሳት ጋዜጠኞችን ማነጋገር እፈልጋለሁ ብሎ ሰበሰበን::
ብርሃኑ ነጋ “በኢሳት አሰራር ላይ የግሌን አስተያየት ለመስጠት እፈልጋለሁ “በሚል ገለልተኛ መስሎ የጠራው ስብሰባ ነበር::
ስብሰባው ሲጀመር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢሳትን የወቅቱ አሰራር በመተቸት ተቋሙ በዚህ ከቀጠለ በ6 ወራት ውስጥ ሊዘጋ እንደሚችል በማስፈራራት ዛተብን::
ይህም የኢሳቱን የዲሲ ቢሮ ለመዝጋት የነበራቸውን ሴራ በገደምዳሜ እየነገረን ነበር::
በዚህ አጋጣሚ “በላ ልበላሃ ” በተሰኘው የኔ ፕሮግራም ላይ ስለሚቀርቡ ሰዎች አሉታዊ አስተያየት መስጠት ጀመረ::
ከነዚሁም መካከል :-
1- አቶ ያሬድ ጥበቡ
2-ዶ/ር ፍስሐ እሸቱ እና
የመሳሰሉ ሰዎች ለምን ኢሳት ላይ ታቀርባላችሁ ? በማለት ወደ እኔ እያየ ቅሬታውን ለመግለፅ ሞከረ:: በውቅቱ እነዚህን ሰዎች ያቀረብኩት እኔ ነበርኩ::
በጣም ገረመኝና ” ለምን ? ” የሚል ጥያቄ አቀረብኩለት:: በደፈናው “የሚረቡ ሰዎች አይደሉም “በማለት መለሰልኝ::ለጥያቄየ የሚያረካ መልስ ስላልሰጠኝ ደግሜ ማብራሪያ ጠየቅኩት::
ኢሳት ነፃ ሚዲያ በመሆኑ የፖለቲካ ሰዎችን አመለካከት ማስተናገድ እንጅ ” ለምን እኛ እንፈርጃቸዋለን ” ስል ርእስ ከፈትኩ:: “እንደምትላቸው ከሆኑም አይረቡም ማለት ያለበት አድማጭ ተመልካቹ ነው እንጅ እንዴት ሚዲያ ላይ አታቅርቡአቸው ይባላል ” ስልም ተከራከርኩ::
ለዲሞክራሲ እና ለነፃነት የሚታገል ሚዲያ ለምን በሰዎች ላይ ገደብ ይጥላል? አንተስ እንዴት እንዲህ ልትል ቻልክ እያልኩ አከታትየ ጠየቅሁት::
“ለዲሞክራሲና ለነፃነት እታገላለሁ እያልክ አፈናን እንዴት ታበረታታለህ ” በሚል ስሜት ነበር ዶር ብርሃኑን የጠየቅኩት ::
በዚሁ አጋጣሚም ዶ/ር ታየ ወልደሰማያትና አቶ ልደቱ አያሌው በኢሳት ላይ ኢንተርቪው ማድርግ ፈልጌ እነሲሳይ አጌና እንዳልፈቀዱ ነገርኩት::
ዶር ብርሃኑ ገልመጥ እና በስጨት ብሎ “ጭራሽ እነሱንም ልታቀርብ ፈልገህ ነበር? “በሚል ስሜት ርዕሱን ጨርሶ ለመቀየር ሞከረ::
መልሱን እንደምጠብቅ በማሳወቅ ሁሌም እንደምለው “ጉዳዩን እንደ ቅድመ ምርመራ (Sensorship) ወይም አፈና አድርጌ እንደምቆጥረው አስረግጬ ተናገርኩ::
ዶር ብርሃኑም ምንም ትኩረት ያልሰጠው በመምሰል ” በነገራችን ላይ ሰዎቹ ስለማይረቡ ነው እንጅ አመለካከታቸውን ፈርቼ አይደለም” በሚል ሊያድበሰብሰው ሞከረ:: ሰዎቹን የሚጠላው ግን የፖለቲካ ባላንጣዎቹ አድርጎ ስለሚቆጥራቸው መሆኑ ገብቶኛል::
ወዲያውኑም ስለ ዶር ብርሃኑ ማሰላሰል ጀመርኩ:: ቀደም ሲል “የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ ” ብሎ በመሰረተው ስብስብ ውስጥ ከኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኦዴግ / እና ከአፋር ነፃነት ፓርቲ መሪዎች ጋር እየተፈራረመና እየተላላሰ ” የአማራ ተወካዮች ግን ብሄርተኞች ስለሆኑ መጋበዝ የለባቸውም ” ማለቱን
አስታወስኩ::Double standard!!
እኔንም በተመለከተ በአሉባልታ የሚሰማውን ይዞ “የአብን ተወካይ ነውና ተጠንቀቁት ” እያለ ለኢሳት ማኔጂንግ ኤዲተሮች መመሪያ እንደሚሰጥ አውቅ ስለነበር በወቅቱም ፀረ አማራነቱን መገንዘብ ችየ ነበር:: በዚያ ስብሰባችን ጊዜ ደግሞ ዶር ብርሃኑ ፀረ ዲሞክራቲክ አመለካከት እንዳለው ተገነዘብኩ::
በወቅቱ በነበረው አጋጣሚ ስለ ብርሃኑ ነጋ ማንነት በደንብ እንድገነዘብ አደረገኝ:: ሰውየው እውነትም ፀረ አማራ እና ፀረ ዲሞክራሲያዊ መሆኑን::
ያኔ በውስጤ የተሰማኝ ” ይህ ሰው ለኢትዮጵያ ነፃነት እታገላለሁ እያለ ለካ ለስልጣን የሚቋምጥ ሰው ነው ?” የሚል ነበር::
“እንዴት እንዲህ አይነት ሰው ይህን አመለካከት ይዞ ሀገር ሊመራ ይችላል ? ” በሚልም በፊት ስለሱ የነበረኝን በጎ አመለካከት በመቀየር ውድቅ አደረግኩት::
በዚህ አጋጣሚ በሱ ላይ የተሳሳተ በጎ ምስል ይዛችሁ “ብርሃኑ ” ኢትዮጵያን ሊያድን ይችላል “ብላችሁ ለምታስቡ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ አንድ ቁምነገር ልንገራችሁ::
በአሁኑ ምርጫ የብርሃኑን ፓርቲ ከመምረጥ ብልፅግናን መምረጥ ይሻላል:: ምክንያቱም ሁለቱም ያው ስለሆኑ ልዩነት የላቸውምና ::
እውነት እውነት እላችሁአለሁ
“ብርሃኑ ነጋ ለወንበር የቋመጠና ዘጠኝ ፓርቲ የቀያየረ የስልጣን ጥመኛ ስለሆነ ሀገርን አይጠቅምም:: – አትምረጡት!!!
“አማራ መጤ ነው ! አማራ ሰፋሪ ነው
አማረ በዘሩ ተለይቶ አልተጨፈጨፈም ” የሚል ቀጣፊን በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ ማየት አንፈልግም::